spot_img
Thursday, July 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትየብሄራዊ ምክክሩ ጉዳይ አንዳያማህ ጥራዉ  አንዳይበላ ግፋዉ ሆኖብናል !!

የብሄራዊ ምክክሩ ጉዳይ አንዳያማህ ጥራዉ  አንዳይበላ ግፋዉ ሆኖብናል !!

አቡሽ ጌታነህ 

በአገሪቱ ዉስጥ በዜጎች መካከል ያሉትን የዉሽት ትርክቶችና አለመግባባቶች የሚፈታዉን ሂደት ይመራል ተብሎ በመንግስት ተስፋ የተጣልበት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በ2021 መገባደጃ ላይ በአገሪቱ ፓርላማ  ãድቆ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ኮሚሽኑም የተቋቋምበትን ዓላማ ለማሳካት የሦስት ዓመታት እድሜ ተሰጥቶት አእንቅስቃሴዉን ከጀመረ ብዙ ወራቶችን አስቆጥVል፡፡ ይሁን አንጂ የጠ/ ሚ/ር አቢይ አህመድ  መንግስት የሀሳብ ልዩነትን በጦር መሳሪያ እየደፈጠጠ፤ የአገር ሉዓላዊነትንና አንድነትን እንዲያስጠብቅ የተgkመዉን የብሄራዊ ጦር ሰራዊት በክልሎች አስማርቶ ዜጎችን እያስጨፈጨፈ ይህን ኮሚሽን ማቆkሙ ራሱ የሚፈልገዉን እየፈãመ የፊት ለፊት ገፅታዉን ለማሳመር፤ ህዝቡን ለማሳመንና ለማደናገር የተጠቀመበት ስልት ነዉ ይሉታል። ክዚህ በመነሳትም የምክክር ኮሚሽኑ በኢትዮጵያዉያንም ሆነ በዉጭ አካላት ዘንድ የዚህ ስትራቴጂካዊ አካል ተደርጎ በመወሰዱ ተዓማኒነቱ በጠና ታሞና እየተሸረሸረ ይገኛል፡ ሁሉን አቀፍ አለመሆን፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት እና የመንግስት የሰብአዊ መብቶችን አለማክበር የኮሚሽኑን ተዓማኒነት እና ትርጉም ያለው አገራዊ ውይይት ላይ ለመድረስ ያለውን አቅም እጅግ  አድርጎ ጎድቶታል። ይሁን እንጂ በተለያዩ  አካላት የአቅባና ተቃውሞ እየገጠምዉ ቢሆንም ቅሉ ኮሚሽኑ ይህን ተቃዉሞ ቸል በማለትና መፍትሄ ሳይሰጥ ስራዉን በመቀጠል ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ኦረቶዶከስ ትዋሀዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አመታዊ ሰብስባዉን በአጠናቀቀበት አለት በኢትዮጵያ ብሃራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ተገቢና ከላይ የተጠቀሱ ችግሮችን በሚያርጋግጥ መግለጫዉ ላይ ኮሚሽኑን በተመለከተ የመረረ ቅሬታዉን  አሰም~ል፡፡  

