Homeነፃ አስተያየትየኢትዮጵያ ጸሃይ እየጠለቀች ይሆን? የወያኔና የሻቢያ ጥምረት እንድምታ

የኢትዮጵያ ጸሃይ እየጠለቀች ይሆን? የወያኔና የሻቢያ ጥምረት እንድምታ

Advertisement
World Wide Travel Group

ጥሩነህ ግርማ

የአብይ እብሪትና ድንቁርና ከውጭ ጠላቶቿን እያሰባሰበ ከውስጥ ደግሞ ግጭት እየፈለፈለ ኢትዮጵያን የሞት ሽረት ትግል ውስጥ አስግብቷታል። ዛሬ ግዛቷ ተቆራርሶ በውጭ ሃይሎች ተይዞ በመሃል ደግም እራሳቸውን ለመከላከል በወጡ ታጣቂዎች አብዛኛው መሬት ክቁጥጥሩ ውጭ ሆኖ፣ ህግና ስራዓት ደፍርሶ፣ መሃል አዲስ አበባ የህገ ወጦች መናሃሪያ ሆና፣ አሁንም የአብይና የኦሮሙማው ቡድን ባልተገራ ምላሳቸው በሚተፉት መርዘኛ ንግግር የበለጠ ሃገራችንን እያደሙ፣ እየገደሉ ነው። አንድ ጊዜ ስብሃት ነጋ እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ሲል እንደነበረው ደቀመዝሙሩ አብይም እኔ ከሌለሁ ትፈርሳላች ሲል በድፍረት የተናገረውን እናስታውሳለን። አምስት አመት ሙሉ በጦርነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የሚደነፋው አብይ ገና ስልጣን ላይ እንደወጣ ነው በስልጣኑ የሚመጣ ካለ በደርግ ጊዜ የነበረውን ደም መፋሰስ የልጅ ጨዋታ ነው ያለን።     

የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጣው ኦሮሙማ በአካባቢው በሚፈጥረው ማተራመስ በዙሪያው ያሉ ሃገሮችን እንዲሰባሰቡና እንዲገዳደሩት ትልቅ ስራ ሰርቷል፣ እየሰራም ነው። በተለይ አንድ ጊዜ ወንድሜ ቅብርጥሴ ሲለው የነበረውንና በትግራይ ጦርነት ጊዜም ስቦ ለምኖ ያስገባውን ኢሳያስን ዛሬ ጠላት ማድረጉ በራሱ የሰውየውን ጤናማነት የሚያጠያይቅ ነው። ለነገሩ ክህደት፣ ውሸትና እብሪት ለአብይ ቅርብ ናቸው። ቀርቦ የራቃቸው፣ አንገታቸው ስር ተጥዶ ፍቅር በሚመስል ያሽተታቸውና የከዳቸው የስድስት አምታት ጉዞው የታሪኩ አካል ናቸው።  ባጭሩ አብይ ወዳጅ የማይወጣለት ከሃዲ ነው። አስተዳደግ የበደለው በትነግሳለህ ትንቢት እአምሮው የተበከለ የኢትዮጵያ ጠላት ነው። በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው  እልቂት ለሱ መዝናኛው ነው፣ ሞት ማሾፊያው ነው፣ ለሞቱት ዛፍ እንትከል የሚል አውሬ ነው። ከአውሬ በላይ ነው ማርክ ትዌን ( Mark Twain)  “ of all animals man is the only  one that is cruel. He is the one who inflicts pain for the pleasure of doing it.’   ያለው እንደ አብይ አህመድ ያሉትን ከአውሬ በላይ አውሬዎችን እያሰበ ነው።

 አብይ ዛሬ አሁንስ እግዜር የት እንዳለ ግራ ገብቶናል የሚያሰኝ ጊዜ አድርሶናል፣ ሰው በገጀራ አንገቱ ሲቀላ፣ እርጉዝ ከሆዷ ውስጥ ሽል በካራ ሲወጣ፣ የሰው ልብና ጉበት ሲበላ በድሮን ነፍስ ያላወቁ ህጻናት ሲነዱ፣ እህል ሆን ተብሎ በሳት ሲጋይ፣ ከብቶች በጥይት ሲደበደቡ ህዝቡ ፈጠሪውን ቢጠራጠር ይፈርድበታል? እንዴት አብይ አህመድን የሚያክል ሰይጣን ኢትዮጵያ መሬት ላይ አበቀለ?

