Homeነፃ አስተያየትየትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለብት ተስማምታችሁ ግዙን ወይንስ አማራጭ እንፍጠር?

የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለብት ተስማምታችሁ ግዙን ወይንስ አማራጭ እንፍጠር?

Advertisement
World Wide Travel Group
People of Tigray
ከኢትዮጵያ ኢንሳይት ድረ ገጽ የተገኘ

ከራሴላስ ወልደማርያም 

አንድ የስቶኮሎም ሲንድረም (Stockholm Syndrome) የሚባል የስነልቦና በሽታ አለ። ስያሜውን ያገኘው ከስዊድን በስቶኮሆሎም ከተማ የባንክ ዘራፊዎች ክስተት ነው።  የባንክ ዘራፊ አራት ሰዎችን አፍኖ ይወስዳሉ።  የተወሰዱት ከመነጠልና ከመፍራት የተነሳ ለአጋቻቸው ፍቅርና ክብር ያሳያሉ። ለአጋቶቹ አክብሮት ብቻ ሳይሆን ወዳጅና አዳኝ አምላል ያደጉታል። ከዛ አልፈው ተርፈው በፓሊስና በህግ አስከባሪ ላይ የጠላትነት ስሜት ያዳብራሉ።  በመጨረሻም ፓሊስ ወንጀለኛውን ሲከስ አንመሰክርም ይላሉ። ከዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ የተሰጠፈው ቪዲዮ ብዙ ምሳሌዎች አሉትና ስለ ስቶኮሎምንሲንዲረም ለመረዳት ከፈለጉ ይመልከቱ።

ይን ነገር በበርካታ ቦታዎች ተደጋግመው ሲታይ ይህ የአጋችና ታጋች። የጨቋኝና ተጨቋኝ፤ የአንባገነን እና የተጨቋኝ ህዝብ ቁርኝት የስቶኮሎም ሲንድረም ወይንም የስቶኮሎም ስነልቦናዊ ቁርኝት ይባላል። 

አንድ ሰው ታፍኖ ተወስዶ ከተሰቃየ ለአፋኙ ጥላቻና በቀል ሳይሆን ቁርኝት ይፈጥራል፤ ማምለጥ አይፈልግም። ሊያድኑት በሚመጡ ፓሊሶችና ቤተሰቦች ሳይቀር የጥላቻ ስሜት ያጎለብታል ከዛ አልፎ አጋቹን ድፕግፎ ከፓሊስ ጋር እስከመታኮስ የደረሱ አሉ።

ይህ ቁርኝት በጨቁዋኝ ባልና ሚስት መሀከል ይታያል። ባልዋ እየደበደባት ሌላ ሰው ሊያስጥላት ገብቶ ባልዋን ቢገፈትረው ነብር ሆና አዳኝዋን በጥርሷም በጥፍሩዋም የምታጠቃ አለች። የደብዳቢዋ ክፏ ከሚነሳ እሷ ብትቀጠቀጥ ደስ የሚላት ሚስት አለች። ይህ የስቶኮሎም በሽታ ይባላል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በፓለቲካውም እንዲህ አይነት ቁርኝት ይፈጠራል። ስታሊን ዘመን ተገርፈው ተቀጥቅጠው የተጣሉ ኮሚኒስቴች እንባቸውን እያፈሰሱ ተንበርክከው ስታሊንን ሲያሚመልኩ ነበሩ። የሶቭየት ህብረት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረው ሞቶሎቭ ለስታሊን ታማኝነቱን ለመግለጽ የልጆቹን እናት ሚስቱን ለስታሊን ሰጥቶ አስረሽኖ ለስታሊን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ አገልግሏል። ፈርቶ ነው እንዳይባል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለነበረ ከስታሊን ማምልጥ ለሱ ቀላል ነበር።  የኤርትራ አንባሳደው ሆነው እስከ ዛሬ በታማኝነት ለኢሳያስ የሚያገለግሉ ሚስታቸውን ወስደው ለኢሳያስ አፈወርቄ ሰጥተው አሳስረው እስካሁን ያለችበት አይታወቅም። እሳቸው ግን በታማኝነት አንባሳደው ሆነው በአምልኮ ደረጃ አቶ ኢሳያስ አፈወርቄን ያገለግላሉ።

ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ደግሞ የስቶኮሎም በሽታ ተጠቂ የሆኑት ፈረንጅ ቢሆኑ ኖሮ በርካታ የምርምር ውጤት ሊታተምባቸው የሚችል ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ ናቸው። 

ለአሳሪዎቻቸው ለገረፋቸው፤ በጭለማ ቤት አስረው፣ ለሰደቧቸው፣ ለገረፏቸው ያላቸው ፍቅርና ክብር በቃል ተገልጦ አያልቅም። እሳቸው የንባብና የእውቀት አድማስ በጣም ጠባብ ስለሆነ ይህንን በሽታቸውን እንደ የክርስትና ይቅርባይነት አድርገው ያቀርቡታል። እሳቸው ክርስቲያን ነኝ ይበሉ እንጂ ክርስትና እንደ ሬስቶራንት ሜኑ መርጠህ የምትመገበው አይደለም። የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ የበደሉንን ደግሞ ይቅር ማለት ግድ ነው። እሳቸው በስልጣን ተመክተው የገረፏቸውን፣ የገደሏቸውን፣ ግደሉውልቸው ብለው የቀሰቀሱባቸውን ለምሳሌ እስከዛሬ ይቅር በሉኝ አላሉም። ይልቁንም መለስ ዜናዊን ቢሮው ድረስ ሄጄ ይቅርታ አድርጌልሀለሁ፣ እወድሀለሁ ብዬዋለሁ። ስለዚህ ቅደስ ነኝ ይላሉ። አልገባቸውም እንጂ እሳቸው የስቶኮሎም ሲንድረም ተጠቂ ናቸው።  እስከ አሁንም የስነልቦነ ሀኪም ድጋፍ ስላልጠየቁ እስከመቃብራቸው ድረስ የዚህ ቁርኝት ተጠቂ ሆነው ይቀጥላሉ። 

አቶ ታምራት ላይኔ እድሜ ልካቸውን ሙሉ የታገሉበትን አላማ ተቀምተው፤ ሌባ ተብለው፤ ልጅህንና ሚስትህን እንገላለን ተብለው፤ እንደ ድሮ ሌባ ሻይ ገመድ ታስሮበት በገበያና እንደሚለቀቀቅ አቶ ታምራት ላይኔም ፓርላማ ተጠርቶ በቴሌቭዥን ካሜራ ተተደቅኖ “እኔ ሌባ ነኝ፤ ያለ መከሰስ መብቴን ይህ የተከበረ ፓርላማ ያንሳልኝ” እንዲሉ አስብለዋቸዋል። ለምን ሲባሉ ልጅህንና ሚስት ግን እንችላለን ስላሉኝ ይላሉ። ይህ እንግዲህ የስቶኮልሆም ሲንድረመ መንስኤው ነው። ያም ትልቅ ፍርሀት፣ ይህ ፍርሀት ደግሞ እሳትን እንደ ብቸኛ አዳኝ ማየት። እሱን በመውደድ በማፍቀር በማምለከ እራስን የማዳን ጥረት ነው። ይህ ነው የስሜት ቁርኝት የሚፈጥረው። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከዛ መነጠል ይሄንን በሽታ ያጠናክረዋል። አቶ ታምራት ለ8 ዓመታት ለብቻቸው ታስረዋል። እስር ቢት ቆልፈው ሲሰድቧቸውና ሲያንጓጥትቷቸው ቆይተው። እራሳን ለማጥፋት ፈልጌ አልቻልኩም ብለዋል።  ከዛ አይምሮዋቸው የወለደው ጠላቶቻቸውን እንደ ወዳጅ እና ባለ ውለታ ማየት ነው የማምለጫ መንገድ ሆኖ ታያቸው። 

