Homeነፃ አስተያየትበእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ (ከብሩህ ተስፋ)

በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ (ከብሩህ ተስፋ)

Advertisement
World Wide Travel Group
በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ (ከብሩህ ተስፋ)
ከ “ኢትዮጵያ ኢንሳይት” የተገኘ



ከብሩህ ተስፋ

መግቢያ

የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ ከላፉት 50 ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን መጠነ ሰፊ ግድያ፣ መፈናከቀል፣ የጂምላ ጭፍጨፋ፣ ከሰራ መገለል፣ በማንነቱ ተለይቶ የማህበራዊ ጥቅም እንዳያገኝ መደርጉ፣ ሲቶችን በማንነታቸው ተለይተው በተጠና ዘዲ እንዳይራቡና ትውልዱን እንዳያሰቀጥሉ መደረጉ አንሶ ችግሩ በአሁኑ ስዓት አደማሱን እና መጠኑን በማሰፋት ህዝቡን በህልውና አደጋ ወስጥ እንዲወድቅ አደርጎታል።

የአማራ ህዝብ በህልዉና አደጋ ወስጥ ነው ሲባል አንዳንዶቹ ነገሩን በማቃለል የአማራው ችግር ከለሎች የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ተለይቶ የማይታይና የአማራ ሊህቃን ችግሩን እንዳጋነኑት ተደርጎ የሚተረጎምበትም አጋጣሚ እንዳለ መገንዘም አሰፈላጊ ሰለሆነ  የህልውና ትግል ስንል ማን ማለት እንደሆነ በጥቂቱ መዘርዘር ያሰፈልጋል እላለሁ።

ህለውና ትግል ሲባል የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በመኖር እና ባለመኖር ሁናቲ ወስጥ መኖሩን ይመለክታል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ሰንል ደግሞ ህዝቡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የህልወና አደጋ ውስጥ እንዳለ ያመለክታል። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በቀጥታ የህልውና አደጋ ወስጥ ነው ስል ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁን ስዓት የህግ የበላይነት የሚባል ነገር እንደሊለል እና ህዝቡ በበርሃው ሀግ እየተዳደረ እንደሆነ ሁላችንም የምናየው ነገር ሰለሆነ እና ጉልበት ያለው ጉልበት የሊለውን እንደፈለገ አደርጎ በሰሩ አድረጎ ሊገዛው እንደሚችል ያሳየናል። ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮጵያ አገራችን ለላለፉት 35 ዓመታት በዘውግ ፖለቲካ የአገዛዝ ሰር ወድቃ ጉለበተኞቹ የፖለቲካወን ምህዳር እነነሱ እንደፈለጉት አደገው ሰለመሰረቱትና ተሽናፊው እነሱ በአወጡት ህግ ሰር ወድቆ የተባለውን ከማደርግ ውጭ ሊላ ምንም መርጫ የለውም። 

ምክንታቱም ሁሊ አሽናፊዎች እውነትን እነሱ እንደፈለጉት ማሰቀመጥ ሰልሚችሉ። እነሱ እውነት ብለው የበየኑት ነገር ደግሞ ኢትዮጵያ የመቶ ህምሳ ዓመት ታሪክ ያላትና ይህችንም አገር አማራ የፈጠራትና አገሪቱ ውስጥ በሚኖሩ ሊሎች ኢትዮጵያን ላይ አማራው የራሱን  ባህል፣ ወግ፣ ቁንቋ በመጫን የተመሰረትች ሰለሆነች ይህን አፈረሰን ሊላ በብሃር በሃረሶቦች ይሁንታ የተመሰረትች አገር መመሰረት ችለላል ያሉት የዘውገኛ ቡድኖች አሽናፊ ሰልሆኑና ለደረሰው በደል ሁሉ ተጠያቂው አማራ ነው በማለት ለአለፉት 35 ዓመታት መጠነ ሰፊ የሆነ በደልና ሰቆቃ ሰያሰተግድ ቆይቷል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በድሮን፣ በተዋጊ ጀቶች፣ እና በከባድ በሳሪያዎች በመታገዝ ህዝቡን ለቀጥታ ጥቃት በማጋለጥ የህልውና አደጋ ወስጥ እንዲወድቅ በማድረግ ላይ ይገኛል። የህልውናው አደጋ በቀጥታ በቻ አይደለም ጥላውን ያጠላው በተዘዋዋሪ መንገድም የአማራ ህዝብ አደጋ ላይ እንዲዎድቅ ሆኗል። 

በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቃት ሰለባ እየሆነ ነው ሰል ደግሞ አማራወች አማራ በመሆናቸም ብቻ ተለይተው ከሰራ ይገለለሉ ካልሰሩ ደግሞ መሠረታዊ የሆነውን ፈላጎታቸውን እንዳያሟሉ ይሆናሉ። እንደ ህክምና የመሳሰሉ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ይደረጋል። ህክምና ካላገኙ ደግሞ በበሺታ እንዲሰቃዩና ብሎም በተፈጥሮዊ ሞት እንዲሽኙ ይደረጋል። ሲቶች አማራ በመሆናቸም ምክንያት ተለይተው መንግስታዊ ፆታዊ ጥቃት እንዲደርሰቸው ይሆናል፡ እዚህ ላይ 17 የአማራ የዩኒበርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም ብርቱካን ተመሰገንን ማንሳት ተገቢ ነው። እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ተዘዋዋሪ የህልውና አደጋ ሰለባ ሲኮን ደግሞ ሰው ተስፋ በመቁረጥ በራሱም ሆነ በቢተስቦቹ ላይ አደጋ ሊያደርስ ይችላል። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ጨለማ ሆኖ ሲታይ የመኖር ጉጉትን ይሰረቅና  ተበዳዩ ሰው ለመኖር ምክንያት ሲያጣ እራሱን ሊያጠፋ የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ይሆናል። የአማራ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የህልውና አደጋ ወስጥ ገብቷል የምለውም ከለላይ በተጠቀሱት ሁለት ምክንታያቶች እንደሆነብ ልብ ይበሉ።

ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የተወሰኑ የዘውግ ፖለቲካ አራማጆች እንደ ህዝባዊ ወያኒ ሃርነት ትግራይ እና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ደርጂት እንዲሁም አሁን እራሱን ብልፅግና ብሎ የሚጠራው የአበይ አህመድ የግል ኩባንያ የመሳሰሉት ደርጂቶች በትረሰልጣኑን ሰለያዙትና ጠላት የሚሉትን አማራን እና ኢትዮጵያን በማፈራራረስ የረሳጨውን አገረ መንግስት ለመፍጥር እንዲችሉ እንቅፋት ነው ያሉትን ማንንም ሃይል ለማጥፋት ወደሁላ እንደማይሉ ለአለፉት በዙ ዓመታት እያያየነው ያለ ጉዳይ ሰለሆነ ለሁላችንም ግልፅ ነው።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ይህ እንዲሆን ደግሞ ትዉልዱን በጥላቻ በማሳደግ ጨካኝ እና አረመኒ እንዲሆን አደገውታል። ይህ በጥላቻ ያደገ ወጣት ደግሞ ምን ሊያደግ እንደሚችል በግዚው አቶ ለማ መገርሳ ነግረውን ነበር። በሁላም ያየነው አማራውን ከወለጋ ከአርሲ ከምእራብ ሺዋ እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ተብየው እየትጨፋጨፍና እየተፈናቀለ መሆኑን እያየነው ያለ እውነት ነው።

የዚህ አይነት ዘውግን ማእከል ያደረገ ጥላቻ እና ግፍ እንዲሁም የዘር ማጥፋት በጀርመን ናዚ እንዲሁም በሩዋንዳ ተከሰቶ እንደነበረ እና ይህንም ተከትሎ ብዙ ህዝብ እንዳለቀና አለምም ከዚ ተምሮ የተረጋጋች አለምን እንድትመጣ እንሰራልን እያሉ በ21 ምእተ አለም በእኢትዮጵያ የጀርመንን የመሰለ የህዝብ ጭፍጨፋ እያየ በዘምታና በአርመሞ ማየቱን መርጧል። ምክንያቱም ምእራብያዊያንም ሆነ ለላወ የአለም ህዝብ የሚሰቀደመው ጥቅሙን እንጂ ሰባዓዊነትን እንዳልሆነ ልብ በሉ። 

Viktor Emil Frankel የተባለ የሰነ ልቦና እና የሰነ አእምሮ ሃኪም የነበረ አይሁዳዊ በጀርመን ናዚዎች ከ እነ ቢተሰቡ ማለትም ሚስቱ፣ ወላጆቹ እና ወንድሙ በ 1942 በTheresienstadt የማጓሪያ ካምፕ ወስጥ እንዲት እንዳሳለፈና አብረውት የታሰሩ ቢተሰቦቹ ሁለ በዚያ ሲያልቁ እሱ በቻ በሂዎት እንደተረፈ እና ከዛ በሁላ የሂወትን ተርጉም አጥቶ ተሰፋ በመቁረጥ ወስጥ እንደነበረ psycology and existans በሚለው መፅሁፍ አንብቢያሉሁ ከዛ በሁላ ግን ለሊሎች መኖርን እና ሊሎች እሱ እንደገጠመው እዳይገጥማቸውና ከገጥውማቸውም እነሱን መርዳት እንደሚችል በማሰብ ለመኖር ምክያት በማግኘቱ በተፈጥሮ እስኪሞት ዽረስ Lego terapy የሚባለውን የሰነልቦና የህክምና ዘዲ በመጠቀም ብዙ ሰወችን ሲረዳ ቆይቷል።

ይህ ከላይ የጠቀስኩት ታሪክ የአማራና የይውህዳውያን ጉዳይ እንዲት እንደሚመሳለና ታሪክም እራሱን ሲደግም አለም በዝምታ የሚያየው ጉዳይ መሆኑ ነው። በጀርመን የአርያን ዘር የበላይነትን ለመሰረት እንድ ወጥ(homogenes) የሆነ የአርያን ዘር ለመፍጠር ጥቁሮችን፣ አይውዳውያንን እና ጂፕሲዎአችን እንደፈጀው ሁሉ በኢትዮጵያም በአሁኑ ሰዓት ከአማራ የፀዳች ኦሮሚያን ለመመስረት ለማስቻል አማራወችን፣ ጉራጊወችን እና  ኢትዮጵያዊያንን በመጨፍጨፍ ነፅ አገር የመመሰረት ስራ ላይ እንደተሰባሩ እያየን ያለው እውነታ ነው።

- Advertisement -

የወጣት ብርቱካን ጉዳይ

ከላይ ያለውን ለመግቢያ ያህል ካልኩ ዘንዳ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ። ሰሞኑን በልጃችን እና በህታችን በወጣት ብርቱካን ተመስገን የሂወት ገጠመኝ ዙሪያ በEBS ከተላለፈ በሁላ ኢትዮጵያውያን ተመለከቱና ጉዳዩን በሰፋት ማውገዝ በመጀመራቸው አገዛዙ ድንጋጢ ውስጥ ይገባና የEBS ሰራተኞችንን እና ብርቱካንን በማሰር የሺብር ክስ መሰርቶባጨዋል። ምክንያቱ በአማራ ህዝብና በአማራ ሲቶች ላይ እየደረሰ ያለው አፈናና ፆታዊ ጥቃት መንግስታዊ ሰለሆነና ብርቱካንም በዚህ የtelevision ጣቢያ ቀርባ የሆነውን አዲስ መእራፍ በሚባለው እና ድሆችን እንዲረዱ በሚያስችለው የEBS ክፍል ቀርባ የሂዎት ታሪኳን እና ገጠመኞቿን ሰተናገር አገዛዙ የሚይዘ የሚጨብጠው ነገር አጥቶ በደመነ ነብስ የእውር ድንብሱን በtelvison ጣቢያውም ሆነ በበርቱካል ላይ በሁላም በአንድ መንግስት ተብየ ሊተዎን የማይገባና በጣም ያልበሰለ ዘጋቢ ፊልም በመሰራት እውንቱን ህዝብ እንዳያውቀው በሚዲያወቹ አማካኝነት ረብርቡን ተያይዞታል። ይህ የሆነው በዕለት 23/03/2025።

