
ራሴላስ ወልደማርያም
የቸገረው እርጉዝ ያገባል የባሰበት ደግሞ እምነት ይላሉ። አብይ እነ ጃዋር ሳይቀር ጠቀሜታው አቋል ብለው አምነዋል። አብይ አህመድ ሰሞኑን የኦነግ ሸኔን ምክትል ጃል ሰኚን የኦሮሚያ ሚሊሻ ሀላፊ አድርጎ ሾሟል። በሌላ በኩል ደግሞ ጃዋር መሀመድ አብን ደግፎ የኦሮሞን ስርአት ለማቆም እንደማይችል ስለተረዳ እኔም አለሁ “ልብ አድርጉልኝ” እያለ ነው።
አሁን አብይ ለሚታረዱ ክርስቲያኖችና ዐምሓሮች ግዜ የለውም። ግጥምያው የኦሮሞ ብሄረተኞች ደርቢ ሆንዋል። የ72% አትዮጵያ ህዝብ ወይንም ከ120 ሚሊዮን የአትዮጵያውያን ውስጥ 86.4 ሚልዮን አትዮጽያውያን አጀንዳ የአብይ ገዳይ መሆን ከቆመ ስንብቷል። በአብይና በብአዳን፣ ድህዴን፣ አፋርና ሱማሌ መሀከል ግንኙነት የቅኝ ገዢና የተገዢ ግንኙነት ይመስላል። ፏክክሩ በኣሮሞ ብሄረተኞች መሀከል ሆንዋል።
የአብይ ስናኖር ኦሮሞ ስንሞት ደግሞ ኦሮምያ እንሆናለን
ለነገሩ አብን በፌስ ቡክ አልከታተልም። ይሁንና አንድ በቲክቶክ አብይ የአማራ ክልል ኦሮምኛ ካልልስተማረ “ዋ” የሚል ማስተጠንቀቂያ ሰማሁ። እኔ አንድ ሰው ብዙ ቋንቋ መማር ይጠቅመዋል ብዬ አስባለሁ። አሁን ደግሞ ኦሮምኛ መማር እነ ሽመልስ አብዲሳና እነ አብይ አህመድ በኦሮምኛ የሚረጩትን የዐምሓራውን ዘር የማጥፋት ቅስቀሳ ለመረዳት እና የነዚህን መርዘኞች መርዝ ለማርከስ ጠቃሚ ነው።
አብይ ስልጣን ላይ ሲመጣ ትግራይ፣ ዐምሓራው፣ ደቡቡ፣ ኤርትራው፣ የአለማቀፍ መሀበረሰቡ ሳይቀር እልል ብሎ እስከ ኖቤል ሽልማት ተሰጥቶት ነበር። አብይ ድጋፍ ያላገኘው እና ህዝብ ተሰልፎ ያልወጣው በኦሮምያ ክልል ብቻ ነበር። ይመስለኛል አብይን በቅርብ ስለሚያውቁትና ከሱ በተሻለ ለማ መገርሳ መሪ እንዲሆን ይፈልጉ ስለነበረ አንድም በኦሮምያ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ አልተካሄደም። ይልቁንም በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አዲስ አበባና አርባ ምንጭ ነው እስከ 5 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ሰንደቅ አላማ አሰርቶ ህዝብ ሰልፍ የወጣው። አሁን አብይ ከትግራይና ዐምሓራን ደም ተቃብቷል። የአዲስ አበባን፣ የደቡብን፣ የኦርቶዶክሱን፣ የእስላሙን፣ የጉራጌውን፣ የሲዳማን፣ የሀድያን ድጋፍ አጥቷል። ስለዚህ አሁን መንጠልጠያ አካም አካም ብቻ ሆንዋል። አብይ ስልጣን ላይ ለመቆየኝ የሚችለው የኦሮሞን