አቶ ታምራት ያበዱ ኮሚኒስትና ጸረ አብዮት ያሏቸውን ሁሉ ገለዋል። በቃለመጠይቅልቸው እንደገለጹት “ነጻነት ከጠመንጃ አፈሙዝ ይገኛል” ብለው የሚያምኑና ያስተማሩ ኮሚኒስት መሪ ነበሩ።

እሳቸው በስልጣን ላይ ሆነው የበደሏቸውን ሰዎች “በድያቸሀለሁና ይቅር በሉኝ” እስካሁን አላሉም። አቶ መለስ በሳቸው ላይ ያደረገውን እስልቸውም በብዙ ነፍሳት ላይ ፈጽመዋል።  ይሁንና እባካችሁ በስልጣን ተመክቼ ለበደልኳችሁ ለገደልጇችሁ፤ ለገርፍኳችሁ ይቅር በሉኝ አላሉም።  ሱፈቱ ቀጥ ብለው የሄዱት ወደ አቶ መለስ ዜናዊ ቢሮ ነበር። ልክ የስታሊን እስረኞች ፊቱ ተንበርክከእው ታማኝነታቸውን ይገልጹለት እንደነበር  አቶ ታምራትም ያደረጉት መለስን እወድሃለሁ፤ አልተቀየምኩህም፤ እንደውም ክርስቶስን እንዳውቅ አደረግክልኝ ስለዚህ እወድሀለሁ ብለው እቅፈው ገጸ በረከት ስጥተው ነው የወጡት። አቶ “መለስ ደነገጠ” ይላሉ አቶ ታምራት። መለስ ስለ ስትል ህልም አላነበበም እንጂ አቶ ትምህርትን ወስዶ የጊቢ ጥበቃ ሀላፊ አድርጎ ቢሾማቸው እንደስልቸው ታማኝና ደረቱን ለጥይት የሚሰጥ አገልጋይ አያገኝም። ኮለኔል መንግስቱ ሻለቃ ፍቅረስላሴ ወግደረስን ከነ ተፈሪ በንቲ ጋ ለመረሸን ቀላቅሎ ቃታ ሊሳብ ተዘጋጅ ከተባለ ቦሀላ መንግስቱ እንደ ቅዱስ ገብርኤል ብቅ ብሎ ፍፍቅስልሳ  ና ውጣ ብሎ አድኖ የእድሜ ልክ አሽከር ፈጠረ። 

የአቶ ታምራት ባህሪ የጨቋኝና የተጨቋን ስነ ልቦና ቁርኝትን እንጂ ክርስትና ይቅር ባይነት አይደለም። አቶ ታምራት የክርስትና መንፈስ ቢሆን ቀድመው የበደሏቸውን ሰዎች ይቅር በሉኝ ነበር የሚሉት።

- Advertisement -

አቶ ታምራት እኮ በኢህአዴግ ውስጥ ሁለተኛ ሰው የሆኑት ፍቅርን እየሰበኩ አይደለም። ጨካኝ አብዮተኛ ነጻ አውጪ መሪ ነበሩ። ስለዚህ ብዙ ንጹሀንን ገድለዋል። ፊውዳል፤ አደሀሪ፤ የኢንፔርያሊዝም ቡችላ፤ ጠንቋይ፤ ቄስ፤ጸረ አብዮተኛ፤ ደርግ፤ ኢስፓ፤ ከፋፋይ፤ አንጃ ብለው።

ከዛም አልፈው የተማረኩ የደርግ ወታደሮች እነ ኮለኔል ሰረቀ ብርሀን፤ እነ ጄኔራል በረታ ገሞራው፤ እና የኢህአፓ መሪዎች እነ ደብተረውን ገድልዋል።  እኛ ባናውቅ እንኳን ፈጣሪ አቶ ታምራት በግፍ ያጠፋቸውን ሰዎች ስምና ቁጥር አይረሳም። በእርግጥ ይሄንን ባያደረጉ ኖሮ የኮሚኒስት ታጣቂ መሪ መሆን አይችሉም ነበር።

