spot_img
Thursday, July 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትሰባተኛው ንጉስ "ፍጻሜ መንግሥት"

ሰባተኛው ንጉስ “ፍጻሜ መንግሥት”

በእስያኤል ዘ ኢትኤል
ሰኔ 26/2016 ዓ.ም.

ቀዳማዊ ተክለ ጊዮርጊስ እ.ኢ.እ 1779 እስከ 1800 ባለው ጊዜ ውስጥ ከነገሱ የሰለሞን ሥርወ-መንግስት ከሆኑት የኢትዮጵያ ነገስታት ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ብዛት ላለው ጊዜ ከስልጣኑ የተገለበጠ ሲሆን ስድስት ጊዜ ስልጣን ላይ ወጥቷል፡፡ በ1779-1784፣ 1788-1789፣ 1794-1795፣ 1795-1796 እና 1798-1799፣ እንዲሁም ከመጋቢት 24 ቀን 1800 እስከ ሰኔ ወር ድረስ በንጉሠ ነገሥትነት አገልግለዋል። እንደ ስቬን ሩበንሰን አገላለጽ፣ ተክለ ጊዮርጊስ ሥልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ የተጠቀሙበት የመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት ስለነበሩ በኢትዮጵያውያን ትውፊት “ፍጻሜ መንግሥት” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶት ነበር። ንጉሠ ነገሥቱ ገና ከጅምሩ ስርወመንግስታቸው አልተወደደላቸውም ነበር፡፡

ስለንጉሱ የተለያዩ ጽሐፍት የተለያዩ ነገሮችን የሚሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ እንግሊዛዊው  ጸሐፊ ፒርስ ገለጻውን የሚያስቀድመው የንጉሠ ነገሥቱን ባህሪ በመጥቀስ ሲሆን እንዲህም በማለት ስለባህሪያቸው ይደመድማል፡- “በግልጽ ቋንቋ እርሱ ለመግለጽ ታላቅ ውሸታም እና መጥፎ ሰው ነው፤  ከልጅነቱ ጀምሮ ተለዋዋጭ ባህሪ ያለው ፣ ቁጡ ፣ አታላይና ቃሉን የማይጠብቅ ሰው ነው” በማለት ይገልጸዋል፡፡ 

ይህንን ታሪክ ለማንሳት ያስገደደኝ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሁኔታ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ላለፊት ሦስት አስርት ዓመታት ቋንቋን መስረት ባደረገና ዲሞክራሳዊ ባልሆነ የፌደራል ስርዓት ውስጥ ችግሮችን ከቀላሉ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ የማዕከላዊ ስልጠኑን እራሱን የኢህአዴግ በማለት የሚጠራው ፖርቲ በበላይነትና በብቸኝነት ሀገሪቷን ሲዘውራት ቆይቶ እስካሁን ያለንበት ደረጃ እንድንደርስ አድርጎናል፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ኢህአዴግ እውነተኛ የፌደራልዝምን ስርዓትን አላመጣም፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አምጥቷል፣ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶችን ይረግጣል፣ የፀጥታ ተቋማቱ በአንድ ብሄረሰብና በአንድ ፖርቲ የበላይነት የተያዘ ነው፣ ከአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውጭ ያሉትን ፖርቲዎችን አጋር ተብለው ድምጻቸውና ውክልናቸው ዝቅተኛ ነበር፤ የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ሲነሱበት የነበረ ፖርቲ ነበር፡፡ 

በመጋቢት 25፣ 2010 ወደ ስልጣን የወጣው በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አሊ የሚመራው የኢህአዴግ ፖርቲ የነበረውን ህወሀት ፖርቲን በማግለል እራሱን የብልጽግና ፖርቲ በማለት ኢህአዴግ ብሎ የሞላውን አባል ኦሪኔል ብልጽግና በማለት እንዲሁም የአዲሱን የፖርቲውን ስያሜ አልቀበል ያለውን በማባረር፣በመፈረጅና በማሰር ተበላሽቶ የነበረውን የኢህአዴግ አሰራር በከፋ ሁኔታ በማበላሸት ሀገሪቷን መስቀለኝ መንገድ ላይ አድርሰዋታል፤በዚህም ሀገሪቷን በምትፈርስና በተዳከመ ሀገር መካከል እንድትገኝ አድርጓታል፡፡ 