ህዝብ ወደ እሳት በመንገድ ብቻ ነው። ለአብይ አህመድ ዳንኤል ክብረት፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ብርሀኑ ነጋ፣ አበባው ታደሰ፣ ተመስገን ጥሩነህ ህይወታቸውን ይሰጡለታል ብሎ የሚያስብል ጅል ብቻ ነው። ሬድዋን ሁሴን ከህወሀት በፊት ያስቀድመኝ ሲል ኖሮ ቀን ሲጎድልባቸው ሳንጃውን ስቦ ነው በድሮንስ የቀጠቀጣቸው።
ስለዚህ ካሁን እያጋጨና እሳት እያነደ የሚሞቀው ኦሮሞን እየማገደ ብቻ ነው። ይሳካለት እንደሆን በቅርብ ቀን ይታያል።
ችግሩ የአብይን ማንነት ቀስ በቀስ የኣሮሞ ብሄረተኞች አብይ ከኦሮሞ አባት እንዳልተወለደ እየነገሩን ነው። ኮለኔል ገመቹ አያና የሚባል የኦነግ ባለስልጣንን ቃለ መጠየቅ ላይ እያሾፏ በኦሮሞነት ደም በመቁጠር ከሆነ ከዶ/ር አብይ በላይ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም እና አጼ ኃይለስላሴን ይበልጣሉ ብለው እውነቱን ተናገሩ። ዶ/ር አብይ እያምታንቱ ነው እንጂ የት ከ 7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንደተማሩ እንኳ የሚያውቅ ወይንም ማን አባታቸው እንደሆነ የለም።
አንድ ትልቅ የኦነግ ባለስልጣን አንድ ግዜ አብይ እንደመጣ ተገናኝተን አብይ ኦሮምኛ አይችልም ሲሉኝ ያኔ ራሴ ሰምቻለሁ። ታድያ እሱ ራሱ በስነስርአት የማያውቀውን ኦሮምኛ፣ ለጎንደሬ ልጆቹና ሚስቱ ያላስተማረውን ኦሮምኛ ለአርማጭሆ፣ ለደንምበጫና ለወልቃይቴ ወጣት በግዴታ ይማር ሲል የጥላቻ ጠማቂነቱን ያሳያል።
ብሄረተኞች የማይናገሩትን ቋንቋ፣ የማይኖሩበትን ባህል ይዘው ነው ስለ ባህልና ቋንቋ ሙሾ ሲያወርዱ የሚውሉት። እስቲ ጃዋር መሀመድ እንመልከት የኦሮሞ አንደኛ ብሄረተኛ ነኝ ሲል ይውልና የሚጽፈውና የሚሸጠው ጨቆነኝ በሚለው ቋንቋ ነው። ምክንያቱም የሱ ቁቤ ወንዝ እንደማያሻግረው ያልውቃል።
ታድያ መጽሀፍ በማይጽፍበት ቋንቋ የጭልጋ ወጣት ኦሮምኛ ቢማር ምን ሊያነብ ይሆን። የዐምሓራ ወጣት ኦሮምያ ሄዶ ይሰራል እንዳይባል ኦሮምኛ የሚያውቁት፣ በኦሮሞ ባህል ያደጉት፣ በቁቤ የተማሩት የወለጋ ሰዎች እየታረዱ ነው። ወለጋ ሄጄ እንደ ድሮ ተጋብቼ ተዋልጄ እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ እብድ ብቻ ነው።
