spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeነፃ አስተያየትየፕሪቶርያው ስምምነት አበይት ስህተቶችና ያስከተሏቸው መዘዞች (የቀይ ባህር ሰው)

የፕሪቶርያው ስምምነት አበይት ስህተቶችና ያስከተሏቸው መዘዞች (የቀይ ባህር ሰው)

የፕሪቶርያው ስምምነት

የቀይ ባህር ሰው

 1. የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት በአሜሪካ ከፍተኛ ጫና፡ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ነት፡ ህዳር 2, 2022 ዓ ም የተኩስ ማቆም ስምምነትን ያካተተ”የፕሪቶርያ ስምምነት” ተፈራረሙ። ይህ ስምምነት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ይፈጥራል ተብሎ ተስፋ ቢጣልበትም፡ በአካባቢ ው ከፍተኛ አለመተማመን፡ውጥረትና እልቂት አስከትሏል። ለዚሁ መዘዝ ዋናው ምክንያት በፕ ሪቶርያና በናይሮቢ የተፈጸሙት አብይት ስህተቶች መሆናችው ይጠቀሳል።
 2. እነዚሁም፡ (1) የወያኔ ሽንፈት በተቃረበበትወቅት ጦርነቱ መቋጫ ሳያገኝ እንዲቆም መደረጉ፤ (2) በኢትዮጵያ ፓርላማ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀና እገዳከተጣለበት ህወሓት ጋር ድ ርድር መደረጉ፡ (3) እጅግቁልፍ የሆነው የወያኔ ሰራዊት ትጥቅ መፍታትየሚለው በፕሪቶርያው ስምምነት ሰፍሮ የነበረውአንቀጽ በናይሮቢ እንዲቀየር መድረጉ፡ (4) በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጲ ያ ዋናኛ አጋሮች የነበሩትንየኤርትራንና የፋኖ ታጣቂዎችን ጥቅም አሳልፎ መስጠቱን ያጠቃልላ ል። ከዚህ በላይ የተጠቀሱትንአራት ነጥቦች በዝርዝር እንመለከት።

አንደኛው ስህተት፡ ወያኔ በጦር ሜዳ ሽንፈቱበተቃረበበት ወቅት ጦርነቱ ሳይቋጭ መቆ ሙ !

 1. የኢትዮጵያን የኤርትራ ጥምር ሃይል ትግራይን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጥርና መቀሌ ገ ብቶ የወያኔን ፍጻሜ ለማረጋገጥ በተቃረቡበት ወቅት፥ አብይ አህመድ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ወደ አስመራ በመላክ፡”አሜሪካ ጦርነቱን አቁም! መቀሌ እንዳትገባ፡ከወያኔም ጋር ድርድር አድርግ ! በ ማለት ከፍተኛ ጫናእያደረጉብኝ ነው”፡ የሚል መልእክት ያደርሳል። በወቅቱ የኤርትራ መንግስት የሰጠው መልስ “ተው ! በአሁኑ ሰዓት ተኩስ ምቆም ጠቃሚ አይደለም፤ ብዙዋጋ ከፍለን ያገኘና ቸውን ድሎች በማጠናከር መቀሌ ገብተን የወያኔን ፍጻሜ ማረጋገጥ አለብን። አሁን የተኩስ አቁ ም ስምምነት ማድረግ፥ ወያኔን ከሞትማዳንና በስልጣን እንዲቀጥል ብቻ ሳይሆን ለወደፊት በቀጠናው ከፍተኛ ቀውስ እንዲፈጥር ጭምር ዕድል መስጥት ይሆናል፡ ይህም ስህተት ከፍተኛ ዋጋ በድጋሚ አንደሚይስከፍልህ መገንዘብ ያስፈልጋል” የሚል ነበር።
 2. የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱን በአሸናፊነት ከመቋጨት ይልቅ፡ የኤርትራን ምክር ወደ ጎን በመግፋት፡ ህወሓትን ከመሞት ላማዳን በአሜሪካ በተሰጠው ተልእኮ መሰረት በፕሪቶርያ የተኩስ ማቆም ስምምነት ተፈራረመ። ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኞች ይህን ስህተት አስመልክተው “ይህ ስምምነት አብይንና ቀጠናውን ለወደፊት ከፈተኛ ዋጋ ያስከፍላቸዋል” ብለው ነበር።

ሁለተኛው ስህተት፡ በኢትዮጵያ ፓርላማ ሽብርተኛተብሎ እገዳ ከተጣለበት ህወሓት ጋር ድርድር መደረጉ!