ሰባተኛው ንጉሱ

አብይ አህመድ የተወለዱት በጅማ ዞን በትንሿ በሻሻ ከተማ ነው። ሟች እናታቸው ወይዘሮ ትዘታ ወልዴ 7ኛው የኢትዮጵያ ንጉስ አንተ ነህ` አለቺኝ ሲሉ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ሲናገሩ ይሰማ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መሪ እንደሚሆኑ ያወቁት ገና በልጅነታቸው እንደነበር ለመንግስት ከፍተኛ ባለስልለጣናት  በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ፣ም ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው መድረክ ላይ እንዲህ ሲሉ ስለልጅነት ህልማቸው ተናግረዋል፤


“ባለፉት ጊዜያቶች ከሰዓት ጋር እንድሮጥ እንድቸገር ካደረጉኝ ሁሉ በሳባት ዓመቴ እናቴ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ አንተነህ አለቺኝ። የማነበው፣ የምሮጠው፣ ምናምን የምለው ንግስና ይመጣል በሚል ሂሳብ ነው። ለምሳሌ የዛሬ 20 ዓመት በወታደር ቤት ውስጥ የምተዋወቃቸው ሰዎች ፎቶ አብሬ ከተነሳሁ ንጉስ ስሆን አብረን ነበርን እያልክ ታሳያለህ በማለት ፎቶ አብሪያቸው አልነሳም ነበር። ባድመ ከሳሞራ ጋር አብረን ስለ ነበርን ንጉስ ስሆን እንዲህ ትሆናለህ እለው ነበር። ለመለስም ነግሬዋለሁ። መጀመሪያ እኔ ስናገር ሰው ይስቅ ነበር። ነገር ግን ቀስ በቀስ ስራ አስፈጻሚ መሆን ስጀምር ‘እንዴ ይሄ ሰውየ!’ ማለት ተጀመረ። መጀመሪያ ቀልድ ስለሚመስለው ሰው ብዙ አይቀየመኝም ነበር፡፡ ብዙ አላፍርም ዝም ብዬ እናገራለሁ። ርዋንዳ እያለን በጣም ጩጬ ነበርኩ፤ አንዲት ፈረንሳዊት ሴት ትወደኝና ልጅ ስለሆንኩ ‘ወደ ፈረንሳይ ይዤህ ልጥፋ?’ አለቺኝ፤ ‘እንዴት እኔ ንጉስ የምሆን ሰውይ እንዲህ ትለኛለች?’ በማለት አለቀስኩ። ያኔ ፍራቻ አልነበረም በኋላ በኋላ ላይ ወደ ከፍተኛ አመራርነት ስመጣ ግን ‘ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ይፈልጋል’ የሚሉና መሰል ዱላዎች ሲበዙ መደበቅ ጀመርኩ። ግን ውስጣችሁ ያለን ነገር አትደብቁ፤ ስሩበት፤ ስትሰሩበት ለሆነ ክብር ምናምን ሳይሆን ለሚሳካ ህልም ይሁን” የሚሉና መሰል ዱላዎች ሲበዙ መደበቅ ጀመርኩ። ግን ውስጣችሁ ያለን ነገር አትደብቁ፤ ስሩበት፤ ስትሰሩበት ለሆነ ክብር ምናምን ሳይሆን ለሚሳካ ህልም ይሁን” የሚል ንግግር ሲያደርጉ ቪዲዩ አሁን ድረስ ዩቱዩብ ላይ ተጭኖ አለ፡፡ እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ ንግርት አለኝ እነግሳለሁ ያሉት ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ንግስናውን ይህንን ያህል ምን ሊሰሩበት ፈለጉት? ኢህአዴግ ቤት የቆዩበትን ጊዜ ሁሉ እንዴት በማስመሰል ማለፊ ቻሉ? የሚሉትና ሌሎች ጥያቄዎችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