ሃገራችን በተላያዩ የታሪክ ወቅቶች ፈታኝ የሆኑ የውጭ ጠላቶች ገጥሟታል፣የወስጥ ችግሮችም እንዲሁ። በየዘመኑ የነበሩት የታሪክ ባለአደራወች እንዳመጣጡ በብላሃት፣ በምክክር አለፍ ሲልም ተዋድቀው ለቀጣዩ ትውልድ አሸጋግረዋል። ትግሉ መስዋትነትን መዳረሻው ያደረገ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በመሞት ህይወትን እየሰራ የዘለቀ ነው። ከወጣት እስከሽማግሌ ከወንዶች እስከሴቶች ሃይማኖትን ሳይለይ ዘርን ሳይቆጥር በየደኑና ሸንተረሩ በአቀበቱና በሸለቆው ባንድ ላይ ክልትም ብለው የቀሩትን ታሪክ ብቻ ነው የሚቆጥራቸው። ይህ የውጭውን ወረራ የተመለከተ ነው። እንደዚህ እየሆነ ነው አንዱ ትውልድ ሞቶ ለሌላው ህይወት እየሆነ ትውልዱን ቀጣይነይ እንዲኖረው ያደረገው። በእርግጥ በታሪክችን በመካከላችን ግጭቶች ነብሩብን ግን ሁልጊዜ መፍትሄው በሽማግሎቻችን ስለነበረ ዙረን እንታራቃልን። የዛሬው ልዩ ነው፣ በጣም ልዩ ነው። አንደኛ ሃገር በቀል የሆነ  በሌለ ትርክት ቂም ያረገዘ ከውነት ጋር የተጋጨ አርመኔያዊ ስብስብ ነው። እርቅና ይቅርታ ሽንፈት አድርጎ የሚውስድ ጠላት ነው። በውሸት ትርክት ተበድላችኋል ተነሱ አመጽ ፍጠሩ ህይወት ባመጽ ነው ብሎ የሚሰብክ፣ ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት እንደ ጨዋታ የሚያይ የአእምሮ ድኩም ነው።  ።   

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የጥላቻ እሬት የተጋተ አእምሮ ፍትህን ማሰብ አይችልም ፣ እኩልነት ስድቡ፣  አንድነት ቀልዱ፣ ፍቅር መሳቂያው ይሆናል። አቢይ አህመድ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጫነው ይህን የጥላቻ ከባድ ሽክም ነው።

በዚህ የጥላቻ ስብከት ቤተክሪስቲያኖች፣ መስጊዶች ተቃጥለዋል አሁንም ድርጊቱ አላቆመም። ሰዎች ካደጉበት ሰፈራቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በመንጋ ፍርድ እኛን አትመስሉም በሚሉ ጎደሎዎች ነው። እልቂቱ ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገ ይሁን እንጅ አትራፊ የለውም። ገዳዮችም ይገደላሉ ፣ በሌሎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ እነሱንም ማሰቃየቱ ምንጊዜም አይቀርም። የኛና የነሱ የማለያየት ስብከት፣ ትርክት ማንንም እንደማይጠቅም እነሱም አጥተውት አይደለም ግን ህዝብን ለማጋጨት የሚሄዱበት እርቀት የትየለሌ ነው። እስካሁን ድረሥ እነሱው አስባስበው በጥላቻ ኮትኩተው ካሳደጓቸው በስተቀር ብዙሃኑ የኦሮሞ ህዝብ ስላልተከተላቸው እልቂቱን በዚያም አካባቢ እየፈጸሙት ነው። በተለይ በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ጭንቅላታቸውን ስላናወዘው ማሰብ እስክሚሳናቸው ይንፈራገጣሉ። የአማራ ባለሃብቶችን ይዘርፋሉ፣ ያስራሉ፣ ይገድላሉ። የአማራ ትምህርት ቤቶችን የያወድማሉ፣ ክሊኒኮችን ያነዳሉ፣ መድሃኒት እንዳይገባ ያግዳሉ፣ የአማራ ሃብት ስለሆኑ ክብቶችን ይግድላሉ፣ እህል ያቅጥላሉ። በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች በመሆናቸው ብቻ በየስርቤቱ ታጉረው ምድራዊ ስዖልን እንዲያዩ ይደረጋሉ። ይህ ሁሉ አማራን ከማጥፋት የመነጨው የዘር ማጥፋት እቅዳቸው ነው። 