አብይ ሳይማር የተማረ መምስል፣ ሳይወለድ ኦሮሞ የሆነ አስመሳይ ነው። የአብይ አህመድ አላማ ኦሮሞን ከሌላው በመነጠል ኦሮምን በበታችነት ስሜት በማጦዝ ስልጣኑ ሲነቀነቅ ኦሮሞ ጄኔሳይድ እንዲፈጽምለት ማዘጋጀት ብቻ ነው። ለ27 ዓመታት ቪላና ቪ8 ለመንዳት ብሎ ኦሮሞን ሲሰልል፣ ሲጨፈጭፍ ነው የኖረና የከበረ ነው። አሁን ደግሞ በድሮን እየጨፈጨፈው በየ እስር ቤቱ እያስገረፈው ነው። የአብይ ጠገዴ ኦሮምኛ ካልተማረ ዛቻ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣልዋት” ጉዳይ ነው።
በመጀመሪያ የፌዴራል አመራሮች እነ ብርሀኑ ነጋ፣ ጌዲዮን ጢሞቲዌስ፣ ሬድዋን ሁሴንን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አበባው ታደሰን ኦራምኛ ተማሩ ይበላቸው ። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ወለጋም ሄደው ህዝብ ማነጋገር ይገባቸዋል።
አብይ ልክ እንደ ትግሪኛው ገጣጥሞ እንደመያወራው ነው ኦሮምኛም የሚያወራው። እስቲ ኦሮምኛ የሚናገሩትን ሰዎች ጠይቁ። አብይ የ NPD syndrome ተጠቂ ስለሆነ ብዙ ነገር ማስመሰል ችሎታ አለው። አሁን እንደውም እያሻሸለ ነው እንጂ የአብይ የአፍ መፍቻው ቋንቋ ኦሮምኛ አይደለም። አፍ መፍቻ ያልሆነ ቋንቋ ደግሞ በቅላጼው ይታወቃል። የቀጄላ መርዳሳን ወይ የሌንጮ ለታን አማርኛ የሰማ አፏቸውን በአማርኛ እንዳልፈታ ማንም ይረዳል።
የአብይ ትዕይንት አንድ: ከሜለሀ ጽቡቅ በትግሪኛ
አብይ ህወሀቶች ዘረኞች እንደሆነ ስላወቀና ትንሽ ትግርኛ አጥንቶ እነ ሳሞራ የኑስን ከሜለሀ ጽቡቅ እያለ አንጀታቸውን በልቶ ከሬዲዮ ተሸካሚነት እና ከ7ኛ ክፍል ትምህርት አዘልለው ኮለኔል አሉት። ሁላችንም እንደምናውቀው ትግሬዎቹ ትግርኛ የተናገረ ሁሉ ወንድማቸው ነው። ስለዚህ ህወሓቶችን ጢቢ ጢቢ ተጫወተባቸው። “ከሜለሀ ጽበቅ” ሲላቸው አንጀታቸው ቡጭ ቡጭ እያለ የስለላ መዋቅር ሀላፊ፣ ከዛም የደህንነት ስልጣኑን ተጠቅሞና የሰው ጽሀፍ አስገልብጦ ሰመጣና ዶክትሬት ነኝ ስል የኛ ሰው ነው ብለው ተዉት። አብይ የዘረኞች ድክመታቸውን ተጠቅሞ ብብታቸው ውስጥ ገብቶ የራሳቸውን መርዝ ጋታቸው።
ትዕይንት ሁለት አካም አካም
ጀነራል ተክለ ብርሀን አብይ ከኢንሳ ሲያባርረው ትግሪኛውን ትቶ ፕሮቴስታንትና ኦሮሞ ሆነ። ይህ የአብይ ኦሮምኛ የሚጀምረው። ልክ ዛሬ ዳንኤል ብርሀን ጌታቸውን ሲደግፍና ደብረ ጽዮንን ሲቃወም ለምን በትግርኛ ንግግር አታደርግም ብለው ትግሬነቱን ጥርጣሬ ውስጥ ሲጥሉበት አሁን ትግርኛ መማር እንደጀመሩት ማለት ነው። የአብይም ኦሮምኛ ንግግር ከኢንሳ መባረር ቦሀላ የመጣ እንጂ አፏን የፈታበት ቋንቋ አይደለም።