ከዛም አልፈው የዐምሓራውን ህዝብ ሀረር ሄደው በጅምላ ግደሉ እስከማለት ደርሰዋል። ድሬደዋ ሱማሌዌችን ሰብስበው ለማነጋገር ወደ እፕዳራሽ ሲገቡ እየጨበጡ ሲያልፍ እንደ ሱማሌ ያለበሰ አንድ ስው ነበር። ሳይጨብጡ አለፏት። ከዛ ወንድማችን ሀጂ እንትና ነው ሲሉት እኔ ደግሞ “ነፍጠኛ” እዚህ እንዴት ገባ ብዬ ነበር ብለው ተመልሰው ጨበጡት። እንዲህ አይነት ጨቅላ ጨካኝ አገልጋይ ስለሆኑ ነው ታምራት ጠቅላይ ሚኒስቴር ያደረጋቸው። ለራሳቸው ክርስትና መግደል ያሚያጸድቅ እና ይቅርታ የማያስፈልገው የጽድቅ ተግባር መስሎ ነው የሚታያቸው። ይሁንና የሱማሌ አዛውንቶች ታምራትን ቆመው አጨብጭበው ሸኝተው ማንም ሱማሌ ይሄንን እንዳይሰማና ዐምሓራ እንዳይገድል አውግዘው ተለያዩ። በዚህ ምክንያት ኦሮሞ እንጂ ሱማሌ ዐምሓራን አልገደለም። በመጨረሻውም ህወሓት በጄኔራል ኳርተር አዝማችነትና በአንድ ኢሌ አደራጅነት ብዙ ክርስቲያን ዐምሓራ በመሆኑ ከትግሬ እየተነጠለ በሊስት ተገድሏል። በስህተት አንድ ትግሬ ቄስ ብቻ ነው ጅጅጋ ውስጥ የሞተው።  ወደ ቁምነገር ስንመለስ አቶ ታምራት ክርስትና የመሰላቸው የስቶክሆሎም ሲንድረም በሽታቸው ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።

የህዝብና የጨቋኝ የስቶሎሎም ቁርኝት 

ህዝብም የስቶክሆሎም ሲንድረም ይጠቃል።  ከጨቆነው ከረገጠው፤ ካዋረደው ከገደልውና ካስፈራራው ጋር የስነ ልቦና ቁርኝት ይፈጥራል።  አቶ መለስ ሲሞቱ አዲስ አበባ ላይ ያየሁት እውነተኛ እንባ አንዱ መገለጫው ነው።

ብዙ ህዝብን ያገለገለ፤ የህዝብን መብት የከበሩ፣ ሀገር ያበለጸጉ መሪዎች ሲሞቱ ህዝብ ሀዘኑንና አክብሮቱን ይገልጻል እንጂ እንባውን አፍሶ ከፎቅ ላይ ሲወድቅ አይታየም። የሴንጋፑሩ መሪ ሲሞቱ ሰው ተሰልፎ ሸኛቸው። የሰሜን ኮርያ አንባገነን ሲሞቱ ግን ሰዎች ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ እስከ እራስ መሳት ደርሰዋል። 

አንድ ጨቋኝ በጣም ጨካኝ የሰውን ህይወት ሁሉ የተቆጣጠረ ሰው ከሞተ ህዝብ እንባ በእንባ ይሆናል። እንደ ሰሜን ኮርያው ኪም ኤል ሱንግ፤ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ፤ እንደ ማኦ ያሉ ጨቋኞች  ሲሞቱ ህብብ እንባውን ያፈሳል።  ብዙ ሚዲያ ይሄንን የስቶኮሎም ሲንድረም መሆኑን ሳይረዱ ህዝብ ተገዶ ወይንም ፈርቶ ነው የሚያለቅሰው ይላሉ። ባቶ መለስ ጊዜ በአይናችን ያየነው በይበልጥ ያለቀሱት የሚጠሏቸው ሰቆች ናቸው። አቦይ ስብሀት ሲጠየቁ “መለስ ሞተ፣ ጫላ ሞተ፣ አበበ ሞተ ኢህአዴግ ይቀጥላል” ባለው ሞቱን ሲያቃልሉት በቅንጅት ረብሻ ልጆቹ ግንባር ግንባራቸው የተባሉበት የአዲስ አበባ ነውልሪዎች ግን ከትግራይ በላይ ነው ሲያለቅሱ የታዩው። ምክያቱም ይህ የስቶሎሎም ሲንድረም የጨቋኝና የተጨቋን ቁርኝት መገለጫ ነው። 

