Homeመጣጥፍመቸና እንዴት ይሆን?

መቸና እንዴት ይሆን?

Advertisement
World Wide Travel Group
መቸ ይሆን
የአዲስ ገብሩ የጥበብ ስራ

ጠገናው ጎሹ


ከረጅሙ ታሪክ በቅጡ ተምረን
ክፉውን በማረም በጎውን አፅንተን
እንዲመጥን አርገን ላለንበት ዘመን
ለስሜት ፈረሱ ልጓም አበጅተን
ከምር ተፀይፈን
የውድቀት አባዜን
ደግሞም በልክ አርገን
ከየእለት ክስተት ጋር መሞቅ መቀዝቀዝን
ከምር እምቢ ብለን
መከራ መቁጠርን
ውርደት መሸከምን
በቅጡ ሳንኖር አለን የማለትን
የውርደት አዙሪት የቁም ሙትነትን
የጨካኞች ቀንበር ሰለባ መሆንን
ሥር የሰደደውን እንቆቅልሻችን
በቃ የምንለው በአንድ ላይ አንድ ሆነን
መቼና እንዴት ይሆን?

በዓለማዊም ሆነ በሥነ መለኮት
ልሂቃን ነን እያልን የምንኩራራበት
ከማነብነብ አልፈን ነፍስ ያልዘራንበት
የከንቱ ውዳሴ የተግባር አልባነት
መሬት ላይ አውርደን ያልተጠቀምንበት
ገዳይ አስገዳይን ያልተጋፈጥንበት
ግፈኛና ግፍን ያልተፀየፍንበት
ህዝብን ከመከራ ያላወጣንበት
የዘመን ጠገቡ የውድቀት ላይ ውድቀት
መቸና እንዴት ይሆን ፈውስ የሚገኝለት?

ትምህርትና መማር በአጭሩ ሲጨመቅ
እውነት ሆኖ ሳለ የማያጠያይቅ
በጎውን የማፅደቅ ክፉውን የመናቅ
ብሎም በአርበኝነት ለነፃነት መውደቅ
ትውልድን የማዳን እውቀት በማስታጠቅ
አንቅቶ አደራጅቶ ለድል ብስራት ሰንደቅ
ተላብሶ መኖርን የሰላም ወርቃ ወርቅ
በፍቅር እየኖሩ በፍቅር የመፅደቅ
ስናበለሻሸው እንዴት አያሳቅቅ?
እንዴትስ ነው እማይጨንቅ?

እስኪ እንጠይቀው እኛኑ ራሳችን
ቆመን እያስገደልን ንፁህ ወገናችን
ደግሞ አያሌዎችን
ለእስር ለመከራ ሲዳረጉ እያየን
የሰቆቃ ጩኸት በግልፅ እየሰማን
አገር ምድረ ሲኦል እያየናት ስትሆን
እየገፈተረ ቁልቁል ያወረደን
ብለን እስክንጠይቅ ምንድን ነው ሰው መሆን?
ፍፃሜ እሚያገኘው መቸና እንዴት ይሆን?

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

እንደ እኔ መፍትሄው
ከሰቆቃ መውጫው
አንድና አንድ ብቻ ነው ።

አዎ! እንነጋገር ካልን ስለ እውነት በእውነት
የሸፍጠኞችና የሴረኞች ሥርዓት
የዘመናት መርገምት
በሁለገብ ትግል መነቀል አለበት።

የሰመረ እንዲሆን ፍኖተ መፍትሄው
ግቡን እንዲመታ ያሰብነው ያቀድነው
ወደ ዴሞክራሲ የመሸጋገሪያው
ትውልዳዊ ታሪክ እውን የማድረጊያው
ፈታኝ እንደሚሆን ግልፅና ግልፅ ነው።
እናም ለዚህም ነው ከዳር እየቆሙ ከመተቸት ይልቅ
ግልፅነትንና ገንቢነትን ሳይለቅ
እንደ ፋኖ አይነቱን ማገዝና ማምጠቅ
የአጋርነት አውድን ማስፋትና ማድመቅ።

__

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡ https://borkena.com/subscribe-borkena/

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News