Homeነፃ አስተያየትየአማራው ሕዝብ የተድቀነበትን የህልውና አደጋ በዘላቂነት ለመወጣት የትግሉ ስልት ምን መልክ መያዝ ...

የአማራው ሕዝብ የተድቀነበትን የህልውና አደጋ በዘላቂነት ለመወጣት የትግሉ ስልት ምን መልክ መያዝ  ይኖርበታል?

Advertisement
World Wide Travel Group
ከድረ ገጽ የተገኘ
ከድረ ገጽ የተገኘ

ሽመልስ አማረ

የአማራው ሕዝብ በተለይም ምሁሩ በብዛት ውይም ሁሉም በሚባል ደረጃ እንደአማራ ሳይሆን እንደኢትዮጲያዊ በማሰብና ኢትዩጲያዊ አጀንዳ በማንገብ አገራዊ መፍትሄ መሻት ያስፈልጋል የሚለውን አመለካከት ለረጅም ጊዜ እንደገዢ ሃሳብ ተቀብሎ በአንጻሩም እንደአማራ ተሰባስቦ የአማራውን ጥቅም ማስከበር ያስፈልጋል የሚለውን አስተሳስብ እንደጠባብ አመለካክት አይቶ ለብዙ ጊዜ ሳይቀበሉ ቆይቶ እንደነበር ግልጽነው፡፡ ባሁኑ ሰአት አማራው በተጋረጠበት የሕልውና አደጋ ምክንያት የዚያ አይነቱ አመለካክት ተቀይሮ አማራው እንደአማራ ተደራጅቶ ለመብቱ መታግሉ ለመላው አማራ ሕዝብ አማራጭ የሌለው መሆኑ ግልጽ ከመሆኑም በላይ ቅን አስተሳስብ ያላቸው ሌሎች ኢትዮጲያኖችም ትግሉ ፍትሕዊ መሆኑን ይቀበላሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የህልውና ትግል ምን አይነት የትግል ስልት ቢከተል ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ ያመጣል የሚለውላይ ግን አለመግባባት ውይም ብዠታ ስላለ በግልጽ ተወያይቶ የጠራ አመለካክት ገዢ ሃሳብ ሆኖ መውጣቱ ወሳኝ ስለሆነ በዝምታ ማለፉ ወይም የአንዳንድ ግለስቦችን አመለካክት በጭፍን መቀበሉ ትልቅ ዋጋ ስለሚአስከፍል ከወዲሁ ማስብ አስፈላጊነው፡፡ 

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንድሰጥ ያነሳሳኝ በቅርቡ በመስከርም አበራ የቀረበውን ጽሁፍ አንብቤ፤ አንዳርጋቸው ጽጌም በአንከር ሚዲያ ቀርቦ ከመስከረም አበራ ጋር ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማና ጽሁፉ እንከን የለሽ መሆኑን የገለጸበትን ቃለ መጠይቅን ከስማሁ በኋላ ስለሆነ አስተያየቴ ይኽን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ቢሆንም የመስከረምን እና አሁን ደግሞ አንዳርጋችውም የተቀበለውን አመለካክት የሚደግፉት ስላሉ ትግሉ ምን አይነት የትግል ስልት መያዝ አለበት የሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡ በርግጥ እኔ የድርጅት አባል ስላልሆንኩ ሃሳቤን የማስተላልፈው በዚህ መንገድ ቢሆነም የድርጅት አባል የሆኑትም የውስጥ ውይይት በዚህ ላይ ቢያደርጉ የተሻለ አረዳድ እንዲፈጥሩ ይረዳል፡፡ 

በእኔ እይታ የአማራው ሕዝብ የተጋረጠበትን የሕልውና አደጋ በዘላቂነት ሊፈታ የሚችለው ስርአቱ ሲቀየር ስለሆነ የሕልውና ትግሉ ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ኑሮት ሁሉንም ማሰባሰብና ሌሎች ኢትዮጲያኖችንም የሚያካትት ግንባር ሲፈጠር ስለሆነ በመጀመሪያ ይኽን አመለካክት ገዢ ሃሳብ አድርጎ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ በርግጥ ይኸን አስተሳሰብ በስራ ለመተግበር የፋኖው እንቅስቃሴ በአንድ መአከላዊ የወታደራዊና የፖለቲካዊ አመራር ስር መጥቶ የጠራ እራእይና ፍኖተ ካርታ ሲኖረው ስለሆነ በዚህ ላይ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ጎን ለጎን የሚስሩ ስራወች አይኖርም ማለት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው መስከረም ያለችው “የመጀመሪያው ወሳኝ አመታት(Formative Years) ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት በአማራ ብሄርተኝነት ጉዳዮች ብቻ ነው፡፡” የሚለው ስህተት የሚሆነው፡፡ ለዚህም ነው ካሁኑ ያመለካከት ጥራት ካልተፈጠረ ትግሉ ብዙ ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ ሊሳክ ይችላል ወይ የሚለውን እንድንጠይቅ የሚአስገድደን፡፡ 

