Homeነፃ አስተያየትአዲስ  አበቤ ንቃ! (በአንቺንአሉ)

አዲስ  አበቤ ንቃ! (በአንቺንአሉ)

Advertisement
World Wide Travel Group
አዲስ  አበቤ

በአንቺንአሉ

የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በተከሰተ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት አከባቢ የአገልግሎት ጊዜው ያለቀበትን መታወቂያዬን ለማሳደስ ወደምኖርበት ክፍለ ከተማ አቅንቼ ነበር፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ወለል ላይ ደርሼ ወደ ውስጥ ስገባ ግን በየተከለላቸው ዴስክ ተቀምጠው እዛ እና እዚህ ሁሉም ሰራተኞች በኦሮምኛ ሲነጋገሩ ሳይ አዲስ አበባ አንድ ክፍለ ከተማ ሳይሆን ኦሮሚያ ክልል ወደ አንድ የአገልግሎት መስጫ ቢሮ ውስጥ የገባሁ የመሰለኝን ያህል ተደናግሬ ነበር፡፡

ቆም ብዬ ካስተዋልኳቸው በኃላ ከወሬያቸው ውስጥ የሌለ እና ሲያዩትም የምግባባው እና ከተማ ቀመስ ወደመሰለኝ አንዱ ወጣት ባለሙያ ጋር ተጠግቼ ለምን እንደመጣሁ ነገርኩት፡፡ ከእነሱ ጨዋታ ሲሳተፍ ባለማየቴ በዲሞግራፊ ቅየራው ያልመጣ እና ነባር ሰራተኛ ነው፤ በቋንቋዬ ያናግረኛል የሚል ግምት ወስጄም ነበር፡፡ ግምቴ ትክክል አለመሆኑን የተረዳሁት አፍታም ሳይቆይ ጉዳዬን ከሰማ በኃላ ዞር ብሎ እሱም በፌዴራሉ ይፋዊ የስራ ቋንቋ በአማርኛ ሳይሆን በኦሮምኛ ከጎኑ ያለውን ባለሙያ ሲያናግረው ነበር፡፡ ያለን መስሎናል ‘ወራሪ’ የምንባለው ለካ ተወረን አልቀናል አልኩኝ በውስጤ፡፡

የሆነው ሆኖ ‘በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሰራተኞች በፈረቃ ስለምንሰራ እና የመዝገብ ቤቱ ሰራተኛ አርብ ስለምትገባ ፋይልሽን አስወጥተን እንጠብቅሻለን አርብ እለት ተመለሺ’ አለኝ፡፡ ስለወረርሽኝ ሲያነሳብኝ እኔም ስለ’ወረራ’ እያሰብኩ ካለው ጋር ተገጣጥሞብኝ በውስጤ ፈገግ እያልኩ ነበር፡፡ 

በተባለው ቀን ሄጄ ወደእራሱ ወደባለሙያው ቀርቤ ጉዳዬን አስታወስኩት፡፡ ‘የመዝገብ ቤት ሰራተኛዋ አልገባችም በቀጣዩ ሳምንት ተመልሰሽ ነይ’ አለኝ፡፡ ለመታወቂያ እድሳት ይሄን ያህል አልጉላላም እንደውም በቃ መሸኛዬን ስጠኝ አልኩት፡፡ ‘ለመሸኛም ቢሆን ከየት የት እንደምትሸኚ የሚገልፅ መሸኛ ለመፃፍ እራሱ ፋይሉ ያስፈልጋል’ ብሎ ክርክር ስንገጥም ነበር ጥግ ላይ ተቀምጦ የነበረው አንድ ሰው ‘ነይ ወደ እኔ ምንድነው ጉዳይሽ? እኔ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ነኝ ንገሪኝ’ ያለው፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ወደስራ አስኪያጁ ቀርቤ ለሁለተኛ ግዜ መምጣቴን እና የሆነውን ነገርኩት፡፡ የማያድሱልኝ ከሆነም መሸኛዬን መስጠት ግዴታቸው መሆኑን አከልኩበት፡፡ ይሄንን ግዜ ነው እንግዲህ እስክንድር ነጋ ስለኦህዴድ መራሹ መንግስት ከማንም ቀድሞ ‘ለአዲስ አበባ  ነዋሪ ላልሆኑ የኦሮሚያ ዜጎች መታወቂያ በገፍ እያደሉ ነው’ ሲል ‘እብድ’ ተብሎ የተጠራበት አጋጣሚ እውነትነትን ያረጋገጥኩበት ክስተት የተፈጠረው፡፡