የትግራይ ህዝብና የስቶኮለም ቁርኝት፤ እባካችሁ ታርቃችሁ ግረፉን

በትግራይ ህዝብ ላይ ሰሞኑን የማየው ጩሀትና እንባ እባካችሁ ተባብራችሁ ያኔ የጣላችሁብንን ቀንበር መልሳችሁ ጫኑብን የሚል መማጸን ነው። ማርማራዊት የምትባል ያኔ ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል የነበረች ህወሓት ርንባዋ ዱብ ዱብ እያለ ስትማጸን በቲክቶክ አየናት። አሁን እንባው እባካችሁ ተስማምታችሁ ሲፈልጋችሁ እሰሩን። እባካችህ ታርቃችሁእንዳናነብ፤ እንዳንጽፍ፤ እንዳንጠይቅ፤ እንዳንቃወም፤ አድርጉን። እባካችሁ ከናንተ ውጪ የመደራጀት፤ ፓርቲ የመመስረት መብት አንፈልግም። እባካችሁ ቶሎ ኑና አንድ ለአምስት በሚባለው ጠርንፋችው መተንፈሻ አሳጡን። ከፈለጋችሁ የበኩር ልጆቻችንን ያለኛ ፈቃድ እየወሰዳችሁ ማግዱዋቸው።  እኛ ብዝሀ ፓርቲ፤ ብዝሀ አስተሳስብ ፤ የራሳችን ሀሳብ ምን ያደርግልናል። እናንተ አስባችሁ የነገራችሁንን እንደ እግዜር ቃል መውሰድ ይሻለናል እያሉ ነው እነ ማርማዉት በእንባበ። የናንተው ካድሬዎች ይርገጡን፤ ይስደቡን ሲፈልጉም እንደ ጥጃ እየወሰዱ ይሰሩን የሚል እንባና መማጸን ነው። 

ልምድ ሰዎች በራሳቸው ማሰብ ይጠላሉ የሚባለው ብዙ ተጽፎበታል። Fydor Dostoevsky’s Crime and punishement ሰዎች የሚፈሩት አዲስ እርምጃ መውሰድ አዲስ ነገር ማለት ነው ይላል (Taking a new step, uttering a new word is what people fear most”።  ሰዎች ማሰብ አይወዱም። ስው አስቦ ቢነግራቸው ይቀላቸዋል።

ጀርመኖች ለምን ሂትለርን ደገፋችሁት ሲባሉ። Hitlor made us “free from freedom” ነበር ያሉት። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም “ከግል ነጻነት ነጻ አወጣን” ማለት ነው። በራሳችን አናስብም፤ በራሳችን አንወስንም። ሄትለር የሚያስፈልገንን ይነግረናል እንፈጽማለን፤ ድሮ እኛ ተጨንቀን፤ ተጠበን መዝነን ነበር የምንወስነው። አንዳንዴ ትክክል ይሆናል አንዳንዴም ግን ስህተትም ይሆናል። ስህተት ሲሆን በስህተታችን  መጸጸት ውስጥ እንገባለን። አሁን ግን በራሳችን አናስብም በራሳችን አንወስንም በምንሰራውም ስክተት ጸጸትም ተጠያቂነትም የህሊና ወቀሳም የለብንም ነው።  

የትግራይ ህዝብም ለ50 ማሰብም፤መመዘንም፤ መወሰንም፤ በውጤቱ መጸጸትም ረስቶ ኖርዋል። መለስ ብቻ ያስባል ሌላው ይተገብራል። መለስ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች ሲል ማሰብ የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ አረ አሉላ የተዋጋበት ዶጋሊ፤ ሰቲት ኤርትራ ውስጥ ናቸው። አዱሊስ የሚባለው የአክሱም ወደብ እኮ ኤርትራ ብሎ ጣልያን የጠራው መረብ ምላሽ ነው ያለ አንድ ባለ ፒኤች ዱ አንድ ፕሮፌሰር አልነበረም።