አብይና ለማ
አብይ ሲባረር አቶ ምናሴን በቅጽል ስሙ አባ ዱላን ጡት ጠብቶ ታዛዥ ሆነ። አባ ዱላ ደግሞ ኦነግን ለማጥፋት ህወሓት የዳቦ ስም ሰጥቶ ኦሮሞ ያደረጋቸው የሰሜን ሸዋ ሰፋሪ ናቸው። ኦሮሞ ቅን ስለሆነ ድሮ ስምህ ማን ነበር ብሎ አይጠይቀውም። ሞት ባይኖር መለስ ባጫ አለው፣ ምናሴን ደግሞ አባ ዱላ፣ ዮሃንስ ለታ ደግሞ ሌንጮ ለታ ሄኑ፣ ሌሎቹም እነ ኩማ፣ እነ ዳውድ እየተባሉ ከኔ በላ ኦሮሞ የለም የሚሉት ስማቸውን እየቀየሩ ነው። ጀነራል አለምሸት ብቻ ነው ያልቀየረው። ጀነራል አበበ ተክለሀይማናት የአየር ሀይል አዛዥ ሲሆን ጀነራል አለምሸት ምክትል መሆኑን አልወደደውምና አለምሸት ስሙን እንደነ አባ ዱላ የኦሮሞ እንዲቀይር ይገለዋል። አለምሸት አልችልም ይለዋል። አበበ ይናደድና አንተ ከአባዱላ ትበልጣለህ ወይ ይለዋል። ያኔ አባዱላ የመከላከያ ሚኒስቴር ነበርና። አለምሸት እሱማ ምናለበት የስድስተኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ነው። እኔ ከንጉሱ ዘመን ጀምሬ የሰበሰብከት የትምህርት ማስረጃን ስንቱን ቀይሬ እችለዋለሁ አለ ይባላል። አለምሸት በመንግስቱና በንጉሱ ዘመን ወታደር ስለነበረና የተማረከ ነው። እነ ጀነራል በረታ ገሞራውና እነ ኮለኔል ሰረቀብርሀን እነ ጻድቃንንና እነ ሀየሎምን የዘመናዊ ጦርነት ስልጠና ሰጥተውና እያማከሩ መንግስቱን ቢጥሉም ዐምሓራ ስለሆኑ ህወሓት ስልጣን ሰይዝ እነሱን ሲረሽን አለምሸት ኦሮሞ ነኝ ስላለ ትቶ የአየር ሀይል ምክትል አደረገው።
የኦፒዲኦ መረዎች የተጋነነ የኦሮሞ ስም የያዘት አብን ጨምሮ ከስድስተኛ ክፍል ያላለፏት ምርከኞች ናቸው። ትንሽ ፊደል የቆጠሩት እነ ደመላሽ፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የዐምሓራ ስም ይዘው መቀጠል ግድ ሆነባቸው።
አብዮት አሀመድ ወደ አብይ አህመድ የቀየረው አንደኛ ስላልተማረ ሲሆን ሁለተኛ እሱም ደበላ ወይንም ጫላ እራሱን ማለት ይችል ነበር። ይሁንና ጫላ ብሎ እነ ሳሞራን በከሜለሀ ማጭበርበር ስለማይችል ነው እራሱን አብይ ያለው። አብይ በኦሮሞ ነኝ ብሎ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ስሙን ከአብዮትን ወደ መገርሳ ይቀይር ነበር የሚቀይረው።