ይህ ይሆን ይረዳው ዘንድ ብዙ ሰዎችን በማሰባሰብ ገንዘብ እና ማሰፈራት ጨምሮበት ለዚህ የትወና ዘጋቢ ፊልም እንዲሰራ አሰገድዶታል። ይህም አገዛዙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጉዳዩ ውስጥ ሰላለበት እውነትን ለማፈን እና ህዝቡ እውነቱን እንድያውቅ በማድርግ በብርቱካን ላይ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ከችግሮ በላይ በሃሰት በራሷ ጉዳይ ላይ እንድትመሰክርና በEBS ቀርቢ የተናገርኩት ሁሉ ሰህተት ነው ለሊሎች የፖለቲካ ጥቅም ተብሎ እንድተውን ታዝዥ እንጂ የተናገርኩት ሁሉ ውሽት ነው ብላ እንደትናገር በማሰገደድ አገዛዙ ምን ያህል ጨካኝና አረመኒ እንደሆነ ማሳያ ነው። 

ይህ አልብቃ ብሎ ደግሞ ብርቱካን ትዳር እንደነበራት ልጇንም በትዳር እንደወለደችውና እንዳለተደፈርች የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በመሰራት ይህ እውነት እንዲመሰል ደግሞ ሰዎችን በገንዘብ በመግዛት እና በማስፈራራት በተውኒቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ምን ያህል በተሳታፊዎችም ላይ የሞራል መልሽቅ ሰለባ ተጎጂ እንዲሆኑ ማደርግ እንደቻለ ማሳያም ነው።

ሰው ተገዶ እና ዋሺቶ በሊሎች ላይ እንዲመሰክር ማድርግ በተሳታፊዎቱ ላይ የሞራልም ሆነ የፈርሂ እግዚአቢር አልባነትን ውስጥ በመጥል ለዘውትር ፅፅት እና ሃዘን እንዲዳረጉ መንግስታዊ ጥቃት  መፈፀም ችሎል።

የመንግስት ቀዳቂ ሃላፊነት የዚጎችን ደህንነትና ሰላም መጠበቅ ሆኖ ሳለ ከአደጋ ሊጠበቅህ የሚገባው ሃይል እራሱ እንዲት የህዝቡ ህልውና ሰጋት ምንጭ እንደሆነም ማረጋገጥ ተችሎል።

እዚህ ላይ መጠየቅ ያለበት ጥያቂም አገዛዙ ለምን በዚህ ደረጃ ከወትሮው በተለየ መልኩ ሊደናበር ቻለ? እንደ እኒ አመለካከት የአገዛዙ የፈርሃት ምንጭ ይሆናንሉ የምላቸወን ነጥቦች እንደሚከተለው አቀርባቸዋለሁ።

1ኛ. አገዛዙ በበርቱካን አፈና ጉዳይና በደረሰባት ግፍ እጁ እንዳለበት የሚያሳይ ፍንጭ ብርቱካን በቃለ መጠይቋ ጠቅሳለች። ይህወም መጀመሪያ ሰትያዝ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ወስጥ እንደነበረችና ሰትያዝም የደንብ ልብስ የለበሱ የአገዛዙ ወታደሮች ጥይት ሲተኮስ እነሱ ወዳዘጋጁት መኪና እንዲገቡ በማድረግ ወደ አልታዎቀ ጫካ እንዶሞሰዷቸውና  ከምኒው የደንብ ልብሳቸውን ቀይረው ጭንብል በማጥለቅ እንደመጡ ብርቱካል ተናግራላች። ይህ አባባል አገዛዙ እጁ እንዳለበት የሚጠቁም በመሆኑ።

2ኛ. ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንደሚባለው ብርቱካን በቃለ መጠይቋ ውስጥ አንድም ግዚ የተማረችበትን የዩኒቨርስቲውንም ሁኖ ዩኒቨርስቲው የሚገኝበትን ክልል ሰም አልጠራችም። ይህ ባልሆነበት ጉዳይ ላይ ለም የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ በጉዳዩ ላይ መግለጫ መስጠት አሰፈለገው? ምን አልባት አገዛዙ የብርቱካንን ሙሉ የቃለመጠይቅ መረጃ ከEBS አግኝቶት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም EBS ለእራሱ ፕሮግራም የሚጠቅመውን ብቻ ቆርጦ ሊያቀርብ እንደሚችል ግምት ውስጥ በማሰገባት»

3ኛ. ከEBS ሊወስደው ይችላል ብየ በምገምተው ሙሉ መረጃ ወስጥ የ17ቱ የእደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረጃው ተነካክቶ ሊሆን ሰለሚችልና በሊሎች ምክንያቶች አገዛዙ እውነቱ ወጣ ብሎ በመደናበር ይህን ዘጋቢ ፊልም ሊሰራ እንደተገደደ እና ሊደናበር እንደቻለ ነው የሚገባኝ።

የብርቱካን ታሪክ እውነት ነው። ወጣቷ የገጠማትን ተናገራለች። ለምንስ መዋሽት አሰፈልጋታል? ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ስዓት እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ብርቱካን ካለችው እውነታ ጋር የሚጋጭ ነገር አለውን? አይጋጭም እትዮጵያ የምድር ሲኦል የሆንችበት ግዚ ነው ብል የሚቃዎመኝ ይኖራል ብየ አላሰበም። ምክንያቱም እውነታው እሱ ሰልሆነ።

በበርቱካን እና በአገዛዙ ላይ ያለውን የሃይል ሚዛን እናጢን።

ወጣት ብርቱካን ደሃ፣ ምንም ዘመድ የሊላትና መሰረታዊ ፈላጎቷን ማሟለት የተሳናት ማስኪን ሰትሆን ከዚህ ጋር ተዳምሮ ደግሞ ከደፋሪዋ የወለደችው በሺተኛ ህፅን ልጂ ያላት ሲሆን በደረሰባት ግፍ ምክንያት የሰነልቦ ችግር ወስጥ የምትገኝ ስትሆን ወደ EBS ያስኪዳትም ምክንያት እርዳታን ለማግኝት ነው። ታዲያ ይች ምስኪን ወጣት ከርዳታ ውጭ ምን ለማግኘት ብላ ነው ከመንግስት ጋር ግብ ግብ የምትገጥመው? አማራ ሰለሆነችና እውነቱን ለህዝብ ማሳዎቅዋ ነው ጥፋቷ። የአገዛዙን ግፍ፣ ፍርሃት እና ጭካኒን ልብ ይበሉ።

የአገዛዙን ሃይል ደግሞ እንመልከት። የሚዲያ ሰራዊት ያለውና እውነት በውሽት ሊቀይር የሚችል ህይል ያለው፣ ወታደር ያለው ሲፈልግ የሚደፈር ሲፈልግ ደግሞ የሚያግት ሁሉንም ማደረህ የሚችል፣ ገንዘብ ያለው ለዘጋቢ ፊልሙ ግባዓት የሚሆኑ ሰዎችን በማሰፈራራትም ሆነ በገንዘብ በመግዛት እውነትን በውሽት መቀየር የሚችል። ታዲያ የብርቱካንና የአገዛዙ የመጫቆቻ ሚዳ እኩል ባልሁነበት ሁኒታ ውስጥ እንዲት ነ እውንትን ፈልጎ ማግኝት የሚቻለው? ይች አለም ፍትሃዊ አለመሆኗን ልብ ይበሉ።

ታዲያ ይህ ሆኖ እያለ ለምን ይሆን አንዳንዶቻችን የብርቱካን እውነት መቀበል የተሳናቸው?