አረ የአሉላ ከተማ እኮ አስመራ ይባል ነበር ያለ ምሁር የለም። አረ አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሀይማኖት፤ አንድ ባህል ያለን ስለሆን ነን ምናልባት ዘመዳሞች ሳንሆን አንቀርም ብሎ የጠየቀ ምሁር የለም። 

መለስ ኢትዮጵያ ምኒሊክ የፈጠራት የዛሬ መቶ አመት ነው ሲለ አረ አጼ ዮሀንስ፤ አጼ ቴዎድሮስ ኢዛና ካሌብ የሚባሉም ነገስታት ነበሩ ያለ የለም። መሬት ሰው ጠፍጥፎ አልሰራው አይሸጥም ሲል  እውነት ነው: መሬት ብርድልብስ አይደል ነበር ያሉት።  ህዝብ ቀርቶ ምክትሎቹ እነ አቶ ስዮም መስፍን፤ አባይ ጸሀዮ፤ አርከበ እቁባይ፤ ገብሩ አስራት፤ ስዬ አብርሀ፣ ብርሀን ገብረክርስቶስ ፣ጻድቃን ገብረትንሳይ በራሳቸው ማሰብ መብት አልነበራቸውም። 

ታድያ የትግራይ ህዝብም ህወሓት ከሀሳብ ሸህም ገላግሎነ ለ50 ዓመታት ኖርዋል። ከነጻነት ሸክም ጠብቆን ኖርዋል። አሁን እንዴት አድርገን እናሰብ የሚል የመስላል? ግራ ተጋብቷል፣ እነ ቴዎድሮስ በርዕዮት እነ አሉላን፣ እነ ፕሮፌሰር ጌታችፕውን እና ዳዊት ከበደን ጠርቶ አወያይቶ ነበር።  ውይይቱ ትግራይን ያለ ህወሓት ማየት እንደከበዳቸው መገንዘብ ይቻላል። 

ስለዚህ ክደቂቅ እስክ ሊቅ ቀላል ይሆናል ብል የሚያስበው ህወሓቶች ሰብሰብ ብለው ከማሰብ ሸክም ነጻነት አድኗቸው ነው። የህወሓት መሪዎች ነፍሱን ለማዳን የትግራይ ወጣት ከጥይት ሲያፈገፍግ የህወሓት መሪዎች በጥይት በለው።  “ለትግራይ ያልሞተ ላማን ሊሞት ነው” ረሽኑት ሱሉ ሰምተናቸው ጦሩ ወደ መቀሌ  ሲጠጋ በሩጫ ደቡብ አፍሪካ ሄዳችሁ የቀረበላችሁን ሁሉ ፈርሙ እራሳቸውን አዳኑ።  

የትግራይ ህዝብ ተነጥሎ ለሀምሳ አመት በጨቋኝ ስርአት ውስጥ በመኖሩ በስቶኮሎም ሲንድረም ከህወሓት ጋር ተቆራኝቷል። ሳሞራ የኑስ በ40ኛ የህወኅት በአል ላይ “ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ማለት ደግሞ ህወሓት ማለት ነው፡” ብሎ ነበር።  ይሄንን ሳሞራ ሲል ማንም የትግራይ ምሁር ምን ማለትህ ነው አላለም።  ወሬ ለማድመቅ እነ ሰራዊት ፍቅሬ ካኪ አሰፍተው ሽርጥ ገስተውላቸው ብዙ አርቲስቶች ወደ ደደቢት ወስደውት ነበር።  ከነሱ መሀል አንድ ህሊና ያላት አስቴር በዳኔ የምትባል ትያትረኛ ተገኘችና ሳሞራን ይህ ምን ማለት ነው አለችው?  አንድ የትግራይ ፒኤች ዲ ግን ከማሰብ ሸክም ህወሃት ስለገላገለው አልጠየቁም። ሁሉም ተጣድፎ ሳሞራን ላማሞካሸት ታድያ ምን ሊባለ ነው። አንድ ነን አሉ። በመጨረሻ የትግራይ ህዝብና ሳሞራ እንድ እንደሆኑ በጦርነቱ ጊዜ ታየ።  ሳሞራ ወጣት ሚስቱን አቅፎ ለውለታው አብይ 2000 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ሰጥቶት በአንዴ ባለ 300 ሚሊዮን ብር ባለ ሀብት ሆነ። ቤት ተሰርቶለት ኑሮውን አደላድሏል።  ያ እኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ነን ያለው ሳሞራ ህዝቡ በመራሀብና በመሞት ሲጠበስ ቆንጆ ወጣት ሚስቱን አቅፎ በቪላ ውስት ተንቀባረረ።