ይህ ኮሚሽን በተቆkመበት አዋጅ ላይ በግልጥ አንደተቀመጠዉ ኮሚሽኑ የተgkመዉ በባለ ድርሻ አካላት ላይ ምንም ዓይነት አድልዎ ሳያደርግ ዜጎችን በግልጥና በእኩልነት በማሳተፍ አውያይቶ በአገሪቱ ዉስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ነበር፡፡ ነገር ግን ከአገር ምስረታ ጀምሮ  ለአገር አንድነትና ሉዓላዊነት በግንባር ቀደምትነት ተዋናይ የሆነችዉን አናት ቤተክርስቲያን አንዳትሳተፍ ያደረገዉ ከክልከላ በማያንስ መልኩ የፈãመዉን  በመርሳት ሳይሆን  አንደ ፖልቲካዊ ዝንጋታ አድርገን አንቆጥረዋልን፡፡ ይህም የሚያሳየን ኮሚሽኑ እያክናወነ ያለዉ ጠ/ሚ/ር አቢይ አህመድ የውደዱትንና የፈቀዱትን እንጂ በራሱ ቆሞ ስራዉን ማክናወን ያልቻለ መሆኑን ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ዉስጥ ከ60 ሚሊዮን በላይ ተከታይና ስፊ ተቀባይነት አንዳላት፤ የስላምና የዕርቅ  አናት  አንዲሁም በየቀኑ ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ስላም ለኩሉ ህዝበ ክርስቲያን በሚል የስላም ሰባኪ መሆና እየታወቀ ክዚህ የምክክር ሂድት መከልከል ጠ/ሚ/ር አቢይ አህምድ በ2018 ዓ ም ወደ ስልጣን ከመጡበት ቀን  ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለዉ ክፍተኛ ጥቃት ጠንክሮ መቀጠሉን ያመላክታል፡፡ ከአገልጋይ ካህናቶ‡ና ተከታዮቿ ግድያ፤ ማሳደድና ማፈናቅል፤ቤተ ክርስቲያኒቱን ልሁለት መክፈል ጀምሮ አቢያተ ክርስቲያናትን አስከ ማቃጠል፤ ሃይማኖታዊ በዓላትን አረንÒዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራዋን በማዉለብለብ በነèነት አንዳታከብር አስከ መገደብ ድረስ፤ እንዲሁም ከሌሎች ወንድምና አህት ሃይምኖቶች ጋር አንድትጋጭ በማድረግ የመረበሽ አባዜ ቀጣይ መሆኑን ዜጎች ሁሉ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡  ቤተ ክርስቲያኒቱም ከብሄራዊ ምክክሩ ሂደት ብዙዉ ክተጠናቀቀ በ=ላ ለመግባት መወሰናና ያሉባትን ችግሮች በሂደቱ ላይ እንዲታዩላት ማቅረብ ካልቻለች ወደ ዉይይቱ መድረክ መግባቱ ምን ጥቅም ሊስጣት አንደሆነ ሊገባኝ  አይችልም?  

1 አወያዮችና የምክክሩ ተሳፊዎች በማንና እንዴት ተመረጡ?

በሁሉም ክልሎች፤ዞኖችና ወረዳዎች እንደተመለከትነዉ አውያዮችም ሆነ የምክክሩ ተሳታፊዎች የተመረጡትና የተዘጋጁት በየእርከኑ በሚግኙ የብልåግና ባልስልጣናት እንጂ ገለልተኛ በሆነ አካል አይደለም፡፡ ይህም የሚያሳየን ክላይ እስከ ታች ድረስ ሂድቱና እንቅስቃስዉ እየተዘወረ ያልዉ በብልåግና ፓርቲ አመራር መሆኑን ነዉ፡፡ስለዚህ በየትም የሚግኙ የብልåግና ፓርቲ አባላት መንግስት በሚያምነዉና በሚፈልገዉ መንገድ ይዘዉሩታል እንጂ የህዝብን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያስጠብቃሉ ማለት ዘበት ነዉ፡፡ በአጠቃላይ ከላይ ባለው መረጃ መሰረት በብሔራዊ ውይይቱ ውስጥ ማን ይሳተፋል ለሚለዉ ጥያቄ ተጨባጩ እዉነታ የብልጽግና ፓርቲ አባላትን ከመላው ሀገሪቱ ወደ ተሳታፊነት በማምጣት ሂደቱን እንደሚያስፍåሙ ግልጥ እየሆነ መጠ~ል።

በሌላ በኩል ለመብታቸዉና ለብሄራችዉ ህልዉና ሲሉ ጦር መዝዘዉ በመታገል ላይ የሚግኙ ወገኖች በብሄራዊ ዉይይቱ ላይ አልተካተቱም፡፡ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽኑን የማይድግፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ተåእኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች አልተካተቱም፡፡ ስለዚህ ይህን የመሰለ ክፍተት ባልበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ኮሚሽኑ ስራ የተJላ ሊሆን  ይችላል?