በሚያደርጓቸው ዘራፍ ንግግሮቻቸው ስንቱን አማራ በሃረር፣ በአሩሲ፣ በውለጋ በሸዋ እንዳስጨረሱና በአሁኑ ሰአትም እያስጨረሱ ያሉት ከዚሁ የዘር ማጥፋት ብሽታቸው ነው። 

 ጦርነት እንደሱስ የተጠናወተው ኦሮሙማ በተለይ አባወራው አብይ ላለፉት አምስት አመታት ለኢትዮጵያውያን በለጋሰነት የሰጠው ጦርነትን ነው። ለተራበው እህል ማቅረብ ተፈጥሯዊ እአምሮ ቢስነቱ አልፈቀደለትም።     

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከትግራይ ጋር በተደረገው ጦርነት ህይዎቱን ያዳኑትን ኤርትራንና አማራን ጠላት ለማድረግ ምንም ያህል ጊዜ አልወሰደበትም። ከወያኔዎች ጋር የሚያጣላው  ስልጣን እንጅ የአመለካከት ልዩነት በለመሆኑ ጦርነቱን ከረዳቶቹ ጋር አሽንፎም የወያኔ ሃይል ከነትጥቁ እንዲቆይ ሲፈቅድ ከወያኔ በላይ ጠላት የሚለውን የአማራ ህዝብ ማስፈራሪያና ሲያልፍም እረዳት እንዲሆነው በማሰብ የወሰነው ማኪያቬሊ ውሳኔ ነበር። በአማራ ላይ የሚደርሰውን ዘርፈ ብዙ መከራ በወያኔ እርዳታ እንደሚያባብሰው አልፎም አማራ እንዳይነሳ ሆኖ እንዲኮታኮት የነበረው ጽኑ ምኞት ነው። አማራ ለህልውናው ነፍጥ አንስቶ ሲዋጋ ማጠፊያው ያጠረው ኦሮሙማ እንድተናካሽ ውሻ እየተልከፈከፈ በዙሪያው ያሉ ሃገራትን ማተራመሱን ተያያዘው። ምንጊዜም ለሽንፈቱ ከራሱ ውጭ ያሉትን መክሰስ ልማዱ ነው። 

ትናንት ሶማሊያን ዛሬ ደግሞ ኤርትራን መናከስ ጀምሯል። ይህ እብሪቱ ለህልውናዋ መነሳት ያለባት ኤርትራ እንደጠላት ከምታያቸውና ከተዋጋቻቸው ወያኔወች ጋር አብሮ ሊያስልፋት ወድ ሚያስችላት ጎዳና እየተገፋች ነው። ወያኔና ሻቢያ ፍቅር አስገድዷቸው ሳይሆን ለመኖር አብረው መሰለፋቸው የማይቀር ነው። በጦርነት ተሽንፎ  ግን በአብይ የአማራ ጥላቻ እንደታጠቅ ያለው ወያኔ ዛሬ ትክሻውን ነቅንቆ፣ ደረቱን ነፍቶ አብይን ወደመገዳደር የደረሰው ያለምክንያት አይደለም። በአንድ በኩል ኦሮሙማ ከአማራና ከሸኔ ጋር በሚያደርጋው ጦርነት ወታደሩ በሞትም፣ በምርኮም፣ በመክዳትም እጅጉን ተመናምኖበታል። በመሳሪያም በኩል እያተማረከና እየተሸጠም ስለሆነ ከከባድን በአየር ላይ ካሉት መሳሪያወች በስተቀር ወያኔ ከያዘው ጋር ብዙም ልዩነት የለውም። በዚህ ላይ አሁንም ጦርነቱ በሁሉም የአማራ ግዛቶችና በኦሮሚያ ብዙ አካባቢዎች እየተደረገ ነው። ይህ ሃይሉን የበለጠ የሚያዳክመው፣ የወታደሩን የመዋጋት አቅምም ሆነ ሞራል የሚያደቅ ስለሆነ ኦሮሙማ እየደከመ እንጂ እየጠነከረ አይደለም። ይህንን ወያኔ በሚገባ ያውቅል፣ ትክሻ ለትክሻ መለካካትም የዚህ ግምገማ ውጤት ነው። 