ህበረተሰብን በማስፈራራት፣ በግደል፣ በማሰር በማግለል እና ጥፍንጎ በመያዝ እውነትንና ሞራላዊ ዚጋን መፍጠር ይቻል ይሆን?

እንደ እኒ አገዛዙ ይህን የመሰለ ጥፍነጋ በማድረግ ትንሺ እድሚ ያራዝም ያደርግ ይሆን እንጂ እውነትና ንጋት ውሎ አድሮ መውጣቱ አይቀሪ ነው።

የአገዛዙ ፈላጎት ጥፍነጋውን በማክበድ የዚጎችን እለታዊ እንቅስቃሲ በፈርሃት የተሞላ በማደረግ ፍርሃትን እንድንለማማድ በማድርግ ስራአቱን ማራዘም ነው የሚፈልገው። ይግ ግን በፍፁም ሊሆን እንደማይችል የእኛም አገር ሆነ የአለም ታሪክ የሚያሳየን ከዙህ በተፃራሪ ነው።

የሃገሪቱ አንጡራ ሃብት የፈሰሰባቸው የመገናኛ ብዙህን ጣቢያዎች የአብይ አህመድ የግል ንበረት በመሆን ለአገዛዙ በማደር የእውነት መጨፍለቂያ መሳሪያ መሆናቸውና በዚህ ተቋም ወስጥ የሚሰሩቱም ጋዢጠኞች ሞያቸውን ወደ ጎን በማለት ምንም አይነት ሞያዊ ኢቲክ በሊለው መልኩ የአገዛዙ እረጂም እጂ በመሆን እንደ ወጣት ብርቱካን በመሰሉ ወጣቶች ላይ የአገዛዙ በትር እንዲያርፍባቸው በማደርግ በእውነት ደፍጠጣ ተግባር ላይ በሳተፍ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ መዘንጋት አይገባም። ባይበላስ ቢቀር?

ኢትዮጵያዊያን ግን ምን ነካን? ለምን ዚጎቻችን፣ እህቶቻችን፣ አማራወች እና በአጠቃላይ በሰው ልጂ ላይ ብርቱካን የመሰለ ጥቃት ሲፈፅም ዝምታን መርጥን? 

ይህ ዝምታችንስ በወደፊቱ አብሮነታችን ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አሉታዊ ነገርስ ግምት ወስጥ አስገብተናልን?

ለምን ያ በውስጣችን የነበርው ፈርሃዊ እግዚህዓቢርንትስ የት ተነነ? ወይንስ ስናስመስል ነው እንጂ ከመጀመሪያውም እራስ ወዳድድና አሰማሳዮች ነበርን?

በዚህ ዝምታ ውስጥ ሆነንስ እንዲትና እስከመቸ ነው የምንገፋው?

ፍርሃት በራሱ ምንድን ነው? ለምድነውስ የምንፈራው? እንዳንሞት? ምኑ እንዳይቀር? ሰቀቀኑ፣ መታረዙ እና መታሰሩ? የቁም ሞት የተባለውንስ ነገር እንዲት ነው የምናየው?

የቁም ሞት ማለት እንደ እኒ አረዳድ የእየ አንዳንዳችን ክብር ሲነካ፣ ዚጎች ሲበደሉ በአቅመ ቢስነት ዝም በሎ መመልከት፣ ማህበራዊ ፍትህ ሲጎደል ምንም አለማድረግ እና እራስክን አለመሆን ሊሎች በእኛ ሂዎት ላይ ገብተው የፈቀዳቸውን እንዲያደርጉ ስንፈቅድላቸው እና በራስህ እንዲደርስ እማትፈልገወን ነገር በሊሎች ሲደርስ ዝም በሎ መመልከት የመሳሰሉትን እንደ የቁም ሞት ነው የምቆጥራቸው። 

ከላይ ያነሳሁቸውን ህይዎትን እና ሞትን በንፅፅር የሚያሳዩ ሰልሆነ ሁላችንም በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ እደንዎያይባቸውና ግልፅነት እንድንፈጥር ብናድርግ በማለት በትህትና አሳሰባችሁ አለሁ።

ወደ በርቱካን እና አገዛዙ ወደ አዘጋጀው ዘጋቢ ፊልም እንመለስ።

እስኪ እወነት ወይንም እውቀት የተባሉትን ነገሮች እንዲት ነው የምናያቸው? ይህን ለማየት በዘርፉ ያሉትን ሳይንሳዊ ቲየርዎችስ ምን ይላሉ?

አገዛዙ እውነትን ለመፍጠር የሂደበትን መንገድና EBS እውነትን ለማግኘት የሃደበትን መንገድ ሳይንሳዊ ዘዲዎችን ተጠቅመን እንመልከት።

በዚህ ፅሁፍ ወስጥ ላቀርብርው የፈለኩት ሁለት እውነትን መመልከቻ ሳይንሳዊ እና ፍልሰፍናዊ እይታወችን ይህናል። ይህን ላደርግ የፈልኩበት ምክንያት አገዛዙ እንዲት አደርጎ ነው የብርቱካን እውነት መቀየር የፈለገው እንዲትስ አደርጎ ውሽትን እውነት አደርጎ ለመፍጠር እየሞከረ እንዳለ እና የብሩካንስ እውነት ምን ይመሰላል የሚለውን ለማየት ሁለቱ የእውነት ማፈላለጊያ መንግዶችን እናያለን።

