spot_img
Thursday, July 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትበትግራይ እየሆነ ያለው ለምን ሆነ? (ፍረዝጊ የዕብዮ) 

በትግራይ እየሆነ ያለው ለምን ሆነ? (ፍረዝጊ የዕብዮ) 

ትግራይ
ከሌላ ድረ ገጽ የተገኘ

ፍረዝጊ የዕብዮ
አዲስ አበባ

ትግራይ  የሴት እህቶታችን ሲኦል ሆናለች፡፡ በየቀኑ ይደፈራሉ ፣ይገደላሉ እና ይታፈናሉ፡፡ የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማትም  የውግዘት መግለጫዎች ይሰጣሉ በትንሹም ቢሆን  በአደባባይም ጭምር በሰለማዊ ሰልፍ ማውገዝ  ተጀምረዋል፡፡ ሰሞኑ  የመቀሌ ሴቶች ከሽፎን ማህበራቸው ወጥተው በድፍረት  የሴቶችን መገደልና መደፈር አውግዘዋል፣ ተቃውመዋል፡፡  እንደዚህ ዓይነት  ውግዘቶች መበራከታቸው ተስፋ ሰጪ ነው፡፡  

ይሁንና ነገሩ ከሆነ በኋላ ማውገዝ አንድ ነገር ሆኖ ግን ለምን ሆነ ብለን ለመጠየቅ ይገባናል፡፡ መፍትሔው የሚመጣም ከዛ ነው፡፡  እዛ ተገደሉ እዚህ ተደፈሩ ሲባል አደባባይ ወጥቶ መጮህ  መሰረታዊ መፍትሔ የሚያመጣ አይደለም፡፡ እኔም ማትኮር ፈለኩት ለምን ሆነ በሚለው ላይ ነው፡፡ መንስኤው ነው መመርመር የፈለኩት፡፡ መድሃኒቱ ሁሉም ሰው ሊፈልግ ይችላል  ዋናው ግን የበሽታው መንስኤ መመርመርና ማወቅ ከሁሉ ይቀድማል፡፡ 

የሰው ልጅ ከአውሬ እንዲለይ ያደረገው ባህሪ  ከግዜ ብዛት የተማራቸው እና ያከማቻቸው እሴቶች ናቸው፡፡ እሴቶቹ ከሃይማኖት አስተምሮ፣ ከባህል እና ከተለያዩ ትምህርቶች ያገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር የትግራይ ህዝብም ለሰው ልጅ ትልቅ ክብርና ፍቅር የነበረው ሃይማኖት ኣክባሪ፣ስራ ወዳድ፣ሃቀኛና  ተመራማሪ ነበር፡፡ በመሆኑም ለሀገርም ሆነ ለዓለም ብዙ  ቅርሶች፣ ጥበቦች እና ክብሮች  አጋርተዋል ፡፡

ታድያ ለምን አሁን በዚህ ዘመን ልጆቹ አውሬ ሆኑ ካልን ግን ከህወሓት ከጥተኛ የሚያያዝ ጉዳይ ነው፡፡ ህወሓት የፈጠሩ ወጣቶች  አዲስ ዓለም ለመፍጠር ከነበራቸው ጉጉት አንፃር የትግራይ ወጣት ወደ አውሬነት ቀይረውታል፡፡ ከመጀመርያ ጀምሮ እነ መለስ  እና አረጋዊ በርሄ በርሃ እንደወጡ የተጣሉት ከትግራይ እሴት ነው፡፡ በትግራይ አገር ሽማግሌዎች ይሰማሉ ያሉትንም ይደመጣል፣ የሃይማኖት ኣባቶች ተቀባይነት ነበራቸው እነሱ ካሉት ውጪ መሆን አስቸጋር ሆነባቸው  ከአልባንያ ለተፈጠሩ የህወሓት ወጣቶች፡፡

ስለሆነም ታላላቅ ሰዎችን እና ሃይማኖት አባቶችን ማጥፋት ወይም  ኣብያተክርስትያናት ማራከስ የመጀመርያ ዓላማ አድርገው ተንቀሳቀሱ፡፡ የሃይማኖት አባቶች መስለው  በየአብያተእመኖቶች ገቡ ሃይማኖታዊ ስረአት ለ‹ፖለቲካ ኣዋሉት፡፡ ፆም የለም ስግደት የለም፣ ሲከበሩ የነበሩ  ቤተ እምነቶች የካድሬ መሰብሰብያ እና የጥይት ማከማቻ ሆኑ፡፡ ይህንን ሲያዩ የሚያድጉ ወጣቶች  በሃይማኖት ኣባቶች እና በለካድሬዎች  ልዩነት መኖሩን መገንዘብ ኣችሉም፡፡  በኣብያተ እምነቶች የነበረውን ክብር፣ፈርሃ እግዚኣብሄር  ቀስ በቀስ ከትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ አደረጉት፡፡ እነቴ ነው በተለያዩ ገዳማትም ሆነ አብያተከርስትያኖት ሄደን ህዝቡ ነጠላ ለብሶ ኣካሉ ቤተክርስትያን ቢሆንም የሚሰማው ግን ድመፀ ወያነ ነው ፣ ከፊት ለፊቱ ያሉት ቁሶች ቢሆነም የሚያየው ግን እነ ደብረፅዮን ነው፡፡ ስለዚህ አንንኛውን መንሴ ህወሓት ለፖለቲካው ዓላማ ሲል ወጣቶች ሊገራ የሚችል ባህልና እሴት ከትግራይ እንዲጠፋ በማድረጉ ነው፡፡