ይሁንና ጀነራል ሳንቲም ሲያባርረው ኦፒዲኦ ሆኖ ብቅ አለ።ከዛ ስልጣን ተንከባላ ለማ እግር ስር ወደቀች። አብይ የለማን እግር ላይ ተጠምጥሞ አለቅም ብሎ ስልጣኑን እንዲሰጠው ለመነ። በመጨረሻ ስልጣኑን ለሀለት አመት ብቻ እንዲሰጠውና ከዛ ከምርጫ ባሀላ እንደሚሰጠው መሆኑን ለማሳመን ሞከረ። ለማም በሰው መሀል እግሩ ላይ ሰው ሲወድቅ ይሉኝታ ይዞት እሺ አለው። ግን አብይን የሚያውቁት ኦሮሞ የደህንነት ሰራተኞች ለማን እኛ ይሄንን ሰው እናውቀዋለን እንዳትሳሳት ብለው ለመኑት። ለማ ግን አብይ ለሁለት ዓመት ስልጣኑን ያስጠብቅና ይመልስልኛል ብሎ አመነው። ለማን አትስጥ ያሉት የደህንነት ሰዋች አብይ ጠቅላይ ሚኒስቴር በሆነ ማግስት ሀገር ጥለው ሸሹ። የአብይን ተበቃይነት ያውቃሉና።
የለማ ጅልነት
ለማ በመታለሉና በጅልነተ ልክ አስገድዶ እንደተደፈረ ወንድ ገዱን ዋጥ አድርጎ ስለኢትዮጵያም ስለ ኦሮምያም የሚያነሳበትን ሰው ስልክ እንኳን አያነሳም። አብይ በቅርብ ሆኖ የለማን ሚስጥሮች መረጃ ሰያሰባስብ ስለነበረ ለማ ጃዋር ባቀናበረው የኦሮሞ ድርጅቶች ህብረት ላይ ሊቀመንበር ሆኖ ተመርጦ ከምርጫ ባሀላ ተመልሶ መምጣቱን አብይ ሲገባው አብይ መኪናውን አስነስቶ ደህነታቹን ይዞ ጃዋር ቤት ከች ብሎ እኔ ነኝ የኦፒዲኦ ሊቀመንበር እኔ ነኝ የምፈርመው ሊቀመንበሩም እኔ ነኝ ብሎ የኦሮሞ ህብረትን አፈረሰው። በአንዴ በታተናቸው። የኦሮሞ ብሄረተኛ ነን ያለትን በሙሉ አንድ በአንድ አጠፋቸው። ሀጫሉን ግድያ ቦሀላ ጃዋርን ጠራርጎ አሰረ፣ እነ በቴን ገደለ፣ የእነግን መሪን ዳውድ ኢብሳን የቁም እስር አደረገ፣ ለማን ከኦሮምያ አንስቶ መከላከያ ሚኒስቴር ያለ ስልጣን ሾምክ አለ ከዛ በደንብ እንግሊዘኛ የማይችለው ለማ የፋኦ ዳይሬክተር ተብሎ ፈረንጅ አገር በጥቅም ታሰረ። ዛሬ ለማ ወጥቶ ስለ ኦሮሞ ፓለቲካ እንድ ነገር ቢተነፍስ የቀዳቸውን ሚስጥሮች አውጥቶ ያዋርደዋል። ስለዚህ ለማ አፏን ዘግቶ ተቀምጧል።
ስለዚህ
1ኛ፣ አብይ ኦሮምኛ ዐምሀራ መናገር ካለበት መጀመሪያ ሚስቱንና ልጆቹን ነው ማስተማር ያለበት። ከዛ እነ እነ ብለን ስዩም፣ ጌድዮን ጢሞትዮስ፣ ሬድዋን ሁሴን መሆን አለባቸው
2ኛ፣ በመንግስቱ ኃይለማርያም ግዜ በነበረው የህዝብ ቆጠራ ኦሮሞ 28.8 በመቶ ነበር። የዐምሓራው ቁጥር ደግሞ 28.4% ነበር። አሁን ኦነግ በጣለው የኦሮሞነት መመዘኛ ማንም ከዐምሓራና ከሌላ ብሄረሰብ ጋር የተነካካ ሁሉ እየታረደ ነው። ወለጋ ያደጉትን ልጆች ደብረ ብርሀን ሄዶ ማየት ይቻላል። ብዙዎቹ ከኦሮሞ አባትና ከወሎ ሴቶች የተወለዱ ናቸው። ሀሁ አያውቁም። ወለጋ የተማሩት በቁቤ ነው። የሚናገሩት ቋንቋ ኦሮምኛ ነው። እንደውም ዲግሪ ይዘው