 1. የኢትዮጵያን ሰሜን እዝ ሰራዊት በድንገትአጥቅቶ፡ ለሁለት ዓመታት ለዘለቀውና በመቶ ሺዎችለሚቆጠሩ ህይወት ዋጋ ላስከፈለው ጦርነት፡ በቢልዮኖች ዶላር የሚገመት የንብረት ውድመት ላስከተለውና፡ ለብዙ ሚልዮን ህዝብ ላፈናቀለው ጦርነት፡ ዋናው ተጠያቂ ወያኔ መሆኑ በግልጽእየታወቀ፡ አብይ አህመድ ለምን ከወያኔ ጋር ድርድርላማድረግ ተጣደፈ? ህወሓት በኢት ዮጵያ ፓርላማሽብርተኛ ተብሎ እንደተፈረጀና እገዳ እንደተጣለበት በግልጽ እየታወቀ አብይ አህመድ ህወሓት ትግራይውስጥ ስልጣኑን እንዲቆጣጠርና እንዲቀጥል ለምንፈለገ? የሚሉ ጥያ ቄዎችን ማንሳት ተገቢ ነው።
 2. ስምምነቱ ” በትግራይ ክልል የሚገኙትንሁሉን የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተተ (Inclusive Regional Administration) ይቋቋማል” የሚል ነው።ሆኖም የተቋቋመው የትግራይ ጊዚያዊ መንግስት ፡ከስምምነት ባፈነገ ጠ መልኩ ፡ በክልሉ ያሉትን ሌሎችየፖለቲካ ድርጅቶችን ብማግለል፡ ህውሓት ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ያደረገ ነው። ከፕሪቶርያ ስምምነት ውጪ፡ ህውሓት ብቻውን ስልጣን እንዲቆጣጥር መደረጉ፡ አለመግባብት እንዲቀጥልና በመንግስትና በወያኔ መሃል ከፈተኛ አለመተማመን እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ህውሓት ያለ ተቀናቅኝ በብቸኝነት ሙሉ ስልጣን እንዲይዝ ስለተደረገ፡ የትግራይ ህዝብ አንገበጋቢ ጥያቄዎች መመለስ ላይ ከማተኮር ይልቅ በስልጣን ሽኩቻ ተንጦ ለ60 ቀናት የዘለቀ
  የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መቀመጡ የዚሁ ስህተት ዋነኛው ውጤት ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።
 3. የብልጽግናው መሪ ህወሓት በሽብርተኛነት መፈረጁን ጠንቅቆ እያወቀ፡ የህወሓትን መቀጠል አንደሚፈለግ ያረጋገጥው፥ ወያኔ የሽብርተኝነት ፍርጃ እንዲነሳለት ያቀረበውን ጥያቄ መቀበሉና የትግራይ ክልል መንግስትን አግልሎ፡ ለህወሓት ህጋዊ ዕውቅና ሰጥቶ ስምምነት በማ ድረጉ ነው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ አብይ አህመድ ስለ ህወሓት የስልጣን ጥምና አስከፊ ባህርይ በቂ ግንዛቤና ጥልቅ ዕውቀት ስለሌለው አልያም ለሌላ ስውር አላማ ሊጠቀምባቸው ስለአሰበ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተየያቶች ይቀርባሉ ። ህወሓት ስልጣን ላይ እንዲቀጥል ማደረጉና እሱን ተከትሎ ለተፈጠረው ቀጣይ ውጥረትና አለመረጋጋት ዋናው ተጠያቂ አብይ አህመድ ለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ለወደፊትም ተጨማሪ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው መገመት አያዳግትም።

ሶስተኛው ስህተት ፡በስምምነቱ ቁልፍ የሆነውየወያኔ ትጥቅ የመፍታት አንቀጽ በናይሮቢ መቀየሩ !