ጠቅላዩ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ከልጅነት ጊዜ የሚመኙትን ንግስና ለማሳካት የተለያዩ ጥረቶችን አድርዋል፡፡ የመጀመሪያው ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ እንደሚባለው ሁሉ በሀገሪቷ ላይ ትልቁን ስልጣን የያዘውን የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት በይፋ እኔን ልትጠይቁኝ አትችሉም፣ በሀገር ውስጥ ለተደረጉ ግድያዎችና መፈናቀሎች እንደ ዘመነ መሳፍንት ሀላፊነትና ተጠያቂ አካል የላቸውም፣ ጠቅላዩም ወንበራቸው/ንግስናቸውን የሚነካባቸውን እያጠፊና የሚያጸናላቸውን እየሸለሙና ጉርሻ እየሰጡ እስከሁን ድረስ አድርሰውናል፣ደርሰዋልም፡፡ ጠቅላዩ ለንግስና ንግርት አለኝ ሲሉ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ነግሰው ስያረጁ ለልጆቻቸው ንግስናቸውን አስተላልፈው ሊሞቱ በምንም ምክንያት ግን ስልጣናቸውን ለአምስት አመት የስልጣን ጊዜ ገደብ እንዳልመጡና አሁን ያለውን የፌደራል ስርዓት እሳቸው ለሚያስቡት የንግስና ፍላጎት ስለማይሆናቸው አዲስ ስርዓትንና ለመንበራቸው መቀመጫ እንዲሆናቸው በ10 ቢሊዩን ዶላር አዲስ ቤተመንግስት ህዝብ እየተራበና በተቸገረበት ጊዜ የሀገሪቷን በጀት የሚበልጥ ገንዘብ መድበው እየሰሩ ይገኛል፡፡ 

ጠቅላዩ በነገሱበት ላለፊት ስድስት አመታቶች ቁጥራችው 21.4 ሚሊዩን በላይ የሆኑ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ መሆናቸው፣በትግራይ ጦርነት ከ1 ሚሊዩን በላይ ዜጎች መሞታቸው፣ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል 2.3 ሚሊዩን እና በሀገር ደረጃ 3.6 ሚሊዩን ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ መሆናቸው፣4.2 ሚሊዩን ዜጎች የዘር ግንዳቸው ተመዞና በጦርነት ምክንያት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዬች በየድንኳኑና ሜዳ ላይ መውደቃቸው(ማስታወስ የሚገባው በሀገሪቷ ላይ ባለው ግጭት ምክንያት ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል)፣አማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ጦርነት ውስጥ መሆኑ፣ በኦሮሚያ በተለይም በወለጋ፣ጉጂና በሸዋ ጦርነት ውስጥ መሆናቸው፣ አፋርና ሱማሌ የቀለጠ ጦርነት ላይ መሆናቸው፣ የጋምቤላ ህዝብ በውጭ በመጡ ሃይላት ጥቃት እየተፈጸመባቸው ያለተከላካይ ጉዳት ወስጥ መሆናቸውና በተደጋጋሚ ደግሞ የዘር ግጭት ውስጥ መሆናቸው፣ትግራይ ሙሉ ለሙሉ ከማዕከላዊ መንግስት ውጭ መሆኗ፣ የሀገሪቷ የነበራት አለምአቀፍና የዲፕሎማሲ ግንኘነት ሙሉ ለሙሉ የተበላሸ ሲሆን ደረጃ ቢሰጠው ዜሮ የሆነበት ጊዜ ላይ መገኘቱ፤ በስድስት አመት ውስጥ በጥቂቱ ንጉሱ ስልጣን ከያዙ በኋላ ሀገሪቷ ሲዖል አድርገዋታል፡፡ እናታቸው 7ኛው ንጉስ እንደሚሆኑ ሲተነብዩ የቱኛው የንጉስ አይነት እንደሚሆኑ ግን አልነገሯቸውም፤ እንደሚመስለኝ ልክ እንደ ቀዳማዊ ተክለ ጊዮርጊስ ፍጻሜ መንግስት ሊሆን እንደሚችል በተግባራ እያየነው መጥተናል፡፡ በዚህም በቀጣይ ወደ ዘመነ መሳፍንት ወይም በአሁኑ ዘመን ነባራዊ ሁኔታ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እያስገባን እንደሆነ ምስክር የማይፈልግ የአደባባይ ምስጥር ነው፡፡ 