የወያኔ እብጠት ከኤርትራ ስጋት ጋር ሲገናኝ ወደትብብር የማይሄዱበት ምክንያት የለም። ኤርትራ ህልውናየን ትላለች፣ ወያኔ ደግሞ ቂምበቀሉን መውጣት ብቻ ሳይሁን ገና ሲፈጠር የነበርውን የመገንጠል አላማ እውን አደርጋለሁ የሚል ስሌት ውስጥ እንደሚገባ መገመት ይቻላል። ከዚያም አልፎ ከኤርትራ ጋር በመሆን አንድ ሃገር እንፈጥራለን የሚለውን የንመለስን ህልም ኤርትራ ፈቃደኛ ከሆንች ለማሳከት መንገድ ይሆናል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን እንወርዳለን ያሉት ወያኔያውያን ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሚሆንላቸው ብዙ የሚያከራክር አይመስልም። የኤርትራ መሪወችም ቢሆን በየጊዘው ከሚደነፋባቸው የአብይ እኩይ ተግባር ነጻ ለመሆን ይህን ሃሳብ አይቀበሉትም ለማለት አያስደፍርም። ዘላቂ ሰላም ለማግኘት ከኦሮሙማ ለመራቅ ትግራይን አብሮ ማሰለፉ አዋጭ አድርገው ሊያዩት ይችላሉ።

ዛሬ ኢትዮጵያ የፈረስች ሃገር ናት( failed state) ህግና ስራት የሉም፣ ሃገር ተቆራርሳ በባለጉልበተኛ( ደቡብ ሱዳን ሰሜን ሱዳን) ስር ወድቃለች። በውስጥም ኦሮሙማ ምንም እይነት ቁጥጥር ወይም የበላይነይ የለውም። ማንም እንደሚያስታውሰው ሶሪያ በአላሳድ መንግስት ስር እያለች የፈረስ ስራት( faileድ state) እንደነበረች የአለም አቀፉ ህብረተ ስብ ያውቀው እውነታ ነበር። ኢትዮጵያ ከዚያ የተለየ ደረጃ ላይ አይደለችም። አሁን ችግሩን የሚያጎላው ውስጥ ለውስጥ ያለው ትንቅንቅ ብቻ ሳይሆን በእርግጥም ከኢትዮጵያ ተቆርሶ ሌላ ሃገር የሚተከል ከሆነ ነው።      

- Advertisement -

ዐብይ እሱ የማይመራት ኢትዮጵያ ብትፈርስ ግድ እንደሌለው ነግሮናል። በወያኔና በሻቢያ ጥምረት የምትፈርስ ኢትዮጵያ የአብይ አቅም ማጣትም አለዚያም በእቅድ ሊሆን ይችል። አብይ መግዛት ካልቻለ የወያኔና የሻቢያን ግንኙነት በማወቅ ሊያፋጥነው ይችላል። ኤርትራን መጣሁብሽ ማለት በስጋት ተሽብባ አጋር እንድትፈልግ ያስገድዳታል፣ ይህ ደግም ተፈጥሯዊ ነው። በህይውት  የመቆየት ትርጉም ይህ ነው፣ ችግር ሲመጣ አጋር መፈለግ። የኦሮሙማው ኦሮሚያን ማዋለድ በዚህ እውን ይሆናል። ሃገርን በማተራመስ ሲመኙት የነበረውን የኦሮሚያ ሪፓብሊክ ከትርምሱ ውስጥ ፈንቅሎ ማውጣት፣ በሰላም መኖር እንዴት ነው የሚቻለው የሚለውን  እነሱም አያነሱት እኛም ለጊዜ እንለፈው።  

በርግጥ ወያኔና ሻቢያ ተጣምረው አንድ ሃገር የሚመሰረቱ ከሆነና ኦሮማም ህልሙን ካሳካ ኢትዮጵያ ዛሬ  failed state ናት ከምንለው በላይ መሆኑን እናያለን። በሰሜን በነዚህ ጥምረት በደቡብ በኦሮሙማ ሪፓብሊክ መካከል ተሰንጎ የተያዘ የአማራ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? 