 1. ጦርነቱን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያስችላል የተባለው፡ 15 አንቀጾችን ያካተተው የፕረቶሪያ ስምምነት ውስጥ፥ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የህውሓት ትጥቅ መፍታት ጉዳይ ነበር። የወያኔ ሰራዊት የትጥቅ መፍታት መርሃ ግብሮች ሶስት እርስ በርስ የተሳሰሩ ሂደቶችን ያጠቃለለ ነው።(1)ትጥቅ ማስፈታት ((Disarmament)፤ (2) ሰራዊትማስናበት (Demobilization)፤ (3) መልሶ ማቋቋም(Reintegration) ያጠቃልላል። በዚህ ስምምነትአንቀጽ 6 ላይ፡” ስምምነቱ በተፈረመ በ30 ቀናት ውስጥ የህወሓት ሰራዊት፡ ቀላልና ከባድ መሳርያዎችን ጨምሮ የያዘውን ሙሉ ትጥቅ ይፈታል” የሚል ሃረግ በግልጽ ሰፍሯል።
 2. ይሁን እንጂ፡ ስምምነቱ ከተፈረም ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሁለቱ ወገኖች ከፍ ተኛ የጦር አዛዦች ታህሳስ 12, 2022 ዓ ም ፡ የናይሮቢ መግለጫ (Nairobi Declaration)” የተሰኘ ሰነድ በኬንያ ተፈራረሙ። ይህ የናይሮቢ መግለጫ ያንን ቀደም ሲል በፕሪ ቶርያ ግንኙነት ላይ የተደረሰበትንና በግልጽ በስምምነቱ አንቀጾች ውስጥ ሰፈሮ የነበረውን የወያኔ ትጥቅ መፍታት ጉዳይ የሚቃረንና የሚያፈርስ ነው፡ ፡የፕሪቶርያ ስምምነት አንቀጽ 6 ፡ “የትግራ ይ ሰራዊት በ30 ቀን ውስጥ ትጥቅ ይፈታል” የሚለውን ሃረግ በመሰረዝ ፡ “የወያኔ ትጥቅ መፍታት ጉዳይ በአካባቢው ከሚገኙት የውጭ ሃይሎችና ከፌደራል ሰራዊት ውጪ የሆኑ የውስጥ ሃይሎች ከሚያደርጉት ከያዙት ቦታ መለቀቅ ሂደት ጋር (concurrently) በተመሳሳይ ጊዜ ተፈጻሚ ይሆናል” በሚል አፍራሽና አወዛጋቢ አንቀጽ አንዲለውጥ ተደርጓል። ይህ ቁልፍ አንቀጽ በመቀየሩ ብዙ መዘዞች አስከትሏል።
 3. በናይሮቢ የተደረገው ለውጥ ቀደም ሲል በፕሪቶርያ የተድረሰውን ስምምነት የሚያፈ ርስ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት ጉዳዩ በጣም አሳሳቢና የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ሊያሻክር እንደሚችል፡ እንዲያውም አላስፈላጉ ወደ ሆነ ፍጥጫ ሊያመራ እንደሚችል የሚያሳስብ አስቸኳይ መለእክት ለአብይ አህመድ በወቅቱ አድርሷል። ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ኤርትራውያን የአብይ አህመድ እርምጃ በኤርትራ ላይያነጣጠረ የመጀመሪያ የጦርነት ደወል ተብሎ ሊቆጥር ይችላል” የሚ ል አስተያየት ሰጥተውበት ነበር።የፕረቶርያው ስምምነት ከተፈረመ ከ15 ወራት በላይ ያሳቆጠረ ቢሆንም ወያኔ እስከአሁን ትጥቅ አልፈታም፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ ወያኔ 270,000 ያህል ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቁ (ከባድ መስርያ ጭምር) እንዳላው በቅርቡ ደረቱን ነፍቶ ይፋ አድርጓል፡: ወ ያኔ ለሚፈጥረው ውጥረት ይሁን እልቂት ዋናው ተጠያቂ አብይ አህመድ ለመሆኑ ምንም አያጠያ ይቅም።

አራተኛ ስህተት፡ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለውየፌደራል ሰራዊትን ከመሸነፍ ያዳኑትን አ ጋሮችጥቅም ማገለሉ !