የመጀርመሪያው ሳይሳዊ ቲዮሪ Socialconstructivisme የሚባለውና በአማርኛ ማህበራዊ ስሪት ይመስለኛል የሚለውን ሲሆን በዚህ ሳይንሳዊ መንገድ በመጠቀም አገዛዙ እውነትን በዚህ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲት እንደፈጠረ እናያለን። በዚህ ሳይሳዊ እሳቢ እወነት የሚባል ነገር የለም እውንት አንፃራዊ ነው ይላል። አንድ ነገር እውንት የሚሆነው እውነት እንዲሆን የሚፈልገው ሰውየ እውነት ነው ብሎ ሲያምን ነው ይላል። እውነትን ለመፍጠር ደግሞ ቋንቋ እና ሚድያ አሰፈልጊ ናቸው። በሚዲያው አማካኝነት ጉዳዩን በመደጋገም በህበርተሰቡ ዘንድ የአሰተሳሰብ እይታን በመቅረፅ እውነትን እነሱ በሚፈልጉት አይነት  ይፈጥራል ማለት ነው። በዚህ ሳይንሳዊ አረዳድ መሰረት እውነትን ሰዎች ተሰባሰበው የሚፈጥሩት ነገር ነው እንጂ እውነት በራሱ እንደሊለ ነው አሰተምህሮቱ ይናገራል። ሰልዚህ እውነት ባህበራዊ ስሪት ነው ማለት ነው።

ይህን ትየሪ በመጠቀም አገዛዙ እንዲት አደርጎ የበርቱካንን ታሪክ እንደሰራ እንመልከት። የብርቱካንን ዘጋቢ ፊልም ለመሰራት አገዛዙ የተጠቀመባቸውን ግብዓቶችን እንመልከት።

1ኛ. ይህን ዘጋቢ ፊልም ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎችን ማሰባሰብ። በግድም ሆነ በገንዘብ በመደለል።

2ኛ. ሊሰራ የተፈለገውን ታሪክ ለሰዎቹ ማሰጨበጥ። ትወናውን በደንም እንዲሰሩ ማዘጋጀት።

3ኛ. ሚዲያ እና መዋለንዋይ በማፍሰስ። ይህ ሊተረክ የተፈለገውን ታሪክ በሚዲያ አቀነባብሮ በመደጋገም እውነቱ እንዲሽፈን በማድረግ ውሽቱን እውነት አደርጎ ለህበረተሰቡ በማሰጨበት በዚህ መልኩ የነበረወን እንዳልነበረ በማደርግ አዲስ እውነታ መፍጠር ይህ ነው አገዛዙ የአገሪቱን ሃብት በመጠቀም አንዲት ምስኪን ወጣትን የዘውግ ፖለቲካ ሰለባ ያደረጋት። ማፈር ይገባናል ይህ እንዲሆን ሰላስቻልነ።

ሁለተኛው ሳይንሳዊ መንገድ ደግሞ EBS የተጠቀመው ሲሆን ቲዮሪውም Fenomology ይባላል። በዚህ ትየሪ አሰተሳሰብ ደግሞ እውነት የምትገኘው ከተራኪው ነው ይላል። ምክንያቱም የሆነውን የሚያውቀው ተራኪው ነው ሰልዚህ ጠያቂው እውነትን ለማግኘት የሚያስችሉትን የአጠያየቅ ዘዲ በመጠቅም ታሪኩን ተራኪው የገጠመውን እንዳለ በመናገር የደረሰበትን እውነት ለጠያቂው ይናገራል። 

እዚህ ሂደት ወስጥ ሁሉን አዋቂው ተራኪው ሲሆን ጠያቂው ሳይጠራጠር እና ፈራጂ ሳይሆን ተራኪው እውነቱን እንዲያዎጣ የሚያስችል የአጠያየቅ ዘዲ ይከተላል። ይህ ትየሪ ሰብዓዊ ከሚባለው የፍልሰፍና አሰትምህሮ የሚመነጭ ሲሆን ተራኪው የሆነውን በመናገር እውነቱን ለጠያቂው ወይንም ለቲራፒስቱ ያሰረዳል። ተራኪው የተጎዳና በችግር ወስጥ ያለ ሰልሚሆን ተራፒስቱ ወይንም ጠያዊው በታሪኩ ፈሰት ውስጥ የተራኪውን በጎ ነገር በመመዝገብ ለተራኪው አጉልቶ በማሳየት ተራኪው ችግር ብቻ ሳይሆን በጎ ነገርም በወስጡ እንዳለ ለተራኪ በመንገር የተረኪውን ጠፍቶ የነበረ ተስፋ እና የሂዎት ተርጉም እንደገና እንዲብብ በማደርግ ከደረስበት ችገር እንዲያገገም የሚያሰችል ትዮሪ ነው።

ይህን ከላይ የጠቀስኩትን ትየሪ እኒ እንደተረዳኝ የEBS ጋዚጠኞች የተጠቀሙበት ይመሰለኛል። የዚህ ፕሮግራም አላማ የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ቀርበው ያጋጠማቸውን ችግር በመንገር ክድርጂቱም ሆነ ፕሮግርሙን ከተመለከቱ በጎ ኢትዮጵያዊያን እርዳታ እንድታገኝ ማሰቻል ነበር። ይህም ነው የሆነው። አማራ እና ደሃ እማይወደው የብልፅግና አገዛዝ ግን ይህን ሰባአዊ ደርጊት በመጥፎ በመተርጎሙና ከዚህ ከላይ ከተገለፅው አላማ ውጭ በመተርጎም ብርቱካንንም ሆነ የኢቢስ የተልቭዥን ጣቢያ ላይ እርምጃ እንዲዎሰድ አስችሎታል። 

__

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡ https://borkena.com/subscribe-borkena/

