Homeአበይት ዜናጋዜጣዊ መግለጫየኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የህግ መከላከያ ፈንድ (ቶሮንቶ) ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የህግ መከላከያ ፈንድ (ቶሮንቶ) ጋዜጣዊ መግለጫ

Advertise Here
Advertise here
ከጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጂት ሲፒጄ ገጽ ላይ የተገኘ

ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የህግ መከላከያ ፈንድ (ቶሮንቶ)

የከተማችን ነዋሪ የሆነው: ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካናዳ የሕግ ባለሙያ ተክለሚካኤል አበበ ሳሕለማርያም ከፌብሯሪ 13 እስከ ፌብሯሪ 24፥ 2025 ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በነበረበት ወቅት አዲስ አበባ ቃሊቲ እስር ቤት በመገኘት ጋዜጠኛ መስከረም አበራን ጎብኝቷል። እንዲሁም ልደታ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝቶ በነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱትን 51  ተከሳሾች የግማሽ ቀን ችሎት ተከታትሏል። የተከሳሾቹ ጠበቆች አስቸጋሪ በሆነና አመቺ ባልሆነ ሂደት ውስጥ ተከሳሾቹን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረትም ታዝቦ አድንቋል።ከታዘበው በመነሳት የተከሳሾቹን ጠበቆች ለማገዝ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ሲደረግ ቆይቶ የሚከተለውን መግለጫ አውጥዋል፡ 

“ተከሳሾች በመረጧቸው ጠበቆች የመወከል፥ አቅም ከሌላቸውም በመንግስት ክፍያ ጠበቃ 

ሊቆምላቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 (5) ይደነግጋል። ብቃት ባለው ጠበቃ መወከል የፍትሕና ርትዕ መሟላት አንዱ መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታ ነው። በኢትዮጵያ ላሉ ፖለቲካ እስረኞች በመንግስት የሚቆም ጠበቃ ለማግኘት ተቋማዊው ነጻነት፥ መተማመኑ፥ ልማዱም፥ ባሕሉም የለም። 

“በዚህ ሁኔታ የነመስከረም አበራ ጠበቆች በጣም በተጣበበ ንዋይ በነጻ ሊባል በሚችል መልኩ የሚሰጡትን አገልግሎት እናደንቃለን። የጠበቆቹን ትጋት ለማገዝ፥ አድናቆታችንን ለማሳየት፥ ሸክማቸውን ለመጋራትና የፍትሕ ስርአቱን እንዲፈትኑት በማሰብ፤ እንዲሁም የተጠናከረ የጠበቆች ማሕበርና የጥብቅና መንፈስ እንዲጎለብት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ በማለም፤ ላለፉት 15  ቀናት ያደረግነውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች ተከላካይ ጠበቆች ገንዘብ የማሰባሰብ ሂደት ዛሬ አጠናቀናል። በዚህ ሂደትም ከአቶ ተክለሚካኤል አበበና አቶ ዳንኤል ጥላሁን የሕግ ቢሮዎች 350,  000 ብር፤ እንዲሁም ከሌሎች 40 ለጋሾች 650, 000 ብር፤ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ችለናል። በዚህ ዙር የተባበሩንን ሁሉ እያመሰገንን፥ በቀጣይም በምናደርጋቸው ተመሳሳይ መርሀ ግብሮች የበኩላችሁን እርዳታ እንደምታደርጉልን እምነታችንን እንገልጻለን።” 

የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የህግ መከላከያ ፈንድ (ቶሮንቶ)

ማሳሰቢያ ፡ በጋዜጣዊ መግለጫ አምድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ከሶስተኛ ወገን የተላኩ እና የኤዲቶሪያል ስራ ሳይሰራባቸው በቀጥታ የሚወጡ ናቸው፡፡
ለመረጃው ትክክለኛነት ቦርከና (borkena.com) ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም። የተገለጹት አስተያየቶች እና እይታዎች የግድ የቦርከናን አመለካከት የሚያንፀባርቁም፡፡

__

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡ https://borkena.com/subscribe-borkena/


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian News – Borkena English

ትዊተር ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News