 1. የኢትዮጲያ ፌዴራል ሰራዊት አጋር በመሆን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ የወያኔን ከንቱ ህልም የማክሸፍ ወሳኝ ድርሻ የነበራቸው የኤርትራና የአማራ ልዩ ሃይል/ፋኖዎች መሰረታዊ ጥያቄዎችን ያልመለሰ በመሆኑ፡ የፕሪቶርያ ስምምነት አብይ አህመድ በአጋሮቹ ላይ የፈጸመው ትልቅ ክህደት ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል። ስምምነቱ ገና በትኩሱ እያለ በአማራ ክልል ከፈተኛ ህዝባዊ ድገፍ ያለው ትግል እንዲፋፋም መንስኤ የሆነው በዋናነት የፕሪቶርያው ስምምነት ይስከተለው መዘዝ ነው። የኖቤል ሰላም ተሸላሚው አብይ አህመድ የአማራ ህዝብን ጥያቄ በአግባብ ከመመለስ ይልቅ በጉልበት ለማንበርክክ እስከ ድሮንና ከባድ መሳርያ መጠቀም አስገድዶታል።የህዝብን ጥያቄ በጦር መሳርያ ሃይል ለመደፍጠጥ የብዙ ንጹሃን ዜጎች ህይወት መቀጥፍ ደንታ የሌለው ጦረኛው አብይ አህመድ አንዴት የኖቤል ሰላም ሽልማት ሊሰጠው ቻለ የሚል ጥያቄ ማቅረቡ ተገቢ ነው።
 2. የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አባላት አብይ አህመድ በተሸለመበት የሰላም ስብእና መሰረቶች ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ በጦር መሳርያ ለዚያውም የገዛ ህዝቡን በመጨፍ ጨፍና በማፈናቀል በሃይል ለመፍታት በተደጋጋሚ ያደረጋቸውን እርምጃዎች ሲመለከቱ፡ የአብይ ጦረኝነት ከድርጀቱ መሰረታው አላማዎች ጋር የሚጋጭ መሆኑን ሲያጤኑ ከ4 ዓመት በፊት ለፈጸ ሙት ስህተት መጸጸት ግድ ይላቸዋል። የኔቤል ፋውንዴሽ ህግጋት የስላም ሽልማቱ አንዴ ከተሰጠ በኋላ መሻርና መቀማትን አልያም ዳግመ ግምት ላማድረግ የሚያስችል እድል መኖሩን ስለማይጠቅስ የሚቻል አይመስለኝም። ህጉ የሚፈቅድ ቢሆን ኖሮ ግን የኖቤልን ስም ከማጠልሸት ለመታደግ ሲባል አብይ አህመድ ሽልማቱን እንዲመልስ ማድረጉን የሚመርጡ ይመስለኛል።
 3. ከፈተኛ መስዋዕት ከፍሎ የኢትዮጵያ ሰራዊት በወያኔ ከመሸነፍ ያዳነው የኤርትራ ሰራዊት መሆኑ እየታወቀ፡ የፕሪቶርያ ስምምነት የኤርትራን የደህንነት ስጋት ይሁን የወያኔን የጦርነት ትንኮሳ ግምት ውስጥ ያላስገባ ብቻ ሳይሆን ባለውለተኛዎቹን አሳልፎ የሰጠ ክህደት ነው ተብሎ መጠቅስ ይቻላል። ይህ ድርጊት ኤርትራ አብይ አህመድ ላይ የነበራትን አመኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባ የመጀመረያ አመላካች ነጥብ ነበር ማለት ይቻላል። ሌላው የፕሪቶርያ መዘዝ ደግሞ፡ ሁለቱ መንግስታት የሰላምና ጸጥታ ትብብር ላማድረግና ለጋራ ልማትና ብልጽግና በጋራ ለመስራት በ 2018 ዓ.ም. በአስመራ የተፈራረሙትን ታሪካው የሰላምና ወዳጅነት ስምምነት የጣሰ በመሆኑ ነው። ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበት የነበረና ወዳጅን አስደስቶ ጠላትን አብግኖ በጥሩ ሁኔታ ወደፊት በመቀጠል ላይ የነበረው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት፡ ባልተጠበቀ ፍጥነት ለመሻከሩና በቀጠናው ከፍተኛ ውጥረት ለመስፈኑ ተጠያቂው ተንኳሹና አርቆ ማሰብ የጎደለው ችኩል የአብይ አህመድ እርምጃ መሆኑን መገንዘብያስፈልጋል።

በአብይ አህመድ በኩል ወያኔ በትግራይ ሙሉ ስልጣን ይዞ እንዲቀጥል ለምን ተፈለገ ?