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

4 COMMENTS

  1. ወንድም ብሩህ፦
    ይህ ነው የሚባል ገንቢ አገራዊ ዓላማና ተግባር ያልነበረውና ያላሳየው (መሬት ላራሹ እንደሆነ እንኳን በደርግ ጊዜ ዛሬም አልተሳካም። የትርፍ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅም የጠቀመው ባብዛኛው ካድሬና የፓርቲ ጀሌ ነው።) ደርግ በዕድገት በሕብረት ካዘመታቸው ተማሪዎች አንዱ የባሌ ክፍለ ሀገር ወንድ ዘማች እንዲህ ብሎ ገጥሞ ነበር፦
    ዘፍነን አዘፍነን ባመጣነው ዕዳ
    አንቺ እንጨት ልቀሚ እኔም ውሀ ልቅዳ።
    ይላል። ገጣሚው አማራ ነው። የከተማ ሰዎች መልዕክቱ ስለማይገባቸው ላብራራው። በገጠሪቱ አገራችን ዱሩ ነብር፣ ጅብ፣ እባብ፣ ዝንጀሮና ሌላም አውሬ ስላለበት ለሴት ልጅ አደገኛ በመሆኑና እንጨት የሚለቀመውም ከዱር በመሆኑ፣ ሴቶች እንጨት አይለቅሙም፤ የወንድ ሥራ ነበር። አንዱ የሴት የሥራ ድርሻ የመንደር ሕዝብ መሄጃ በሆነውና ሰው ምን ጊዜም በሚሄድበት መንገድ ላይ ሄደው ከወንዝ ውሀ መቅዳት ነበር። በደርግ ዘመቻ ወቅት ግን፣ አንዱ ዋና የአብዮት ዓላማ ባህል ማፍረስ/መሻር ስለነበር፣ ሴትም ወደ ዱር ሄዳ እንጨት መልቀሟም አንዱ የለውጥ አካል ተደርጎ በግልቡና ራስ አጥፊው ትውልድ ዘንድ ተወስዶ ነበር።

    ዛሬ ያለንን ችግር የቀፈቀፍነው እኛው ራሳችን ነን። ከታሪክ መማር አቅቶን፣ አገራችንን ባግባቡ ሳናውቅና በ1960ዎች የነበረችው ኢትዮጵያ በስንት ዜጎች ደምና አጥነት እንደተገነባች፣ ስንቱም ላገራቸው ሲዋደቁ በየዱሩና በርሃው መውደቃቸውን ሳናስተውል፣ ኤርትራ በስንት መስዋዕት ወደ እናት አገሯ እንደተመለሰች ሳናገናዝብ፣ በቅናት፣ በምቀኘነት፣ በበቀልና በግልብነት ያለውን ለመዝረፍና የገነቡትን አስተዋይ መሪዎችና ሰዎች ለመግደል፣ ተተኪ የውድመትና የጦርነት አዙሪት መፍጠር ሳይሆን የዕድገት ዓላማም ሆነ አቅም ሳይኖረንና ሳንዘጋጅ፣ ለአገር ጥበቃ በገዛንላቸው መሣሪያ ደናቁርት እየተጋደሉና እየገደሉን አብዮት በሚባል ዕብደት ውስጥ ገባን። ዛሬም ችግር ውስጥ ያለነው ካለፈው ምንም ባለመማራችን ነው።

    በአድዋ ጦርነት ጊዜ፣ የጣሊያን ጦር ሲመጣ አባ ዳኘውም በቂ መሣሪያና አገር ወዳድ ህዝብ ከጎናቸው በሕብረት ስለቆመ፣ ወራሪውን ድል ማድረግ ችለው ነበር። በራሱ መሣሪያ የወረረን ጣሊያን 40 ዓመት ሙሉ ራሱን በሰማይና በምድር የጦር መሣሪያ አሳድጎ ዳግመኛ ሊወርረን ሲመጣ እኛ የቆየነው ከሞላ ጎደል የአድዋውን የአባ ዳኘው መሣሪየ ተሸክመን፣ የዛሬ 2000 ዓመት ያገኘነውን ሞፈር ቀንበር ሳንለውጥ ያው እንደተለመደው በየጎጇችን ውስጥ ተሸጉጠን፣ ጣሊያን በሰማይና በምድር ሲገድለን፣ መቋቋም አልቻልንም። አሸነፈን። እንደ 19ኛው ክፍለ ዘመን ጃፓን በቁጭት አልተዘጋጀንም። ዛሬማ ጣሊያን ከመሬት ለቅቃ የጠፈር ውጊያም አቅም አላት፣ እኛም እዚያው መሬት ላይ በጎጇችን ውስጥ መኖር እንኳ ከብዶናል። ይህ ኋላቀርነት፣ ሆዳችን እስክሞላ ድረስ፣ መሪዎቻችንንና ተማርሁ የሚለውን ትውልድም የሚቆጭ አልሆነም። ዛሬ የምናየው ዋይታ የዕኛው ድንቁርናና ራስ ወዳድነት ውጤት ነው። መድሐኒቱ ዘር፣ ሃይማኖት፣ መንደርና ሥልጣን አምልኮውን እርግፍ አድርገን ወርውረን ለአገር በጋራ መቆም ነው። ሌላው ቀርቶ ዛሬ ለአማራ ሕልውና ሕይወቱን ለመስጠት የወሰነው ቆራጡና ጀግናው ፋኖም ስንት ውትወታ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እየተደረገበት ፈጥኖ አንድነት መመሥረት ያቃተው የለመድነው የ3000 ዓመቱ ጠባብ (short-sighted) የራስ ወዳድነት በሽታ ቀፍድዶ ስለያዘውና ከዚያ የባህል ዕሥር ቤት መውጣት ስላቃተው ነው።

    የዛሬው እልቂት ዘር አይለይም። የዛሬው ዋይታ ሁሉንም ዘር ይመለከታል። ልብ ብንገዛ፣ ሰፊ ለም አገር፣ አያሌ ወንዞች፣ ብዙ ማዕድናትና በሚሊዮን የሚቆጠር ሥራ ፈት ወጣት እያለን፣ ባግባቡ አገር ተመርታ ወደ ሥራ ብንገባ ነገ አውሮጳን የማንስተካከልበት ምክንያት የለም። ወገኖቻችን በአሜሪካ ዕድገት መሪ ተዋናይ ከሆኑ፣ ኢትዮጵያም ያው አቅም የማይኖርበት ምክንያት፣ ራሳችን ድድብና መርጠን፣ ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከመቶ 97 እንዲወድቁ በማድረጋችን በአገር ሕልውና ላይ በመቆመራችን፣ ለትምሕርት፣ ለግብርናና ለተዛማጅ ልማት ትኩረት በመንሳታችን፣ በተለይም ከአብሮነት ይልቅ ክፍፍልና መጋደል በመምረጣችን፣ ክ1000 ጎሣ በላይ የሚኖርባት አሜሪካ በሰላም መኖሯን አለመገንዘባችን፣ የተሻለ የአስተዳደር ሥርዓት እያለና መኖሩንም እያወቅን፣ ለጠባብ ቡድን ጥቅምና ሥልጣን መንበርከካችን ከሰው ዘር በታች አውሎናል።