ከዚህ በተጨማሪም የምክክር ኮሚሽኑን ስራ እጅግ ከባድና ፈታኝ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛዉ በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ማለትም በአማራ፤በጉራጌ፤በትግሬ፤ በወላይታ ወዘተ ላይ እየተፈጠሙ ያሉ እኩይ ተግባራት ናቸዉ፡፡የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህልም፡ አገራችሁ አይደለም በሚል ዜጎች ይሳድዳሉ፤ንብርታቸዉን ይቀማሉ፤ ለብዙ ዓመታት ጥረዉና ግረዉ የአቆkሙት ድርጅታቸዉ የማይሆን ምክናያት እየተደረደረ እንዳይስሩ ይከለከላሉ፤ሲብዛም ንብረታቸዉ ይውሰድባቸዋል፡፡ ማስረጃ ለማቅረብ ያህልም በምስራቅ ሽዋ ዉስጥ ክቆቃ ጀምሮ እስከ መቂ ድረስ ክዋናው መንገድ ብዙ ገባ ብሎና ዳር ለዳር ለብዙ ዘመናት ሰፍረዉ በግብርና ስራ ይተዳድሩ የነበሩ የአማራና ጉራጌ አርሶ አደሮች እንዲገደሉ ከተደረገና ከግድያዉ የተረፉት ደግሞ እንዲሳድዱ ከተደረገ በ|ላ በአካባቢው የነበሩ አብያተ ክርስቲያናትን በሀይል አዘግተዉ መሬታቸዉ  ተቀምቶ ለሌሎች መሰጠቱ፣ከሞት የተረፉትም ቢሆን በዚህ ዓመት በድጋሚ እንዲባረሩ ተደርጎ መሬታችዉ መነጠቁ  ለዚህ ዋነኛ ማስረጃ ነዉ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቤት መስሪያ መሬት የሚሰጠዉ ለኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሰለሆነ ሌላዉ የአገሪቱ ዜጋ መሬት የማግኘት መብትም ሆነ እድል የለዉም፡፡ይህ በመሆኑም ሌላዉ እነርሱ “መጤ” ይሉታል  ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ መሬት ከኦሮሞዎቹ ላይ ገዝቶ የሰራዉን ቤት ህገ ወጥ በሚል ስበብ በአለፈዉና በዚህ ወር ሙልጭ አድርገዉ አፈረሱት፡፡ የቤት ፈረሳዉ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያ ክልልም በሁሉም ከተሞች በባሰ ሁኔታ ተፈäሚ ሆናል፡፡እንደ ተፈናቃዮች አበባል ከሆነ የቤት ፈረሳዉ አገር ለመጥቀም ሳይሆን ከኦሮሞ ዉጭ ያለዉን ኖአሪ  ለማፈናቀልና ለማባረር የተደረገ ሴራ ነዉ ይሉታል፡፡ ሴራ መሆኑን የሚያመላክተዉ ደግሞ በየክተማዎቹ ዉሰጥ ቤታችዉ ለፈረሰባቸዉ ዜጎች ሌሎቹ የየከተማ ናሪዎችች ቤት እንዳያከራዩአቸው በህግ መከልከሉ ነዉ፡፡