ስራ አስኪያጁ ፎቶግራፍ ይዘሻል ወይ ብሎ ፎቶግራፍ ሰጥቼው ተቀብሎኝ አዲስ የመታወቂያ ካርድ አንስቶ እዛ ላይ የሚጠይቀውን መረጃ እየጠየቀኝ መሙላት ሲጀምር ሁሉም በኦሮምኛ ‘እንዴት ዝም ብለህ ትሰጣታለህ ማን ናት?:: ምንድን ናት?:: የእኛ ሰው አይደለችም’ ብዬ የተረዳሁትን ክርክር የገጠሙት፡፡ በማላውቀው ቋንቋ ተገልጋዩአ ቁጭ ብዬ ሲነጋገሩ ብቻ መታወቂያዬን ይስጠኝ እንጂ ብዬ ንዴቴን ዋጥ አድርጌ የሚሆነውን ማየት ቀጠልኩ፡፡

የሆነው ሆኖ የመኖርያ አድራሻ የቤት ቁጥሬን ‘አዲስ’ ብሎ ሞልቶ ማን ልሁን ምን ልሁን ሳያመሳክር አዲስ መታወቂያ ሰጠኝ፡፡ ለእኔ እንዲህ መረጃ ሳያመሳክር ከሰጠኝ በባለጊዜነቱ በያዘው ቦታ እስኬው ላላቸው እሱን መሰል ኦሮሞዎች መታወቂያ በገፍ ላለማደሉ ሌላ ምንም ማስረጃ አላስፈለገኝም ነበር፡፡ 

እውነታቸውን ነው እነዛ ባልደረቦቹ የእኛ ሰው አይደለችም ያሉት፡፡ አዎ! በጨረቃ ቤት ስም፤ ህጋዊ ደሀ፤ መጤ፤ ወራሪ፤ ሰፋሪ፤ ቆምጬ፤ ፎጣ ለባሽ፤ ነፍጠኛ የሚሉኝ እና ከመሰረትኩት ከተማ ሊነቅሉኝ የሚፈልጉኝ እና በገፍ እያፈናቀሉኝ ካሉት እንዷ ነኝ፡፡ አዎ! አማራ ነበርኩ፡፡ አማራ ነኝ፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

እስኬው ያኔ ሲጮህ የት ነበርክ አዲስ አበቤ?

እስክንድር በዚህ አላግባብ መታወቂያ እደላ ዙርያ፤ በቅርስ ቤቶች ፈረሳ፤ በልማት ስም ነዋሪዎችን ከቀዬአቸው ማፈናቀል፤ ተቸግረህ ቆጥበህ ይደርሰኛል እያልክ የምትጠባበቀውን ኮንዶሚኒየም ለባለተረኞቹ የመንግስት ባለስልጣናትና ከኦሮሚያ ለመጡ የመንግስት ሰራተኞች አላግባብ እደላ፤ ከቀሚስ እና ነጠላህ ላይ መለያዬ ሰንደቄ ያልከውን ስለመበጫጨቃቸው፤ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በሌላም በብዙ ብዙ የኦህዴድ መራሹ ሸፍጥ፤ ሴራ፤ የሸር ፖለቲካቸው እና ህገወጥ ድርጊት ዙርያ አደባባይ ወጥቶ ሲናገር፤ ንቃ አዲስ አበቤ ሲል፤ ለወደፊት ስለሚመጣብህ መከራ ቀድሞ ሊያዘጋጅህ፤ ተደራጅ፤ እንደራጅ ሲልክ የት ነበርክ?:: 

የአብይ አህመድ የአምባገነንነቱ ጭምብል ለመጀመርያ ጊዜ የተገለጠበት እና በወቅቱ በብእረኛነቱ እና በሰላማዊ መንገድ ተደራጅቶ እየታገለ የነበረው እስኬው ላይ በዛ ድምፀት ሲዝትበት በዝምታህ አልተደመርክም ነበርን?::

የዛኔ እሱን ‘እብድ’ በሚል መጠርያ ሙድ ስትይዝ አልነበረምን?:: አዎን! ‘እብድ’ ነበር እስክንድር፡፡ በ’እብዶች’ መሀል የተገኘ አንድ ጤነኛ ‘እብድ’ ቢባል አይገርመኝምና፡፡ ተመስገን ደሳለኝ አንዴ ‘አዲስ አበቦ’ አንድ ግዜ ደግሞ ገና ከንጋቱ ‘የአዲስ አበባ ሽኝት’ እያለ ሲፅፍልህ፤ ሊያነቃህ ሲሞክር የት ነበርክ?:: 

