Homeነፃ አስተያየትየሸፈተውንና ካድሬው ያላሸነፈውን የአማራ ህዝብ ልብ በጦር ጀኔራሎች  ጋጋታ ለመመለስ መሞከር  ብልጽግና...

የሸፈተውንና ካድሬው ያላሸነፈውን የአማራ ህዝብ ልብ በጦር ጀኔራሎች  ጋጋታ ለመመለስ መሞከር  ብልጽግና መራሽ መንግስት  ቀብጸ ተስፋ

Advertisement
World Wide Travel Group
Amhara _ Ethiopian Politics
ፎቶ ከኢዜአ

አበራ ገረመው

ሽምቅ ውጊያን  በወቅቱ መግታት ያልቻለ አቅመ ደካማ መንግስት ሁለት አጣብቂኞች  ውስጥ ይገባል፡፡ አንድኛው  የሸማቂዎችን ፍላጎት ለማሟላት ሲል ማድረግ የማይፈልገውን ፖለቲካዊ ውሳኔ መወሰን ነው(ይህ ስልጣንን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ እስከማስረከብ ልደርስ ይችላል)፡፡ ሁለተኛው አማራጭ  ያለውን የሌለውን  ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅሙን አረባርቦ ሸማቂዎችን ለማጥፋት ሲል የጭካኔ እርምጃ /Barbaric action/በአመጸው ህዝብ ላይ  መውሰድ ነው፡፡ 

 የጭካኔ እርምጃ   ህዝብን ለበለጠ አመጽ የሚያነሳሳ  ነው፡፡ አንድ ሰው ካለ ፍትህ መገደል ፣መሰቃየት፣መታሰር… ወዘተ ማለት መቶዎችን በመንግስት ላይ የሚያሳምጽ እርምጃ ነው፡፡ ለምሳሌ ተጎጂው ሰው የቅርብ ዘመዶችና የሩቅ ዘመዶች፣ ቡና የሚጋሩ ወዳጅ ጎሬቤቶች፣የስራ ባልደረቦች…አሉት፡፡ የአንድ ሰው መጎዳት የእኒያን ሁሉ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ በአማራ ክልል  በአንድ አመት በመንግስትና በታጣቂዎች መካከል በተደረገው ውጊያ  ብቻ  በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ልዩ ልዩ ጉዳት እንደደረሰባቸው  ይነገራል፡፡ ታዲያ የዚያ ሁሉ  ሰው መጎዳት  በወዳጅ ዘመድ ሲባዛ  በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በመንግስት ላይ  ይበልጥ የሚያሳምጽና ለሸማቂዎች ድጋፍ የሚያሰጥ አይደለምን?፡፡ የጭካኔ እርምጃ  ወዳጅን ሳይሆን ጠላትን የሚያበዛ እርምጃ ነው፡፡ 

አብዛኞች የጭካኔ እርምጃ የወሰዱ የአለም የጸረ ሽምቅ ዘመቻዎች መጨረሻ ላይ በድል ሳይሆን በሽንፈት ተጠናቅቀዋል፡፡ ከዚህ ባለመማር አሁን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የሚመራው  መንግስት የመረጠው አማራጭ  የጭካኔ ወታደራዊ ዘመቻ  ሆኗል፡፡  የዐለም ዐይን በእስራኤል ህዝቦላና በእስራኤል ኢራን ውጥረት እንዲሁም በራሺያ ዩክሬን ጦርነት ላይ ባተኮረበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያለውን ጦር በሙሉ በአማራ ክልል አሰማርቶ የመጨረሻ ያለውን ኦፕሬሽን ጀምሯል፡፡ 