የ7ኛው ንጉስ ባህሪ

በባህሪ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምናይበት ጊዜ ኢህአዴግ ቤት የቆዩበትን ጊዜ ሁሉ እንዴት በማስመሰል ማለፊ ቻሉ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ ነው፡፡ ላለፊት ስድስት አመታቶች አብይ አህመድ የሚባል ስም ሲጠራ በብዙ ዜጎች አዕምሮ ውስጥ የሚመጣው የመካድ ስሜት ወይም “ከሀዲ” የሚል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡  አብይ ሁሉንም ዜጎች ክደዋል፣ያሉትን አንድም ነገር መፈጸም አልቻሉም፤ ይባስ ብለው ክፋትና ጥላቻን ዘርተዋል፣ ሀገሪቷን ህይወት እንደዋዛ አድርገዋታል፣ ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነባት ሀገር አድርገዋታል፡፡ የጠቅላዩ ባህሪ ልክ እንደ አምሳያ ንጉሳቸው ቀዳማዊ ተክለ ጊዮርጊስ እንደ እንግሊዛዊ ጽሐፍ አገላለጽ “ታላቅ ውሸታም እና መጥፎ ሰው ነው፤  ከልጅነቱ ጀምሮ  ተለዋዋጭ ባህሪ ያለው ፣ቁጡ፣ አታላይና ቃሉን የማይጠብቅ ሰው ነው” እንዳለው አብይም የእነዚህ ባህሪዎች ባለቤት ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜቶች በሚያሳየው ባህሪያትና ምልክቶችን በማንሳት ጠቅላዩ የአዕምሮ ችግር ወይም የስነ-ልቦና ችግር እንዳለባቸው መላ ምታቸውን ሲያስቀምጡ ሰዎች በዝተዋል፡፡ በተለይም በተደጋጋሚ ከሚታይባቸው እራሳቸውን አብዝቶ የመውደድ ባህሪ በመነሳት በራስ ፍቅር የወደቁ(narcissist) ሰው ናቸው ይላሉ፤ለዚህም እንደማሳያ ከልክ ያለፈ ስለራሳቸው አስፈላጊነት ማውራታቸው፤ ለምሳሌ አሻግራችኋለው፣እኔ ከሌለው ሀገር አይኖርም፣እኔ ጅቡቲ ስመጣ ዝናብ ዘነበ፣አለም ከእኛ ልምድ ካልወሰድኩ እያለ ነው፣ብዙ ሀገራት የአብረን እንስራ ከእናንተ እንማር እያሉን ነው፤በየትኛውም አጋጣሚ የትኩረት ማዕከል የመሆን ባህሪያቸው የሚሉና ሌሎች ከእውነታ የራቁ ንግግሮችንና በየጊዜው የራሳቸውን ፎቶና ቪዲዩ በመልቀቅና በብዛት ስለእራሱ እንዲወራ በማድረግና በማውራት የሚታዩ ምልክቶችን በመመሪመር የደረሱበት መደምደሚያ ነው፡፡

በተመሳሳይ ከሚያሳዩት ባህሪዎች መካከል ለሰው ህይወትና ለሌሎች በአጠቃላይ ያላቸው ስሜት ምንም መሆኑ ነው፡፡በዚህም ሰውየው ኢጎማኒያክ (egomaniacal) ነው የሚሉት ደግሞ የሰውየውን ባህሪ ያልተለመደ ወይም እጅግ በጣም ራስ ወዳድ እና ለራስ ከፍ ያለ ግምት ያለው ሰው በመሆኑ ሲሆን በተለይም ለሌሎች ሰዎች ህይወት ምንም ሀዘኔታ የማያሳይ በመሆኑ ነው፡፡ በተደጋጋሚ በአካልና በቴልቪዥን ለማየት እንደሚቻው የአብይ የባህሪ ችግር ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ምን አልባት በወታደር ቤት ወይም በሌላ ምክንያት በጭንቅላቱ(አንጎሉ) ላይ የደረሰ ጉዳት አለ በሚሉ ሰዎች የሚነገረው ወደ አናቱ ላይ የመሰንጠቅ የጠባሳ ምልክቱን በማሳየት የጭንቅላት(አንጎል) አደጋ ደርሶበታል የሚታየው የባህሪ ችግር የሚመነጨው በደረሰበት ጉዳት ነው ብለው የሚሞግቱም አሉ፡፡ 

የአንጎል ጉዳት በአብዛኛው ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ ነው፡፡ በትራፊክ አደጋ፣ መውደቅ፣ ጥቃት፣ የአንጎል ዕጢ፣ የልብ ድካም፣ ስትሮክ፣ ደም መፍሰስ፣ የአንጎል ቀዶ ጥገና ወይም ሌሎች የጤና እክሎች ሊከሰት ይችላል። ጉዳቱ የደረሰበት ሰው ከጉዳቱ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ኮማ ውስጥ መሆንን ሊያካትት ይችላል። ጉዳቱ የደረሰበት ሰው አዕምሮ ከዚህ ቀደም የሚያደርጋቸውን ተግባራት በአግባቡ መከወን የሚሳነው ሲሆን  የአዕምሮ ችሎታዎች እና ስብዕናው እንደበፊቱ በትክክል አይሰራም፡፡ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ መለዋወጥ ችግር ውስጥ የሚገባ ሲሆን የአእምሮ ጉዳት ከመድረሱ በፊት እንደታየው የሚታየው ሰው ተመሳሳይ የአእምሮ ችሎታዎች እና የባህርይ መገለጫዎች በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ ላይቀጥል ይችላል፡፡ ጠቅላዩ የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው የሚሉ ናቸው፡፡ 