- Advertisement -

እኔ ግን እላለሁ! አዎ! እስክንድር እንደዚያ ሲል ታከለ ኡማ ያለበቂ ካሳ የተፈናቀሉ ገበሬዎች እና ልጆቻቸው በሚላቸው ስም ከወለጋ እና አርሲ ላስመጣቸው ኦሮሞዎች ሁሉ ኮንዶሚኒየም እያደለ አንተ ደግሞ በጉርሻው ልብህ ጥፍቶ ብሎ ተዘርረህ ነበር፡፡ ታከለ ጀምሮት አዳነች አቤቤ ባስቀጠለችው የየአደባባዩ እና የየፓርኩ የማስ ስፖርት ከስር ከስራቸው ዘጥ ዘጥ  ስትል ነበር፡፡ አብይ እና አዳነች በየሰፈርህ በከለሉልህ የወጣቶች ማዘውተርያ ቅሪላህን እያንከባለልክ ነበር፡፡ ሳይፈርስ የመኮንንን ባቅላቫ ለመጨረሻ ግዜ ላጣጥም ብለህ ሰልፍ ይዘህ ነበር፡፡

መቼም አመት ጠብቀህ በየጥምቀቱ፡-

‘የኛ ሙሽራ ብይ ቂንጬ

ያንቺ ነው ኮዬ ፈጬ’

‘የኛ ሙሽራ ስሟ ጫልቱ

ያንቺ ነው ቱሉ ዲምቱ’

‘የኛ ሙሽራ ስሪ ጨጨብሳ

ያንቺ ነው ቦሌ አራብሳ’ እያልክ በአደባባይ የጨፈርከውን እንደክሬዲት መዝግቡልኝ አትልም አይደል?፡፡

እስኬውን ለመካስ…?

አዲስ አበቤ ሆይ ኀረ ለመሆኑ እድሜ ልኩን ስለሰላማዊ ትግል ሲሰብክ፤ በጉዳዩ ዙርያ መፅሀፍ ፅፎ ሲያሳትም፤ በዛው መስመር ሲታገል፤ ለበርካታ ጊዜያት ሲታሰር እና ሲፈታ የኖረው እስክንድር ሰላማዊ ትግልን ትቶ ለምን ነፍጥ አነሳ? ለምን ፈነነ? ብለህ እራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ? እንጃ! 

እኔ ግን ይሄንን የወንበዴ መንግስት በሰላማዊ ትግል መጣል እንደማይቻል ድምዳሜ ላይ ከመድረሱ ባሻገር ያንተም ልግመት እና አግዘኝ፤ ተደራጅ፤ ላደራጅህ፤ እንደራጅ ላለበት ጥሪው የሰጠኀው የጆሮ ዳባ ልበስ ምላሽ ተስፋ አስቆርጦት ይመስለኛል፡፡ ቢሆንም እስኬውን ለመካስ ኀረ የምን እስኬውን ለራስህው ስትል የመነሻ ጊዜው አሁን ነው፡፡ አልረፈደም፡፡ 

‘እየመጡ ነው’ ‘እየመጣ ነው’ እያልክ መጠበቅህን ትተህ፤ ‘ፋኖ የት ደረሰ’ን ትተህ፤ እኔ ዘር የለኝም ዘር ለገበሬ ነው እያልክ የምትይዘውን ሙድ ትተህ፤ የ1997 የምርጫ ገድልህን መተረክ እና በትዝታ መኖርህን ትተህ፤ ቡና ገበያ አደገኛ እና ሳንጅዬ ማለትህን ትተህ፤ የጃን ሜዳ የሀርሞኒካ ሾውህን ትተህ፤ በቄሮ እና በደንብ አስከባሪ ዱላ መታገዱን እና መታገቱን ትተህ፤ ጫት አና ሺሻህን ወርውረህ እና ማንሾካሾክ እና ማልጎምገሙን ትተህ፤ በየአከባቢህ እየተወያየህ፡ እየተደራጀህ፡ ያለህን ስለህ፡ ዘገርህን ነቅንቀህ ጠብቀው ወይ ከዋለበት ከወንዶቹ ሜዳ ሄደህ ተቀላቀለው፡፡ 

ይሄው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እና መስመር ብቻ ነው እስኬውን የምትክሰው፡ እራስህንም ከአይጠረቄው ዘንዶ፤ ከኦሮሙማ፤ ከአውሬው የምታድነው፡፡ በሌሎች አይን ሲታይ እስካሁን ተመዝኖ ያልቀለለው ፅኑና ብርቱው ብረቱ እስኬው ለሁሉም ለሚበጀው እና ለሚበልጥበት መስመር ተሰልፏል፡፡ ብትችል እንደ ወንዶቹ የወንዝህ ልጆች እንደ ፈረንሳይ ለጋሲዮኑ ዘላለም ወይም እንደ አፍንጮ በሩ አሮን ወደ ቤተ አማራ/ወሎ ወይ ጎንደር ወይ ሸዋ ወይ ደግሞ ጎጃም ሄደህ ተቀላቀለው!፡፡ ካልቻልክ  ነቅተህ፤ ተሰናድተህ እና ተዘጋጅተህ ካለህበት ካባቶችህ ርስት ከሸዋዋ አዲስ አበባ ላይ ጠብቀው፡፡

አበቃሁ!

__

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡

https://borkena.com/subscribe-borkena/

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News