ኦሮሚያ ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደሚያበቃ የሚያውቅ የለም። ኦሮሙማ ደግሞ ሁሉን ለአኔ ነውና በዚሁ ምክንያት የማያባራ ጦርነት ውስጥ መግባታቸን የማይቀር ነው።  ይህ የኢትዮጵያን መበታተን ብቻ ሳይሆን ማለቂያ የሌለው ግጭት ውስጥ እንኖራለን። በስሜን በኩል ወልቃይትንና የራያን አካባቢ የኛ ነው የሚሉት ሃይሎች ትግራይንና ኤርትራን በማገናኘትና አንድ ሃገር በመሆናቸው የሚተውት አይደለም። 

በሰሜኑና በደቡቡ ሃይሎች ተከቦ ምን ጊዜም ሰላም ሊያገኝ የማይችለው አማራ ዕጣው መዋጋት ብቻ ሊሆን ነው። ይህ ቢሆነኝ ኤርትራ ከወያኔ ጋር ጥምረት አድርጋ የጋራ ሃገር ካዋቀሩ ነው። ከዚያ በመልስ ወያኔ የአብይን መዳከም ተንተርሶ በእብሪት ነጻ ሃገር እሆናለሁ ሊል የሚችልበት አጋጣሚ በአብይ ደካማነት ወይንም ኢትዮጵያን ማፍረስ ካለው ፍላጎት እየተፈጠረ ነው። ፋኖ ያዳከምውን የኦሮሙማ ቡድን ገፍቶ ለመጣል ጊዜው አሁን ነው የሚል የወያኔ እምነት ይኖራል። ይህም ለአማራ ተመሳሳይ አራስ ምታት ነው። ትግራይ ብቻዋንም ቢሆን ተገንጥላ የምናውቃት ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም። በዚሁ አጋጣሚ ኦሮሙማም ኦሮሚያን ቆርሶ ለማውጣት ያለውን ምኞት ለማሳካት ወደ ኋል የሚል አይሆንም። ኤርትራና ትግራይ አንድ ሆኑም ወይም ትግራይ ብቻዋን መገንጠል ለኦሮሙማው ስሌት ለውጥ አያመጣም። ለአማራም የህልውና አደጋ በየትኛውም ቢሆን ለውጥ አያመጣም። ከላይም ከታችም በሚነድ እሳት መለብለቡ አይቀርም። 

ሌላው መንገድ ወያኔ፣ሻቢያና የአማራ ፋኖ በትብብር አብይን ከስልጣን ቢያስወግዱትስ? የሚለው ይሆናል። ኤርትራውያን የጋራ ችግር የሆነውን አብይን ከማስወገድ በዘለለ ሌላ ምኞት ከሌላቸው ለኢትዮጵያ አንድነት የተሻለው መንገድ ይሆናል። የጋራ ጠላታቸውን ያስወግዳሉ፣ ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር በመልካም ጉርብትና ትኖራለች፣ ወያኔም የአብይ ቂሙን ተወጥቶ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርብትን ስራአተ መንግስት አብሮ ያዋቅራል።     

ባጭሩ

  1. ትግራይና ኤርትራ አንድ ሃገር ሆነው  ይወጣሉ?

    2. ትግራይ ብቻዋን ትገነጠላለች?

    3. ትግራይ፣ ኤርትራና ፋኖ የጋራ ግንባር ፈጥረው የጋር ጠላታቸውን አብይንና ኦሮሙማን ያስውግዳሉ?  

ሶስተኛው የሁሉም ጠላት የሆነውን ከማስወገዱም በላይ ለኢትዮጵያ ብቸ ሳይሆን ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ሰላምን መስጠት ይሆናል። በአንደኛውና ሁለተኛው ሊኖር የሚችለው ማቆሚያ የሌለው ጦርነት አይኖርም።ዋናው ጥያቄ ወያኔ ወደቀልቡ መመለሱ ላይ ነው።  ቀልብ አልኩ?

__

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian News – Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

1 COMMENT

  1. ወንድም ጥሩነህ፦

    የኢትዮጵያ ፀሐይ ደምቃ እየወጣች ነው። የትግራይም ሆነ የኦሮሞ ደናቁርት ገዢዎች አጥፊ፣ አውዳሚ፣ አገር በታኝና ሕልውና የለሽ መሆናቸውን የትግራይና የኦሮሞም ወጣት እየተረዳ ነው። በዚህ ላይ አያሌ አገር ወዳድ ጅግኖች አሉን። ኢትዮጵያ ከባድ የአንድነት ፈተና ሲገጥማትም የዛሬው የመጀመሪያ አይደለም። አትስጋ! በአንድነት እንወጣዋለን ! አንተም ድርሻህን ተወጣ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News