ከዚህ በከፋ ሁኔታ በክልሉ ዉስጥ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ኦሮሞኛ kንkን መናገር ካልቻለ በማንኛዉም የመንግስት መ/ቤት አገልግሎት ለማግኘት እንዲሁም ሆስፒታል ሄዶ ለመታክም ከፍተኛ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ይህም የሚሆነዉ አገልግሎት ሰጭዉ ባለስልጣን ወይም ሰራትኛ በአማርኛ ለመናገር ፈቃደኛ ስለማይሆን ብቻ ነዉ፡፡  ይሀን ዓይነት ችግር በግልጥ ለማስቅመጥ በችግሩ ዉስጥ ያለፈ ግለሰብ የተናገረዉን ብጠቅስ እዉነታዉን ይገልጥልኛል ብየ አመንሁ “ I feel comfortable staying in Kenya than in Oromia”. ይህ ማለትም በኦሮሚያ ከመቆየት ይልቅ በኬንያ መቆየት ምቾት ይሰጠኛል ማለት ነዉ፡፡ የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በአገሪቱ  ዉስጥ እርቀ ሰላም ለማዉረድ ጥረት በሚያደርግበት በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ፕረዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት ቅራኔንና ቁርሾን የሚፈጥሩ ንግግሮችን በብዙሃን መገናኛ እየተናገሩና እየፎክሩ እንዴት በአገሪቱ ዉስጥ እዉነተኛ እርቀ ሰላም ሊወርድ ይችላል ተብሎ ይታመናል? ይህ ዓይነቱ አስከፊ ድርጊት እየተፈãመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰላም ይመጣል ብሎ ማስቡ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ የምክክር ሂደቱ እንዲስምር ክተፈለገ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የምክክር ኮሚሽኑ ባለስልጣናት ይህን ደም አፋሳሽ ድርጊት ሀይ ማለት ነበረባቸዉ፡፡ ይህ ዛቻና ፉክራ ባልበት ሁኔታና በክልሉ ዉስጥ እየተፈãመ ያልዉ ግፍና በደል åዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት የምክክር ኮሚሽኑ ምን ዓይነት እርቀ ስላም ለመፍጠር ይደክማል?   

           2      ማጠቃለያ 

የብሔራዊ  ምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ቀዳሚ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል  በሀገሪቱ የተለያዩ ብሔረሰቦች እና የፖለቲካ ቡድኖች መካከል አንድነትን ፣ ዕርቅን እና ማህበራዊ ትስስርን ማሳደግ መሆን አለበት። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እናት እንደመሆ~ መጠን ብሄራዊ ውይይቱ የተለያየ ሃሳብ ያላቸዉ ቡድኖች እንዲሰባሰቡ እና የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እድል ይሰጣል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሁን አንጂ የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ከላይ በተጠቀሱት መሰናክሎች ምክንያት ግቦቹን ለማሳካት አቀበት እየገጠመው ይገኛል። መንግስት እውነተኛ  ውይይት እና ማሻሻያ ለማድረግ ቁርጠኝነት ማጣቱ፣ ዜጎችን በማስርና በማሳደድ የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ረገጣ እና በተቃውሞ ሰልፎች ዝግጅት ላይ የወሰደው እርምጃ  ኮሚሽኑ እምነትን እና ተአማኒነትን ለመፍጠር  በሚያደርገዉ ሂደት ላይ ታላቅ ዳገት ፈጥሮበታል። ሆኖም፣ ኮሚሽኑ አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር ውስጥ አወንታዊ ሚና የመጫወት አቅሙን በማሳደግ፤ እነዚህን ተግዳሮቶች በማስተካክልና ክመንግስት ጋር ያልዉን ቁርኝት በመቀነስ ለሁሉም ዜጎች እውነተኛ ተወካይና ሁሉን አቀፍ አካል ከሆነ እና የተለያዩ አመለካከቶችን ማክበርና ማስትናግድ ክቻለ  ለእውነተኛ  የውይይት ውጥኖች ወሳኝ ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ይሁን እንጂ የዶ/ አቢይ አህመድ መንግስት የምክክር ኮሚሽኑን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ ለመጠቀምና ለመቆጣጠር እንዲሁም  የሃሳብ ልዩነትን ማፈኑ ከቀጠለ  ኮሚሽኑ በአገሪቷ ውስጥ ትርጉም ያለው ዕርቅና ዘላቂ መረጋጋትን ያመጣል ተብሎ መታሰብ የለበትም። እንዲያዉም በዉይይቱ ላይ ያልሆነ ሀሳብ፤አዋጅ ወይም ሁሉንም ሳያካትት በአጀንዳዎች ላይ ክስምምነት ላይ ተደረሰ  የሚል መልስ ከተሰጠ አገሪቱን ልትወጣዉ ወደማትችለው ቅርቃር ዉስጥ አስገብ~ እንዳያልፍ ክፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ይህ ሀላፊነት ደግሞ በኮሚሽኑ ባለስልጣናት ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ ግልጥ ነዉ፡፡

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here