በርግጥ ለውይይት እንዲመች መስከረም አበራ “ የአማራ ብሔርተኝነት እና የሃገረ ኢትዮጲያ መስተጋበር” በሚል ያቀረበችውን እና የአንዳርጋቸው ጽጌ በዚህ ላይ ድጋፍ የስጠበትን ቃለመጠይቅ በሙሉ ማየቱ ጠቃሚ ሲሆን ለመነሻ ከጽሁፉ ገጽ ስድስት ላይ መስከረም ያሰፈረችውን እንመልከት፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“በአዲሱ የአማራ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የአማራ ህዝብ ትግል ሩቅ መንገድ በመጓዝ እራሱንም ኢትዮጲያንም ለመታደግ ከፈለገ በትግሉ የመጀመሪያ ወሳኝ አመታት(Formative Years) ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት በአማራ ብሄርተኝነት ጉዳዮች ብቻ ነው፡፡ በነዚህ ወሳኝ ጊዚያት ስለኢትዮጲያ ሃገረ መንግስት እጣ ፈንታ የሚበይን ሆነ የሚያወሳ የትግል ስልት ለመተለም መሞከር ‘እራስ ሳይጠና ጉተና’ ከመሆኑም ባሻገር ከአማራ ጠሉ ጎራ በኩል በተለመድውው ዱላ ተደጋግሞ ለመመታት በተለመደው የስተት መንገድ መመላለስ ነው፡፡” 

መስከረም ከላይ ያለቸውን ስንመለከት አንድ ጥያቄ ማንሳት ግድ ይላል፡፡ ይኽውም የአማራ ሕልውና በዘላቂነት የሚረጋገጠው የስርአት ለውጥ ሲኖር ነው ካልን ተግሉ ያማራውን ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ኖሮት ሁሉንም ለማሳተፍ እና ሰፊ ግንባር ለመፍጠር የሚደረገውን የፖለቲካ ስራ ጎን ለጎን ማካሄድ ሲገባ ለሚቀጥሉት አመታት ስለዚህ አናነሳም ማለት ትግሉ ላይ የሚአስከትልው ጉዳት እንዴት ይታያል የሚለው ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ወገንን ማብዛት ባንጻሩም ጠላትን ማዳከም እንዴት የትግል ስልት ሆኖ አይወሰድም የሚለው ሌላው ጥያቄ ነው፡፡ አንዳርጋችውም ሙሉ በሙሉ ጽሁፉን ሲደግፍና አድናቆቱን በመግለጽም ከስላሳ አመት በፊት የነበርኝ አቋም ነው ሲል ያለፉት ሰላሳ አመታት ይዞት የነበረው ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ሁሉም ነገር ስተት ነበር ነው የሚለን? 

ሌላው መስከረም በገጽ ስመንት ላይ እንዲህ ትላለች “ አዲሱ የአማራ ብሄርተኝነት ቀዳሚ አላማው በመላ ኢትዮጲያ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በህይውት የመኖር መብት ማስከበር ነው፡፡” ይህ አባባል የተቀደስ ቢሆንም ከላይ መስከረም ካለችው ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ ምክንያቱም ስለእትዮጲያ አናወራም ከተባለ የአማራው ክልል በፋኖ ነጻ ቢወጣም በመላ ኢትዮጲያ ከአማራ ክልል ውጭ ያለው አማራ ከዚህ አስከፊ ችግር ሊላቀቅ አይችልም፡፡ ካአመታት በኋላ ስለኢትዮጲ ማንሳት ስንጀምር የሚነሳ ጉዳ ነው ማለትም አይቻልም የህልውናው አደጋ በነሱም ላይ የተጋረጠ ስለሆነ፡፡ 

ስለዚህ የመላው አማራ የሕልውና አደጋ የሚቀለበሰው ትግሉ ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ኖሮት ሁሉንም ሲያስተባብርና ግንባር ሲፈጥር ነው የሚለው አስተሳስብ ገዢ አመለካከት ሲሆን ከዚያ የሚቀዳ ከአድማስ ባሻገር የሚያይ ራእይ፤ ከዚያ የሚቀዳ ፍኖተ ካርታ፤ ከዚያ የሚነሳ የአጭርና የረጅም ግብ ማሰብ ያስፈልጋል ባይነኝ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብዙ ዋጋ እንደሚአስከፍል ከወዲሁ መረዳት ይኖርብናል፡፡ ትግሉ ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ያስፈልገዋል ስል የኣማራው የህልውና ትግል በሁለተኛ ደረጋጃ ይታይ ሳይሆን የህልውናው አደጋ በዘላቂነት መፍትሄ የሚገኝበት የትግል ስልት ያስፈልጋል ማለቴ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በመጨረሻም መስከረም ያቀረብኩት ጽሁፍ የመጨረሻ ቃል ሳይሆን ለውይይት የቀረበ ነው እንዳለችው ይኽን አስተያየትም በዚያ መልኩ አይተን የትግሉ ስልት ጥራት እንዲኖረው ገንቢ ውይይት እንዲኖር ብናበረታታ ጥሩ ነው፡፡ 

ካክብሮት ጋር 
ሽመልስ

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

- Advertisement -

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – Borkena English
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News