 1. የፕሪቶርያ ስምምነት ባስቀመጠው የ30 ቀን ጊዜ ገደብ መሰረት፡ ወይኔ ትጥቅ እንዲፈ ታ ያልተደረገበት ድብቅ አጀንዳ ይኖር ይሆን የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ የማይቀር ነው።ስምምነቱ በተፈረመ ባጭር ጊዜ ውስጥ፡ የብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለቀጠፈው ጦርነት ዋነኛው ተጠያቂዎች የወያኔ ጦር አዛዦች መሆናቸው በግልጽ እያወቀ፡ የብልጽግናው መሪ እነዚህን የጦር ወንጀለኞች ጋብዞ በአዲስ አበባ ትልቅ ድግስ በማዘጋጀት (የውጭ አገር ዲፕሎማትን ጋብዞ በቀጥታ በቴሌቢዥን በማሰራጨት) ዕውቅና መስጠቱ ለምን አስፈለገ ? ነው ውይስ እሰየው !እንኳን ሰራዊታችንን ድንገት በውድቅት ጨለማ ጨፈጨፋችሁልን! ብሎ ለማመስገን ይሆን ? ዕውቅናና ሽልማት መሰጠት ካስፈለገም ለኢትዮጵያ ለአላዊነት መከበር ከፍተኛ ዋጋ ለከፈሉትና ፌደራል ስርአቱን ከውድቀት አፋፍ ለታደጉት አጋሮቹ ለአማራ ልዩ ሃይል/ፋኖዎች፡ ለአፋሮችና ለኤርትራ ጦር አዛዦች መሆን በተገባ ነበር።
 2. አብይ አህመድ ወያኔ የጦር መሳርያ እንዳይፈታ የፈለገበት ዋናው ምክንያት፥ በወቅቱ ዋናው አጋሮች ከነበሩት ከኤርትራና ከአማራው ፋኖዎች ጋር ሊከፍተው ላቀደው ጦርነት የወያኔን ሃይል ከጎኑ ለማሰለፍ ያሰበው አርቆ አሳቢነት የጎደለው ጅላጅል ፍላጎት ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች አሉ። ፕሮፌሰር እዝክየል ጋቢሳ ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሳ፡ “ከ6 ወር በፊት ጀምሮ ጠ/ሚሩ ከትግራይ መሪዎች ጋር ባደረጉት ምክክር የኤርትራን መንግስት ለማስወገድ እንደሚፈልጉና አሁን ይህንኑ ለመተግበር የተነሳሱት አሁን ጊዜው የተመቻቸ ነው ብለው ስላሰቡ ነው የምል እምነት ነው ያለኝ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
 3. ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የውስጥ ምንጮች እንዳጋለጡት፡ አብይ አህመድ ከጀነራል ጻድቃንና ጀነራል ታደሰ ወረደ ጋር ባደረገው የ4 ኪሎ ምክክር ፡”ስለ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት ህጋዊ መብት ጉዳይ አንስቶ፡ ጀነራል ጻድቅንን የባህር በር ስለማግኝቱ ጉድይ ቀድም ሲል የሚደነቅ ጽሁፍ ማቅረቡንና ያለው አቋሙን ካደነቀ በኃላ ፡ ይህን የሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የረጅም ጊዜ ህልም የሆነውን የባህር በር ጉዳይ ተግባራዊ የምናደርግበት አጋጣሚ ተፈጥሯል። ከሻዕብያ ጋር ላቀድነው ፍልሚያ የአንተና የትግራይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ትብብር ወሳኝ ነው ! በማለት በሙሉ ጀነራልነት ማዕረግ የታሰበውን “የቀይ ባህር ዘመቻ” እንዲመራ ጥሪ እንዳቀረበለትና ጀነራሉም በመደሰት፡ የምደግፈው ሃሳብ መሆኑን ገልጾ፡ ከጓዶቹ ጋር እንደሚማከርበት መልስ መስጠቱን” አጋልጠዋል።
 4. ጀነራል ጻድቃን በኤርትራ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥላቻ የአደባብይ ሚስጥር ነው። ተማሪ በነበረበት ጊዜ “ኤርትራውያን እኛ ተጋሩን ይንቃሉ፡አያስጠጉንም” በማለት ከፍተኛ የ በታችነት ስሜትያንጻባርቅ እንደነበረ አብረውት በ4 ኪሎ የሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የነበሩ ኤርትራውያን ያወሳሉ።ከ1998-2000 ዓ.ም. በተካሄደው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትም የወያኔ ሰራዊት ዋናው አዛዥ ሆኖ በጾረናና በአሰብ ግንባሮች ለደረሰባቸው ከፍተኛ ሽንፈት ዋናው ተጠያቂ እሱ በመሆኑ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ከስልጣኑ እንዳባረረው ማስታወስ ተገቢ ይመስለኛል።ስለዚህ ጀነራሉ ለብዙ ዓመታት ሲያሰቃየው ከኖረው በሽንፈቱ የመሰቃየት መንፈስ ለመላቀቅ የአብይን ጥሪ ተቀብሎ ኤርትራን ለመበቀል መፈልጉ የሚገርም አይድለም። የሚገርመው የራሱን ልጆች በከፈተኛ ወጪ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አስተምሮ ያስመረቀ፤ቤተሰቡን ውድና ግዙፍ ያማረ መኖርያ ቤት በመግዛት እዚያው አሜሪካ ውስጥ አንደላቆ እያኖረ፡ በኤርትራውያን ላይ ያለውን የግል ቁጭት ለመወጣት ሲል የትግራይን ወጣት ህይወት ጭዳ በማድረግ አላስፈላጊ ጦርነት ውስጥ ማግዶ ማስጨረስ ጭራሽ ሃላፊነት የጎደለው ሰይጣናዊ ተግባር ነው።

