Homeአበይት ዜናሸኔ መተከል እና ካማሺን በፍጥነት እየተቆጣጠረ ነው ተባለ

ሸኔ መተከል እና ካማሺን በፍጥነት እየተቆጣጠረ ነው ተባለ

Advertisement
World Wide Travel Group

  • ሴቶች በባሎቻቸው ፊት ተደፍረዋል

መተከል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (ከማህበራዊ ሚዲያ )

መርሻ አሰፋ

መንግሥት “ሸኔ” ብሎ በአሸባሪነት የፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል መተከል እና ካማሺ ዞኖችን በፍጥነት እየተቆጣጠረ መሆኑ አካባቢ ነዋሪዎች ለቦርከና ተናረሩ፡፡

ባለፈው ኹለት ዓመት በአንጻራዊነት መረጋጋት ያሳዩት መተከል እና ካማሺ ካለፈው አምስት ወር ወዲህ ቀውስ ቀጠናነት እየገቡ ነው ተብሏል፡፡ ከወለጋ ዞኖች ተንቀሳቅሷል የተባለው ሸኔ ወደ ቤኒሸንጉል ጉምዝ ክልል ዘልቆ በመግባት በርካታ አካባቢዎች በፍጥነት እየተቆጣጠረ መሆኑ ተመላቷል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ታጣቂ ቡድኑ ከሰሞኑ የድባጢ ቀበሌዎች ተቆጣጥሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከግድያ እስከ አስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸመ መሆኑን ተሰምቷል፡፡ ሸኔ ከተቆጣጠራቸው የወረዳው ቀበሌዎች መካከል በርበር ከተማ አንዷ ስትሆን፣ በታዳጊዋ ከተባ በርካታ ሴቶች ተደፍረዋል ተብሏል፡፡

ባለፈው እሁድ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም “አንድ አባት የግል መሳሪያውን ተቀምቶ ከታገተ በኋ፣ ኹለት ሴት ልጆቹ ፊት ለፊቱ ተደፍረዋል” ሲሉ አካባቢ ነዋሪዎች ለቦርከና ተናገረዋል፡፡ በወረዳው እሰከ 10 የሚደርሱ ቀበሌዎች የተቆጣረው ታጣቂ ቡድኑ በየቀኑ ግድያ፣ እገታ፣ ዘረፋና አስገድዶ መድፈር እየፈጸመ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢ ማኅበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት “የተፈቀደ እሰኪመስል ድረስ ሰሚ ጠፍቷል” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ ቡድኑ በተቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቡድኑ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የጸጥታ ኃይሎችም ይሁን ማንኛውም የመንግሥት አካል “ዝር” አይልም ሲሉም፣ መንግሥታዊ ኃይላፊነቱን የሚጣ አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ቡድኑ በሰላማዊ ሰዎችን የሚያደርሰው ጥቃት የክልሉ መንግሥት ለጥቃቱ ትኩረት አልሰጠውም ሲል የአካባቢ ማኅበረሰብ ተወካዮች ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት ለጥቃቱ ትኩረት አልሰጠም ያሉ አካባቢው ማኅበረሰብ ተወካዮች የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በተለይ በመተከል ዞን ቡለን፣ ድባጢና ወምበራ ወረዳዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ነው ተብሏል፡፡ ቡድኑ ያለማንም ከልካይ እየፈጸመ ነው የተባለው ጥቃት ግድያ፣ እገታና ዘረፋ ሲሆን፣ ከግለሰብ እሰከ መንግሥት፣ ከባንክ እሰከ ፖሊስ ጣቢያ፣ ከጤና ጣቢያ እሰከ ሆስፒታል ከፍተኛ ሀብት መዘረፉ ተገልጿል፡፡

ሸኔ በሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ከመንግሥት እሰከ ሚዲያ ጆር አልተሰጠውም በሚልም የአካባቢው ማኅበረሰብ ተወካዮች ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ “ሕዘቡ በተደጋጋሚ ለክልሉ መንግሥት የድረሱልኝ ጥሪ ቢያቀርብም ሰሚ አላገኘም” ያሉት ተወካዮቹ፣ የፌደራል መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ዜጎችን ከጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

መንግሥት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ካልቻለ ማኅበረሰቡ ራሱን አደራጅቶ አካባቢውን ከጥቃት እንዲከላከል እንዲፈቅድ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ የግል መሳሪያ ያላቸው ታጣቂዎቾ ራሳቸውን አደራጅተው እንዲከላከሉ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት በተጨማሪ፣ ወጣቱ ሰልጥኖ አካባቢውን እንዲጠብቅ እንዲደረግም ተወካዮቹ ጠይቀዋል፡፡

__

- Advertisement -

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡ https://borkena.com/subscribe-borkena/


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News