    ራሳችን ከፈጠርነው ውድቀት የምንወጣውም በራሳችን ጥረት እንጂ በሌላ አካል ሊሆን አይችልም። የኔልሰን ማንዴላን የ 1982-1986 አገር ወዳድ አርዓያ ከመከተል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም። ራስ ወዳድነቱንማ ይኸው ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ ያየነው ነው። ከሕብረት ተግባር ውጭ፣ በየአህጉሩና በየመድረኩም መሰዳደቡም ሆነ ማልቀሱም አንድም ፍሬ የለውም።

  2. ለምን ያለፈው ተግባራችን ለዛሬው ኮምዛዛ ፍሬ መንገድ ቀዳጅ እንደሆነ የሃገሬ ሰዎች በተለይም ነቅተናል ተምረናል የሚሉት እንደ ማይገባቸው አይገባኝም። ደርግ ንጉሱን በስልት አሽቀንጥሮ ያተረፈው ትውልድን መፍጀት ነው። To kill a generation: The Red Terror in Ethiopia and Red Tears እና ሌሎችንም የሰቆቃ መጽሃፍት ላነበበ ያለፈው ዘመን የሚዘመርለት ሳይሆን የሚቆዘምበት እንደነበረ ነው። መሬት ላራሹ አራሽ ሳይሆን የፈጠረው አራሹን ነው ያስገደለው። ባጭሩ ግፍ ሞልቶ የፈሰሰበትን ያንን የ 17 ዓመት የወታደር መንጋ ዘመን ዛሬ ላይ የሚያወድሱ ካሉ ህመምተኞች ናቸው። ትሻልን ትቼ ትብስን እንዲሉ ወታደራዊው መሪ ሲፈረጥጥ ወያኔና ሻቢያ የሃገር መሪዎች ከሆኑ በህዋላ የተፈጸመው በደል ሁሉ ከበፊቱ የቀጠለና በተለይም በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በክልል የተሰመረ እልቂት በመሆኑ ግፉን ከደርግ ዘመን ያከፋዋል፡፡ የሃገሬ ልጆች በልጅነታቸው ሳይቧርቁ፤ የእናትና አባት ፍቅር ሳይጠግቡ፤ አያትና ቅድመ አያቶቻቸውን ሳይውቁ በተናጠል በመከራ የሚናውጡባት ምድር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ያኔም ጦርነት፤ ዛሬም ጦርነት ወደፊትም ጦርነት! በዚህ ሁሉ የዘመን እሰጣ ገባ የሞተውን የተፈናቀለውን፤ አካሉ የጎደለውን፤ ንብረቱ የወደመውን አስልቶ ክራራይሶ የሚል አንድም ፍጡር የለም። ለመኖር ሁሉም ይናውዛል። በናወዘ ቁጥር ደግሞ ያሰበውና ያለመው ሁሉ እየራቀበት መከራው ይበልጥ እየተጫነው ያለ ጊዜው ይጎብጣል። ይዳክራል! ሳይታሰብም ድንገት ሞተ ይባልና አማሟቱ ሳይመረመር አፈር ይመለስበታል። ታሪካችን ይህ ነው። ሌላው ሁሉ ቱልቱላ ከእውነት ጋር የሚጋጭ የሰዎችን ደም የረገጠ በህዝብና በሃገር ስም የሚነግድ የፓለቲካ ቸርቻሪ ትረካ ነው።
    ታዲያ በሃገራችን ነገር ሁሉ እንዲህ ከተጣረሰና መከራው በየጊዜው እየናረ ከሄደ መፍትሄው ምንድን ነው? እንደ ቀድሞዋ ደ/አፍሪቃ በአፓርታይድ ህገ መንግስት ሥር የወደቀችው የሃበሻ ምድር ፎካሪ የበዛባት የቀን እብዶች የሚራወጡባት በመሆኗ ከመገዳደል የዘለለ ሌላ ፍሬ ይገኛል ብዬ አላምንም። ሰው ገድለው አስከሬን ጋር ፎቶ የሚነሱ እብዶች፤ ሴትን በደቦ ደፍረው ተኩሰው የሚገድሉ ጉዶች፤ ምግብ አምጡ ብለው በሌለ ቤታቸው ያስተናገዷቸውን ሰዎች በር ዘግተው እሣት የሚለኩሱ የቁም ሙቶች፤ ሰውን ለስብሰባ ጠርተው በመትረጌስ የሚያጭድ አራዊቶች ያዙኝ ልቀቁኝ በሚሉባት ሃገር ሰላም ይመጣል ብሎ ማመን በራስ መቀለድ ነው። ችግራችን መሰረቱ ከእድገታችን ነው። ወላጅ ሲመታን፤ የጎረቤት ሰው ቅጣት ነው ብሎ ሲኮረኩመን፤ አስተማሪው ባጠፋነውና ባላጠፋነው ሲዥልጠን፤ ህግና ደንብ የሚያስከብረው ሲገፈትረን ነው ያደግነው። ሁሉ ነገር በጉልበት ብቻ ይሳካል እንጂ በሰከነ ጭንቅላት ተነጋግሮ ነገሮችን መፍታት አልተለመደም። ስለዚህ በተውሶ መሳሪያ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሰርቶ አዳሪ ወገኖቻችን ስናጭድ አለምን የገዛን ይመስለናል። ከቱርክና ከሌሎችም የተሸመተ ድሮን መሳሪያ አስታጥቀን በጭቃ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ነገ ምን እንደሚበሉ የሚያሰላስሉ ወገኖችን ገድለን መግለጣ እናወጣለን። እብደት ከዚህ በላይ የለም። ለይቶላቸው መንገድ ላይ የወጡ፤ ወይም በአማኑኤል ሆስፒታል የሚረድ እብዶች አይደሉም ሃገርን የሚያተራምሱት። አውቀናል፤ መጥቀናል እያሉ በክፋት የተጠመቁ የብሄር ሰካራሞች እንጂ!
    ትላንትም ዛሬም ወደፊትም በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ይመጣል ብዬ አላምንም። መሰረቱ የተናጋ፤ በጉቦና በእጅ መንሻ የተዛነፈ የፍትህ አሰራር የሰፈነበት፤ ድሃና የድሃ አደጎች የተገፈተሩበት በመሆኑ የከፋው ጫካም ሆነ ቋጥኝ እየፈለገ ሰውን እያፈነና እያሳፈነ አርሶና ሰርቶ መብላቱን ረስቶ የሰውን እንባና ደም ወደ ገንዘብ ለመለወጥ የሚራወጥባት ምድር ነው የምትሆነው። አሁንም ናት። የብርቱካን የመከራ ምንጭ በየሰበቡ የብልጽግናው መንግስት በሞት ከሸኛቸውና በፓለቲካ እስረኞች ስም በየስርቻው ካጎራቸው እስረኞች ታሪክ አይለይም። ተያያዥ ነው። የመንግስትም ጉዳዪን ለማስተባበል መንደፋደፍ ከዚሁ የፓለቲካ ውስልትና የመነጨ ነው። ለመኖር ሁሉም እንዲዋሽ ተደርጓል። እነርሱ ለማስተባበልና ለመደበቅ በጣሩ ቁጥር ነገሩ የባሰ እየጎላና ግፍ በብልጽግናው መንግስት በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ አለማሰለሱን አስረግጦ ያሳያል። ለዚህ ነው የሃበሻ ፓለቲካ በወረፋ የመገዳደል ፓለቲካ ነው የምንለው። ፍሬ የለሽ፤ ፍትህ የለሽ! ሁሉን አስለቃሽ! ሳያለቅስ የሞተ ሰው ካለ አገናኙኝ። ሁሉም አንብቶ በሲቃ ይለየናል። እኛም በቀናችን አይቀርልንም። እስካለን ግፍ ከመስራትና ከማሰራት እንቆጠብ! ከዘመናት በፊት ደበበ ሰይፉ ከቋጠረው አንድ ግጥም እንሆ
    እሱ ነው እሱ አይን ባይኖረው
    ለምን ብርሃን ኖረ የሚለው
    እግር ባይኖረው
    ለምን መንገድ ኖረ የሚለው
    እሱ ነው ከቅናቱ ጸሃይቱን የሰረቀ
    በመንገዴ አሜኬላ ያጸደቀ።