በእርግጥ ኤርትራ ላይ ጦርነት ለመጫር ወይንስ የህዝብ ጥያቄዎችን መመለስ ስላቃተው አቅጣጫ የመለወጫ ዘዴ ?

18 ከአሁን በኋላ በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ምን ሊፈጠር እንደሚቻል መተንበይ ባይቻልም ፡ ከጥቂት አመታት በፊት ወደነበረው መተማመን ወደሰፈነበት ግንኙነት መመለስ እንደማይቻል በርግጠኝነት መናገር ይቻላል። በቅርቡ የአብይ አህመድ፡ “የቀይ ባህር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ ነው ! ኢትዮጵያ ያለ ወደብ ልትኖር አትችልም! የኢትዮጲያ ታሪካዊ ድ! ንከበ1ር0ቀ0ይሚባልህዮር ንነበህርዝብ የባህር በርማግኘት ግድ ይላል፡ ከተቻለ በሰላም ካልሆነ ግንበሃይል ጭ ምር ማረጋገጥ ይኖርብናል” ሲል ያሰማው ዛቻና ፉከራ አዘል ንግግር በግልጽ ያነጣጠረው ኤርትራ ላይ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህ አሁን የተፈለገው በእርግጥ በኤርትራ ላይ ጦርነት መክፈት ነው? “ አሳ ፈላጊ ዘንዶ ያወጣል ! የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል” የሚለውን እንዳያስከትል!! ወይንስ ህዝቡ ያነሳቸውን አንገብጋቢና ፈታኝ ጥያቄዎች መመለስ ስላልቻለ የባህር በር ጥያቄ በማንሳት የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለመጠምዘዝ የተፈረበከ ጊዜ-መግዣ ስልት? እነዚህ የተጠቀሱት ሁለቱም የሱ አማራጭች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት በኤርትራ በኩል በቂ ጥንቃቄእ ንደሚደረግበትና ትኩረት እንደሚሰጠው ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