የቁቤ/ኦሮምኛ አስተማሪ የሆኑ ሁሉ አስተማሪዎች ካንፕን ውስጥ ነበሩ። ሰዎች የሚገደሉት እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የኦሮሞ ስም መደርደር መመዘኛ ስለሆነ አበበ፣ አየለ፣ ሸምሱ፣ ሂራሞ ያለበት ሁሉ እንደ መጤና ወራሪ ተደርጎ ስለታረደ ነው። ግምሽም ሶስት አራተኛ ኦሮሞ ያለበት ሁሉ ኦሮሞ ነኝ ማለት አይችልም። ልክ እንደ ናዚ የኑረንበርግ ህግ ከአስራ ሁለቱ ቅማያቶቹ ውስጥ አንድ ይሁዳ ካለ ይሁዳዊ ተብሎ ተመድቦ ወደ ጋዝ ማጨሻው ይላክ ነበር። የአብይና ይህን የኦሮሞነት ተፎካካሪነት ንጹ፣ የንጹህ፣ ንጹሕ ኦሮሞ መፍጠር ክርክር ስለሆነ ዛሬ የህዝብ ቆጠራ ቢካሄድ የኦሮሞ ቅጥር ከ15% በመቶ አይበልጥም። ይህ ማለት 85% ኦሮሞ ያልሆነ መሀበረሰብ አለ ማለት ነው። የመንግስቱንም የህዝብ ቆጠራ ብንወስድ እንኳን 72% የሚሆን ኦሮሞ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ አለ። ይህ ተገዶ ኦሮምኛ የሚናገርበት ምክንያት የለም። አብይ ኦሮምኛ እራሱ ለምን አይናገርም፣ ለምን ጃዋር የኦሮሞ ብሄረተኛነት ጳጳስ ነኝ የሚለው በኦሮምኛ መጽሀፏን አያሳትምም። እነዚህ ሰዎች ልጆቻቸውን እንኳን በኦሮምኛ አያናግሩም ይሁንና ኦሮሞን እንደፈረስ ይጋልባ
3ኛ፣ አብይ እራሱ አንድ ጠብታ ኦሮሞነት የለበትም። እንጀራ አባቱ አህመድ አሊ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እኔ አብን እንደ ልጄ አድርጌ ነው ያሳደኩት ብለዋል። የአብይ እናት መናገሻ ቃልቻ ቤት ቡና ሲያፈሉና ሲካድሙ ነው አህመድ አሊ ያገኟቸው። እርጉዝዋን ሴትዮ ገድ ትሆነሀለች ተብሎ ተጠንቁሎ ነው እርጉዝ ሴት ይዘው ጅማ የገቡት። የጠንቋዩ ቃልን እናታቸው በአብይ ላይ ጨምረው አብይም እድሜ ልኩን ይሄንን ለማሳካት በመሞከሩ ተሳካለት። ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ self fulfilling prophecy የሚሉት ነው። አህመድ አሊ ቃለ መጠይቅ ሰጥተው እኔ እንደ ልጄ አድርጌ ነው ያሳደኩት ካሉ ቦሀላ ወድያው ባልታወቀ ምክንያት ሞቱ። ብዙ ጉድ ሳይዘበዝቡ ተቀበሩ።