ጄኔራል ሳሞራም አረ ተዉ ስንዴ እንኳን ይግባ አላለም።  ሳሞራም የማሰብ ነጻነት አቶ መለስ ነጻ አድርጎት ነው የኖረው። አሁን ነግሬያቸው ነበር እነሱ ጠግበው ጦር ሰበቁ፤ መክሬያቸው አልሰሙም፤ እንደውም ሲያንሳቸው ነው ይላል።

እለዚህ የትግራይ ህዝብ እኛና ሀወሃቶች አንድ ነን፤ ያለነሱ ጭቆና መኖር አንችልምና ሰብሰብ ብላችሁ ግዙን ከማለት ይልቅ ረጋ ብሎ የትግራይ ህዝብ ከሀወሓት እሳቤ ምን አገኘ? ከህወሃት ፓሊሲ ያተረፍነው ምንድነው? ጭቆና ከጠፋ ምድር ትውጠናለች የምትል የፍርሀት ጭንቀት የጠቀስነው የስቶኮሎም በሽታ ምክንያት ነው።  ታድያ ይህ የስቶኮሎም ሲንድረም ምልክት ካልሆነ ምን ሊባል ይቻላል? 

የትግራይ ህዝብ ማለት ያለበት

ስለዚህ እስቲ እኛ የምናዘው፤ በጠመንጃ፤ በካድሬ የማያራውጠን፤ እኛ የምንሾመው ስንፈልግ ደግሞ የምናወርደው የፓለቲካና የመሀብራውዊ ተቋማት እንገንባ የሚል መሆን አለበት። ከማሰብ ነጻ እንሁን ሳይሆን አስበን የምናዘው ድርጅት እንፍጠር ነው ምልክት ያለበት። 

እስካሁን አንድ የሚያስብ የትግራይ ፕሮፌሰር፤ ዶክተር፤ ምሁር፤ ቄስ፤ ጻጻስ የለም። አሁን ግን ብቅ ብለው ፕሮግራም ጽፈው ሀገራዊም ክልል ስም አለማቀፋዊ እይታ ፈጥረው መደራጀት መጀመር አለባቸው።

እስቲ ኤቢሲዲ የቆጠራችሁ የትግራይ ምሩቃን። ከህወሓት ቁጥጥር ውጪ የመምህራን ማህበር፤ የሰበካ ጉባኤ፤ የመስጊስ መሪ፤ የሰራተኛ ማህበር፤ የጋዜጠኞች ማህበር፤ የህግ ጠበቆች ማህበር፤ የሴቶችና የወጣቶች የገበሬዎች ማህበር ፍጠሩ።  የቻላችሁ ደግሞ መለስ እንዳልው ሳይሆን ለ21ኛው ክፍለዘመን የሚመጥትን የፓለቲካ ፓርቲ ገንቡ። ከቻላችሁም ደግሞ ይህ የስቶኮሎም ሲንድረም በቀላሉ ስለማይላቀቅ የስነልቦና ሀኪም አማክሩ

ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ።  ስለ ስቶኮሎል ሲንድረም ማወቅ የምትፈልጉ ይሄንን ዮቲዮብ ተመልከቱ።

https://www.bing.com/videos/riverview/relatedvideo?q=the%20stockholm%20syndrome&mid=2AFC03A2CFF3EEF2628E2AFC03A2CFF3EEF2628E&ajaxhist=0

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News