  3. ወንድም ተስፋ፦
    ተስፋ አትቁረጥ። ከታሪካችን ስላልተማርን ወይም ከልብ ኢትዮጵያን ስለማንወድ፣ ኢትዮጵያችን ደጋግማ እንድትሞት አድርገናል ወይም ለሞት አመቻችተናታል። እንደ 19ኛው ክፍለ ዘመን ጃፓን የአገርና የወገን ፍቅር ቢኖረን ኖሮማ፣ ዛሬ ከ12ኛ ተማሪዎቻችን ከመቶ 3 ብቻ የዩኒቬርሲቲ መግቢያ ፈተና ማለፍ ያንገበግበን ነበር፤ ያውም በፕሮፌስር ከሚመራ ተቋም። ይኸ ውድቀት ደግሞ ተማርን በሚሉት መሪዎች ብሷል። ቢሆንም፣ ጨለማው ሲገፈፍ ይነጋል ! mezegajet ያለብን ሲነጋ በጋራ ስለምንሠራው ገንቢ ሥራ ሊሆን ይገባል። ተማርን የምንል ሁሉ የትውልድ አደራ አለብን። ለሆድ ተገዝቶ መኖር ወይም ለሆድ ብቻ ሠርቶ መሞት የእንሥ ሳት ተፈጥሮ ነው።

    • ወዳጄ አንድነት ስለ አበራታች ቃሎችህ አመሰግናለሁ። ጀርመናዊው Bonhoeffer እንዳለው Stupidity enables evil ሆነና እንሆ እንዲህ ሆነን ተገኝተናል። ግን የእብዶች ቀን በሃበሻ ምድር የሚመሸው መቼ ነው? ፈላስፋና ባለ ቅኔው እውቁ ኢትዮጵያዊ ሰለሞን ዴሬሳ “እኔ የብዙ ቤተሰብ ውጤት ነኝ” ያለን ኦሮሞነቱ ተረስቶት አይደለም። እንዲህ በተንጋደደ የዘር ፓለቲካ ስላተቃመሰ እንጂ። በቅርብ ቀን ያለፈው ሌላው ኢትዮጵያዊ ጀግና ዪናስ ዴሬሳ ለኢትዮጵያ ህዝብና አንድነት ለነጻነት እንደተፋለመ አለፈ? ኸረ ስንቱን ቆጥረን እንዘልቃለን። የሚያጣላን ምንድን ነው? ሰው እንዴት ጤነኛ ከሆነ ወገኑን ገድሎና ዘርፎ ያቅራራል? ታመናል፤ ፈዋሽ መድሃኒት አተናል። ብሄራችን የክፋታችን መሸፈኛ ሆኗል!
      የመሬቱ ክፍፍልና የቁስ አካላዊው ፍቅር አይናችን አውሮታል። ያለፈን እየኮነን ዛሬ እኛ አውሬ ሆነናል። ምን ያህል ጊዜ ነው ሰው በዚህች ምድር ላይ የሚኖረው? ያደለው ግፋ ካለ ከ 80 አይበልጥም። ያላለለትም በየምክንያቱ ያለጊዜው ይቀጫል። የምድርን ከንቱነት አለመረዳታችን ከምን የመነጨ አፍራሽ እውቀት ነው? ነው አፍራሽን አፍራሽ እየተካው እኛም አብረን በሃሳብና በተግባር ፈራሽ ሆን? አንድ ማሰንቆውን ቃኝቶ ሰዎች በመሬት ሲጣሉ ያየ አዝማሪ እንዲህ አለ።
      ምን ያጣላችሁሃል በመሬት ጉዳይ
      እንዲህ ዘር ሲጠፋ ይቀር የለም ወይ?
      ጊዜን ያላወቁ ባለጊዜዎች በህዝባችን ላይ ያደረሱትና የሚያደርስቱ ገመና መቼ ነው የሚገታው? መቼ ነው ሰው በሰውነቱ የሚመዘነው፤ ሃይለኛው ለደካማው ከለላ የሚሆነው የት ላይ ስንደርስ ነው? ይጨንቀኛል። ዘንተ ዓለም ሃገሬ ላይ የሚወርደው የመከራ ዶፍ እንቅልፍ ነስቶኛል። የተቆራመቱ እናቶችና ህጻናት ከትግራይ እስከ ወለጋ ይታዪኛል። አይበቃንም መገዳደል። ለህዝባችን አናስብም? ጥላቻን ሰንቆ ጠበንጃ ያነገተ የብሄር ሰካራም ለባህልና ለአስተሳሰብ ለውጥ ራሱን አያስገዛም። ይገድላል፤ ይሞታል። ይህንም ልብ ብሎ ላየው ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው! ስናሳዝን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News