 1. ከፋኖዎችና ከሸኔዎች ጋር የተፋፋመ ጦርነት እያካሄደ ባለበት፡ ማለትም ድሮኖችንና ከባድ መሳርያውችን ጭምር ተጠቅሞ ሊያንበረክካቸው ባልቻለበት፡ 270,000 ብዛት ያለው ሰራዊት አለን የተባለለት ግዙፉ የወያኔ ሰራዊት የጦር መሳርያ ባልፈታበት፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎ ች በከፍተኛ ርሃብና የኑሮ ውድነት በሚሰቃዩበት፡ የፌደራል መንግስት ከሶማልያ ጋር የፈጠረው ውጥረት በተጠናከረበት ተጨባጭ ሁኔታ ስር፡ በእውነት አብይ አህመድ ከኤርትራ ጋር ጦርነት መጫር ያምረው ይሆን የሚል ጥያቄ ማንሳት ብልህነት ነው። አብይ አህመድ ከወያኔና ከዚያም በፊት ከነበሩት የኢትዮጵያ መሪዎች ካጋጠማቸው አሳፋሪ ሽንፈት ተመክሮ ስለቀሰመ ከኤርትራ ጋር ጦርነት መሞከር ከፈተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ጠንቅቆ ያውቃል።
 2. አሳዛኙና አነጋጋሪው ክስተት ግን፡ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረሃብና በኑሮ ውድነት እየተሰቃዩና ከመንደራቸው ተፈናቅለው እይተንገላቱ፡ በአማራና ኦርሚያ የተከሰተው ደም አፋሳሽ ጦርነት በተፋፋመበት ሁኔታ፡ የእነዚህን ዜጎችን ጥያቄ ቅድሚያ ሰጥቶ ከመመልስ ይልቅ፡የኖቤል ሰላም ተሸላሚው ሰላምን አሽቀንጥሮ በመግፋት ቅድሚያ የሰጠው ለተራበው ህዝብ ጉርሻ ዳቦ የማያጎርሱ ብልጭልጭ ፕሮጀክቶች ላይ ነው፡፡በ10 ቢልዮን ብር ወጪ የአጼ ሃይለስላሴ ቤተመንግስት ማሳደስና አዳዲስ መናፈሻ ፓርኮችንመገንባት፡ የውጭ አገር መሪዎ ችን በመጋበዝ ትልቅ ድግስ ደገሶ ዳንኪራ መርገጥን ነው ቅድሚያ የሰጠው።
 3. አጼ ሃይለስላሴም የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የወሎ ህዝብ በርሃብ እንደ ቅጠል ይረግፍበነ በረበት ጊዜ የ80 ዓመት የልደት ብዓላቸውን ሲያከብሩ ብዛት ያላቸው የውጭ አገራት መሪዎች ታላላቅና ዝነኛ ሰዎች ታዳሚያን የሆኑበት፡ ከውጭ አገር በአይሮፕላን ተጭኖ የመጣ ኬክ የተቆረ ሰበት፡ በዊስኪ የተራጩበት፡ እንደነበር ልብ ይለዋል። ይሄው ታሪክ ራሱን ሲደግም የብልጽግናው ሰው ህዝቡን ከረሃብ ከማላቀቅ ይልቅ ቤተ መንግስት ማደስና ፓርኮችንመገንባት የመረጠው መራ ተብሎለታል። በታሪክም በዚሁ ስራው እየታሰበ ይኖራል።