ሌላው ትልቁ መንሴ ደግሞ  በደደቢትም በቴምቤን በርሃም እያሉ  ሲያከናውኑት የነበረውን ተግባር  ነው፡፡ የድሮ ግዜ እንኳን ትተን የህወሓት አመራሮች  የትግራይ ህዝብ የጠላቸው መሆኑን ሲገነዘቡ፡፡ ድሮ በደደቢት በርሃ እያሉ ሲተገብሩት የነበረውን አውሬነት ባህሪ  እንደገና መተግበር ጀመሩ፡፡ የመከላከያ እና የሸዓብያ ወታደር ልብስ እያለበሱ በግድ ሴት ህቶቶቻችን አስደፍረው፣ ወጣት ወwንደችን አስገድለው በቪድዮ እያሳዩ ህዝቡ እነንዲከተላቸው አድርገዋል፡፡ ለራሳቸው ደህንነት ብቻ በማሰብ  መድፈር፣መግደል እና መስረቅ የታጣቂው  የቀን ተቀን ስራው እና ወጉ እንዲሆን አደረጉ፡፡ መድፈር ለህወሓት ታጣቂዎች እና አመራሮች  ስራቸው ነው ማለት ትችላለህ፡፡ ትላልቆቹ  ለፖለቲካ ይሰሩበታል  ወጣቶቹ ደግሞ መግደል፣መድፈር እና መዝረፍ ትክክለኛ እና ጀግኖች ስራ መሆኑን እያመኑ ይሄዳሉ፡፡

እንግዲህ  መመድፈራቸው፣ በመግደላቸው እና በመዝረፋቸው ሲሸለሙ፣ሲወደሱ ነበሩ  ነበሩ ወጣቶች  ቦታ ስለቀየርክ ብዛ መድፈር፣ መግደልና መዝረፍ  ወነጀልና ከስነምግባር  ውጪ መሆኑ ሊታስረዳቸው ኣትችልም፡፡ ከመጀመርያውንም መካሪዎች እንዳይሰሙ ሆነዋል ፣ ሃይማኖት የካድሬዎች መሸሸግያና ቤተእምነቶች የጦር መሳሪያ መደበቅያ ሆነዋል፡፡ ቀጥለው ደግሞ ወጣቶቹ  መግደልና መድፈር እንዲለማመዱ ተደርገዋል፡፡ ኣብዛኛው ተደፍረዋል የተባሉ ሴት እህቶቻችን በህወሓት ካድሬዎችና  ታጣቂዎች የተደፈሩ ናቸው፡፡ በፊት ሲደፍሩ የነበሩ ናቸው አሁንም እየደፈሩ ያሉት፡፡ ልዩነቱ በፊት የመድፈሩም የመግደሉም ጉዳይ ለሌላ ወታደር አሳልፎ መስጠት ነበር፡፡ እነቴ ነው የምላችሁ ኤርትራ ወታደር ያለበት ቦታ እንኳንስ መድፈር ይቅርና አንድም ዕቃ ሊወሰድ ኣይችልም፡፡ ብዙ የጉሎምኻዳ ፣ የኢሮብ እና የምዕራብ ትግራይ ወረዳዎች  በዘሄግ ፍርድ ለኤርትራ ስለተሰጡ በኤርትራ ወታደር ስር ናቸው ያሉት፡፡ በነዚህ ወረዳዎች ግን አንድም ቀን  የመደፈርና የመግድል ወንጀል የለም፡፡ የተወሰኑ  ወረዳዎችም በአመራ ምልሻዎች ስር ያሉ የትግራይ መሬቶች አሉ በነዚህም ቢሆን መድፈርና የመግደል ወንጀል አልሰማንም፡፡ አሁን ወንጀሉ ያለው በህወሓት ታጣቂዎች ስር ባለች ትግራይ ነው፡፡ ስለዚህ  ለኢትዮጵያ መከላከያ እና ለሻዓብያ ወታደር ቢሳበብም አስደፋሪዎችና ተደፋሪዎች ህወሓት እንደነበሩ ግልፅ ነው፡፡ ሌላም ይቅር  ለመዋጋት ገብተው በህወሓት መሪዎች ተደፍረው የተገደሉ፣ የወለዱና የተባረሩ በጣም ብዙ ናቸው፣ እስከአሁን ድረስ የመሪዎች መጫዎቻ ሆነው የተቀመጡ አሉ፡፡

ስለዚህ ዋናው መፍትሔ ትግራይ ወደ እሴትዋ መመለስ  ካልተመለሰች እና ህወሓት የሚባል አውሬ ካልተወገደ ሴት እህቶቻችን መደፈርና መታፈን እንዲሁም መገደል ይቀጥላል፡፡  የሽፎን ማህበርም ቢሆኑ ለማስመሰል ካልሆነ በስተቀር ትክክለኛ መፍትሔ ለመስጠት አይደለም አደባባይ ወጡት፡፡ የሃይማኖት አባቶችም ከላይ እንደተጠቀሰው ከሃይማኖት ይልቅ ወደ ህወሓት ካድሬነት ስለሚያደሉ የህፃናት ስቃይ ለነሱ ዋጋም የለውም፡፡

ተደፈሩ፣ተገደሉ እያሉ በየቀኑ በየሚድያው ሲጮሁ የነበሩ አባሰላማ ማህበር ታሉ አሁን፣ ካቶሊክ አባቶች የታሉ ኣሁን፣ በህወሓት ስር ያለ ህዝብ እየተሰቃየ ጭሆቱ ግን ስለ አለማጣና ስለ ወልቃይት ነው፡፡ ለምንድነው ስለወልቃይትና ስለአለማጣ የሚጮሆው እነሱም በሀህወሓት ታጣቂዎች ይደፈሩ፣ይታፈኑ እሰቃዩ ነው ነገሩ፡፡  

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here