ጠቅላዩ

7ኛው ንጉሳችን ልክ እንደ ፊጻሜ መንግስት ማዕከላዊ መንግስቱ መዳከም፣ግዛቶችን መቆጣጠር አለመቻሉ፣ የሰልጣናቸው በመዲናዎ ላይ ብቻ በሚባል መልኩ መቅረቱ፣በየአከባቢው አማጽያን ወታደር አሰልጥነውና በአደባባይ ያለማንም ከልካይ ማስመረቅ መቻላቸው የገንቡት የፀጥታ መዋቅር ደካምነት  ማሳያ መሆኑ፣ ጠላቶቻችን ብቻ ሳይሆኑ ተራ የሰፈር ዱሪየዎች የማይፈሩት መንግስት መገንባታቸው፣ ብዙን ተግባራቸው ከህግና ስርዓት ውጭ የሚፈጽሙ ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ በሚል ፈሊጥ ለሚያደርጉት ተግባራቸው በሙሉ ተጠያቂነትና ግልጸኝነት አለመኖር፣ ሀገሪቷን ወደ ውድቀትና እርስ በእርስ ጦርነት መምራታቸው፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የላሸቀበትና ድህነት የተስፋፋበት በዚህም በየቦታው ወንጀል የተባራከተበት መሆኑ፣ ሙስና የተስፋፋበት በጥቅሉ ሀገሪቷን ወደ ውድቀት ያመኗራት 7ኛው ንጉስ “ፍጻሜ መንግስት” መሆናቸውን እንደማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡

በአጠቃላይ ጠቅላዩ ወደ ስልጣን የመጡት ለመንገስ እንጂ ያገኙትን ትልቅ የመንግስት ስልጣን ለትልቅ ሀላፊነት ሊያውሉት አይደለም፡፡ በየጊዜው የሚነኳቸው ጉዳዮች ጥንቃቄ የሚሻ ሀገራዊ(ሀይማኖት፣ዘር)፣አህጉራዊ፣ ቀጠናዊ ጉዳዪችን ያለ መውጫ እስትራቴጂ  መሆኑ ሀገሪቷን ከፍተኛ የሆነ አደጋ ጋርጦባታል፡፡ በሀገሪቷ ላይ ተቋማዊነት እንዳይኖር በማደረግ  በተለይም  የመንግስትን የፀጥታ ተቋማትን እንደግል ንብረት  በመቁጠር ለመንበራቸው ማስጠበቂያና የግል ቂማቸን መወጣጫ አድርጓቸዋል፡፡ የዘር ፖለቲካዊን ከምንም ጊዜ በላይ የከፋና ወደ መጨረሻው ደረጃ እየደረሰ ይገኛል፡፡ በፈጸሙት የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ስላወቁ በሀገሪቷ በሁሉም አቅጣጫ ግጭት እየጠመቁ ሀገሪቷ ሰላም እንዳትሆን እያደረጉ ይገኛል፡፡ በሀገሪቷ ላይ የተጋረጠውን አደጋ መቀልበስ የሚቻለው ሀገሪቷ ሳትፈርስና ሳይዘገይ ሀቀኝ የሆነ የሽግግር ፍትህ በማንምጣትና ሀገራዊ ምርጫ እስከሚካሄድ ከተለያዩ አካላት በተለይም ነፍጥ አንግተው እየታገሉ ያሉትን ሃይሎችና በሀገር ወስጥ የሚገኙ የተቋሚ ፖርት፣የሲቪል ማህበረሰቦችና ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የሚሳተፈበትና ከተወጣጡ የሽግግር መንግስት ማቋቋም፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ ብትፈርስ የሚፈጠረውን ቀጠናዊና አለማቀፋው ችግሮችን ከግምት በማስገባት ሀያላን መንግስታትና አለም አቀፍ ድርጅቶች በአፋጣኝ ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ድጋፍና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው ኢትዩጵያዊና ትውልደ ኢትዩጵያዊ የእራሱን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል፡፡ 

ሰላም ለሠው ዘር በሙሉ!

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here