በርግጥ ባለፉት አንድ አመት የመንግስት ሰራዊት በአማራ ክልል ያልተቋረጠ ኦፕሬሽን ሲያደርግ ነበር፡፡ አሁን ልዩነቱ ድሮንና አየር ሀይል መጠቀም፣በክልሉ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ  በምስራቅ ቀጠና ያለውን ጦር ወደ አማራ ማስገባቱ እና ደጋፊ ናቸው የሚባሉ የህብረተሰብ አባላትን በገፍ  ወደ ማጎርያ ካምፕ ማስገባት ነው፡፡  ከዚያ ውጪ አመጹ ህዝባዊ  ስለነበር በ2016  ሙሉን አመት የተካሄዱ ኦፕሬሽኖች የአማጽያንን አቅም ከማጎልበት ውጭ ምንም ውጤት ሳይመጡ እስካሁን ዘልቀዋል፡፡ ለዚህም ይመስላል መጠነ ሰፊ ዘመቻ መንግስት የጀመረው፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በአሁኑ ሰአት የአማራ ክልል አመጽ እንደሚባለው በጥቂት  የሸፈቱ ሰዎች የሚዘወር አይደለም፡፡ ኔት ወርኩ በበሀገር ውስጥና በአለምአቀፍ ደረጃ ተስፋፍቷል፡፡ያመጹ አካላት አቅማቸውን ከእለት ዕለት እያጎለበቱ የመጡ ይመስላሉ፡፡ ይህንን የተወሳሰበ   መረብ መበጣጠስ  በቀላል የሚቻል አይመስልም፡፡ 

አማራን ህዝብ ለአመጽ ያነሳሱ አሳማኝ መነሻዎች አሉት፡፡ ሌሎችን የሩቅና የቅርብ ትርክቶችን ወደ ጎን አድርገን በወለጋ የተካሄደው ጭፍጨፋ ብቻ  ራሱን የአማራ ማህበረሰ ብቻ ሳይሆን  ሌሎችን የኢትዮጵያ ህዝቦች ያስቆጣ ድርጊት ነበር፡፡ አስራ ሰባት የቤተሰብ አባላት በወላጋ ጭፍጨፋ ያለቁበት አንድ አዛውንት “አላሃ ለምን በህይወት አተረፍከኝ” እያለ በሰለለ ድምጹ በቲቪ ሲናገር ላየን የደረሰብን የልብ ስብራት በቃላት አይገለጽም፡፡ ይህንን ጭፍጨፋ መንግስት እጁ ባይኖርበት እንኳ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም ተጠቅሞ ጭፍጨፋውን በአፋጣኝ ማቆም፣ የፈጸሙ አካላትን  ለፍርድ ማቅረብ፣የህዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ፣ለጠፋው ጥፋት ይቅርታ መጠየቅና ተጎጂዎችን ማጽናናት ነበረበት፡፡ ይህንን በወቅቱ ባለማድረጉ  የብልግና መንግስት የፖለቲካ ድንቁርናን ያረጋገጠና የአማራ ህዝብ ልቡ በመንግስት ላይ እንድሸፍት ያደረግ ክስተት ሆነ፡፡ 

“አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ቀድሞ ነበር አንጂ መጥኖ መደቆስ”!!፡፡ መንግስት እየወሰደ ያለው የጭካኔ   እርምጃ የሀገሪቱን ፖለቲካ ይበልጥ የሚያወሳሰብ ካልሆነ በስተቀር  ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ አይደለም፡፡ 

የአማራ ክልል ከ2015-16 ዓ.ም በህዝብ አመጽ አብዛኞች የወረዳ መስተዳደሮች  ካከደሬው እጅ ወጥቶ ክልሉ ስርአት አልበኝነት የነገሰበት ከሆነ በኋላ  አሁን  ካድሬዎችን ገሸሽ አድርጎ ጀኔራሎች ከፊት አድርጎ  በየአካባቢው በማሰማርት በጸጥታ ጉዳይ ህዝቡን  ማወያየት ምንም ፋይዳ ያለው አይደለም፡፡ ጀኔራሎች ለመዋጋት ነው የሰለጠኑት አንጂ ለፖለቲካ ስራ አይደለም፡፡ ጀኔራሎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን አዋጭ በሆኑና ባልሆኑ  የጦር ስትራቴጂ ላይ ማማከር አንጂ ካድሬን ተክተው ህዝብን ማወያየት  በምን መስፈርት ነው? የጦር ጀኔራሎች በጸረ ሽምቅ ውጊያ ድል የሚያደርጉ ስልቶችን ቀምረው  የአመጹ መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን መፍትሄ መጠቆም  አንጂ ከሙያቸው ውጪ መዘባረቅ “የጨነቀው እርጉዝ ያገባል”ን ያስታውሳል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ለማኝኛውም መፍትሄው ለአመጹ ምክንያት የሆኑ የህዝብ ጥያቁዎችን  መመለስ የሚያስችል የፖለቲካ ብልጠት እንጂ ጭካኔ የተሞላበት  ወታደራዊ  ዘመቻ ውጤት እንደማያመጣ ልሰመርበት ይገባል፡፡ 

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News