የፕሪቶሪያን ስምምነት እና ውጤቶቹን ለመገምገምየተጠራ ስብሰባ

 1. የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለመገምገም በአፍሪካህብረት የተጠራው ስብሰባ፡ በኢትዮጵ ያ የፌዴራል መንግስትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች መካከል ሸምጋዮች እና ታዛቢዎች በተገኙበት መጋቢት 11 2024 በአዲስአበባ ተካሄደ። በግምገማው ብዙ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ፣ በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ በግልጽ የተቀመጠው ነገር ግን ከአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ በላይ እስካሁን ያልተፈጸመው የህወሓት የትጥቅ መፍታት ጉዳይ ነበር።
 2. ህወሓት እስከ አሁን በኤርትራ እና በአማራ ክልል ቁጥጥር ስር ተይዘዋብኛል የምትላቸው ቦታዎች ወደ ትግራይ ካልተመለሱ ሰራዊቷ ትጥቅ እንደማይፈታን ወደ ህብረተ ሰቡ እንደማይቀላቀል ደጋግማ አስተውቃልች። ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም፣ የኤርትራ ጦር በአልጀርስ በተደረሰው ስምምነትና በሄግ ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት የተደነገገው መሬት ላይ ነው ያለው የሚል ግልጽ አቋሙን አሳውቋል። የኤርትራ መንግስትም ለንደን ታላቋ ብሪትንያ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል የኤርትራ ጦር የሚገኘው በኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል።
 3. ህወሓት በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረውን የድንበር ጉዳይ በሄግ ኔዘርላንድስ በሚገኘው የአለም ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በደጋፊውቹ ድጋፍና በራሱ እምቢተኝነት ውሳኔውን ሳይቀበል ከሃያ ዓመታት በላይ አሻፈረኝ እንዳላለ፡ አሁን ያለምንም ሃፍረት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር በየቀኑ መወተወቱና መለመኑ የወያኔና ድርብ መለኪያ እና ግብዝነት ባህርይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ድርጊት ነው። ባድመ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት ተበሎ በይፋ ከታወቀ ከጥቂትሳ ምንታት በኋላ ዝነኛው ኤርትራዊው አርቲስት በረከት መንግስተአብ ለወያኔ የዘፈነላትን ዘፈነ አስታወስኩኝ። ዜማው”ማሌሊት ለኤርትራ ብለሽ የጠመቅሽው እሬት፣ አሁን ሓቁስ ለታወቀ ያለ ማንገራገር መራራውን እሬትሽን ራስሽ ተጎንጭው/ጠጭው የሚል ነበር፡፡ ወያኔ ያለው ብቸኛው አማራጭ “የመጨረሻና ይግባኝ የሌለው ውሳኔን በውል መቀብል ብቻ ነው ።
 4. የወልቃይት እና የራያ የይገባኛል ጥያቄ በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል ከፍተኛ ውጥረት አስከተሏል።ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በተለያዩ የራያ ወረዳዎች በሁለቱ ወገኖች መካከል የማያቋርጥ የተኩስ ልውውጥ መደረጋቸው ታውቋል። ስለዚሁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት እንዲሁም በአማራና በትግራይ ክልል አስተዳደሮች የሚሰጡ መግለጫዎች: በመካከላቸው መተማመን ማጣት, እና ከባድ ፍርሃት እና ውጥረት መኖሩን ያመለክታል። በፕሪቶሪያ ስምምነት በግልፅ እንደተገለጸው (አንቀጽ 10፡4) በሁለቱወገኖች መካከል አለመግባባት የተፈጠረባቸው ቦታዎች በፌዴራል ሕገ መንግሥት መሠረት ዘላቂ መፍትሔ ይደረግላቸዋል ይላል። ይህን አመልክቶ የትግራይ ክልል ፕርስደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት፡ በኢት ዮጵያ ሆነ በሁለቱም ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ከተፈለገ የፌደራል ህገ-መንግስት በሚፈቅደው መሰረት የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ማለቱ ይታወ ቃል።
 5. በአብይ አህመድ በኩል ከፕሪቶሪያ ስምምነት በማፈንገጥ የተለየ አዲስ አቋም ወስዷል። ከፌደራል መንግስትና ከሁለቱ ክልሎች በተወጣጡ ከፍተኛ ተወካዮች ያካተተ ኮሚቴ ተቋቋሙ በውውይትና “ሰጥቶ መቀበል” በሚል መርህ ጉዳዩን ለመፍታት እቅድ አውጥቷል። በመእሰቅረዱት በቅድሚያ ፈቃደኛ የሆኑ ተፈናቃዮችከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ቦታቸው የመለሳሉ። ከዚያም በቦታው ላይ ያለው ሁኔታ ተገምግሞ፡ ሁኔታውና ጊዜው ሲፈቅድ (የጊዜ ገደብ አላስቀ መጠም) የአካባቢው ሰዎች የራስን ዕድል በራስ መወሰን.መርህ በመከተል (በህዝብ ውሳኔ ማለት ነው) የወልቃይት እና የራያን ጉዳይ በዘላቂነት ይፈታል ተብሏል። ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቁ ወገኖች እቅዱ ውጥረቶችን ከማባባስ እና ከማወሳሰብ በስተቀር ሰላምና መረጋግት ሊያመጣ የሚችል አይመስልንም የሚል አስተያየት ስጥተዋል።
 6. የወልቃይትና የራይ ጉዳይ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሕገመንግሥት መሠረት ዘላቂ መፍትሄ ይ ገኝበታል የሚል ተስፋ ነበር። ሆኖም አብይ አህመድ በወሰደው ከፕሪቶርያ ስምምነት ውጪ የአሆዲነስ አቋም የተነሳ ወያኔ ከዚህ በፊት የያዘውንወልቃይትና ራያ በፌደራል ህገ መንግስት መሰ ረት ወደ ትግራይ ካልተመለሱ ትጥቅ አላወርድም ሰራዊቴንም አላሰናብትም የሚለውን አቋሙን ከቀጠለችበትና የአብይ የአብይን ውሳኔ መቋቋም የሚያስችል ቁመና አልኝ የምትል ከሆነ ግን በ አብይ አህመድ ተለዋዋጭ ባህርይ ሰበብ በፌደራል መንግስት/በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል መካከል በድጋሚ አላስፈላጊ አውዳሚ ጦርነት ሊያስከትል ይችላል። በጦርነቱም የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦች ከፍተኛ የህይወት ዋጋ ይከፍላሉ የሚል ትልቅ ስጋት አሳድሯል።

ቸር ይግጠመን !

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here