4ኛ፣ አብይና ብዙ የኦሮሞ ብሄረተኞች የተቀላቀለባቸው በጉዲፈቻና በሞጋሳ የተወሰደ ሲዳማ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ዛሬ ቀይ መልኩን ይዞ ኦሮሞ ነኝ ይላል። በአንድ በኩል ኦሮሞ ኩሽ ነው ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የሴማቲክ ቀይ መልክ ይዘው እነ አብይ፣ እነ በቀለ ገርባ (ገርባ ማለት በሞጋሳና ጉዲፈቻ የተወሰደ ባርያ፣ ገባር ማለት ነው) እነ ጃዋር ኦሮሞ ነን ይላሉ። ኩሽ ጥቁር ቢበዛም ፈካ ብሎ ጠይም ነው እንጂ የኩሽ ቀይ የለም። እነዚህ ሰዎች ጉራጌ አምሓራ የነበሩና በባርነት ኦሮሞ የተደረጉ ናቸው። እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት። ጂነዲን ሶዶ አንደኛ አምሓራ ጠል ኦሮሞ ነኝ የሚለው የአርሲ ሀድያ ነው። ሶዶ ስሙም የሀድያ ብቻ ሳይሆን የስጋ ዘመዶቹ የሀድያ ካድሬዎችና ባለስልጣኖች ናቸው። እሱ ህወሓት ሲመጣ ሰፋ ወዳለው ኦሮሞ ተጠግቶ የኦሮምያ ፕሬዚዳንት ሆነ። ዶ/ር ብርሀኑ ሌንጂሶ የብሄረተኝነት መጽሀፍ ያሳተመው ወደ ኦሮሞ የተጠጋ ሀድያ ነው። ሀድያ በእሌኒ ግዜ ከጎንደር የሰፈረ በርካታ ጎንደሬ ስላለው እንደነ ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ ከሴማውያን በመወለዳቸው ቀያዬች ብዙ አሉባቸው፣ አባ ዱላ ነኝ የሚለው ምናሴ ከሰላሌ/አማራ ቅልቅል አርሲ የሄደ ዐምሀራ ነው። ህወሓት ምርኮ ኦሮሞ ያደረገው ነው፣ ደመላሽ የሚባለው የፓሊስ አዛዥ አባቱ እናቱም ኤርትራውያን ናቸው፣ ኦሮምኛ ተናጋሪ በመሆኑ ህወሓት በኦሮሞነት እንዲጫወት የመደበው ነው። ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የሻሸመኔ ትግሬ ነው። እስከ ስንት ትውልዱ ቢቆጥር ገብረማርያም ኃይለማርያም ወልደማርያም እንጂ በዘሩ ቶሎሳም፣ ጂማም፣ አይልም አይገኝም። ሺመልስ ያለችውን የሺመልስ እናት አምሓራ ነች ። እነዚህ ሁሉ የኦሮሞን ህዝብ በበታችነት ስሜት በመሸበብ እየጋለቡት ያሉ ናቸው። አሁን እነሱን ተነኩ ብሎ የኦሮሞ ወጣት ለዘር ማጥፋት ተዘጋጅቷል። ይህ የኦሮሞ የመጨረሻው ይሆናል። ኦሮሞ ከሚመጣው ዘር ማጥፋት ሙከራ እኔ ኦሮሞ ነኝ የሚል አይኖርም። ልክ እንደ ሁቱ።
ኦሮሞ እራሱን ለግድያ ከማዘጋጀቱ በፊት እነ አብይ፣ እነ ደመላሽ፣ እነ ወርቅነህ በእናታቸው ይሁን በአባታቸው ኦሮሞ እንደሆኑ ይጠይቅ። ኦሮሞ ለመጣው ሁሉ ወንጀል መፈጸሚያ አይሁን።
__
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ መድረክ ላይ የሚቀርቡ ጽፉፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን ሃሳብ አያንጸባርቁም!
የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡
የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ (የቀድሞው ቲዊተር) ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ







ይህንን ፅሁፍ ያነበበ ሰው ያለ አይመስለኝም ሊኖርም አይችልም ። ፀሀፊው ሰላይ ወይንም የመንግሥት ወሬ አቀባይ ይመስላል ። ስሁፉ ብዙ በማስረጃ የማይደገፉ ሀተታዎችን ያዘለ ነው ። ኢትዮጵያ ስም እንጂ አገር አይደለም ። 72% የኢትዮጵያ ህዝብ የተባለው ማስረጃ የለውም ። ኢትዮጵያ በሚባለው ውስጥ ፣ ከአማራ ህዝብ ውጭ ያሉት ሰዎች በሉአላዊ የጎሳ መንግሥት የሚተዳደሩ ናቸው ። ትግሬና ኦሮሞ ደም አልተቃቡም ። የትግሬና የኦሮሞ ጥል የስልጣን ጥል ነው ። ኦሮሞ ደም የተቃባው ከአማራ ህዝብ ጋር ነው ። አማራንና አማራነትን ለማጥፋት እስካሁን በተደረጉ ሙከራዎች አማራን ያረደውና የአማራን ደም ያፈሰሰው ኦሮሞ ነው ። በኦሮሞ ብሄርተኞች መካከል ያለው ፉክክር ፣ ማን በቶሎ አማራን ያጠፋል ነው ። የቅኝ ገዢና የተገዢ ግንኙነት የሚለውን ከየት እንዳመጣህ አንተ ታውቃለህ ። ትግሬና ኦሮሞ የመገንጠል አላማ ይዘው እስካሁን ቆይተዋል ። የአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል ። ካሁን በኋላ የጁሀርን ወይም የሌላ የቄሮ ቡድን በማንቀሳቀስ የኦሮሞን መንግሥት ማስቀጠል አይቻልም ። በትግሬና በኦሮሞ ተገንጣዮች ሴራ የፈረሰችው ኢትዮጵያ ፣ በአዲስ ህገመንግሥት እንደገና ታንሰራራለች ። የኢትዮጵያ ተስፋ ፍኖ (AFNM ) ነው ።
Explaining Abiy Ahmed’s Moral Authority.
Abiy Ahmed’s regime is characterized by :
1/ Power and legitimacy through Ethnic allegiance and Ethnic loyalty.
2/ Governance through intimidation, terror, and echo chambers.
Deontology can be defined as a theory or a study of moral obligation. According to Immanuel Kant, the morality of an action is based on whether the action itself is right or wrong, rather than on the consequences of the action. The Morality of an action can be determined by asking if its underlying principles could be universalized as a law for everyone. Kant believes that morality is an objective law of reason that applies to all rational beings independent of their personal desires or beliefs. Human action encompasses social, political, and economic spheres of life. Though Immanuel Kant’s theory is focused on the social aspect of human beings, its contribution to the subject of Morality is immense.
Accordingly :
– Abiy Ahmed is irrational.
– Abiy Ahmed has no Moral Authority.
– Abiy Ahmed is immersed in iniquity.
In one of His speech, the president of Oromia Mr. Shimels Abdissa announced that Oromo language is the most spoken language in Ethiopia, and the state of Oromia is in close coordination with the state of Beneshangul, Gambella, and Somalia to expand the reach of Oromo language. He further said: the state of Oromia is building the largest printing company in Africa.
In its face value, the speech looks like developing the Oromo language, which is ok. But, when other issues are considered, the speech is a threat against the Amhara people.
The Amharas have every reason to fight for their survival.
የኦሮሙማው ብልጽግና ፣ ጠላቶቹንና ተቀናቃኞቹን ለማስወገድ በሕቡዕ እና በግልጽ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች በጥቂቱ ፥
– ወጥመድ ውስጥ መክተት
– ፍርሀትን መፍጠር
– ጥርጣሬን መዝራት
– ችግሮቻቸውን ማባባስ
– የጊዜ ፣ የጉልበትና ሎሎች ሀብቶቻቸውን እንዲያባክኑ ማስደረግ
– ግራ ማጋባት
– ማደናቀፍ
– ማስጨነቅ
– ማዘናጋት
– ማዳከም
– አፍ ማዘጋት
– ማዋረድ
– ማታለል
– ማሳሳት
– ተስፋ ማስቆረጥ
– አንድነታቸውን መበታተን
– መቆጣጠር / አቋምን ማስለወጥ
– ወንጀል ማሰራት
– ማስወገድ ።