Homeአበይት ዜናድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ስራውን መስራት እንዳልቻለ...

ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ስራውን መስራት እንዳልቻለ ገለጸ

Advertisement
World Wide Travel Group
የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሃኪሞች በእባብ የመነደፍ አደጋ ለደረሰባቸው ህሙማን ክትትል ሲያድርጉ (ፎቶ ፡ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን)

ሳሙኤል አባተ 

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ– ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ዛሬ ለቦርከና በላከው መግለጫ በአማራ ክልል ያለው ጦርነት የጤና ስራዎችን ባሰበው ልክ እንዳይሰራ እንዳደረገው አስታውቋል።

ሰዎች የህክምና አገልግሎት ፈልገው ወደ ጤና ተቋማት መምጣት አልቻሉም ያለው ቡድኑ ታካሚዎች ለተራዘመ ስቃይ እና ሌሎች የጤና ችግሮች መዳረጋቸውንም አስታውቋል።

በምህጻረ ቃሉ ኤም ኤስ ኤፍ በሚል የሚጠራው ተቋሙ በተለይም በምዕራብ አማራ አካባቢ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በሚል በአብዱራፊ ያቋቋመው የጤና ማዕከል በግጭቱ ከተጎዱ አካባቢዎች ዋነኛው መሆኑን ገልጿል።

በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች በተለይም በእባብ መነደፍ  እና ወባ መሰል ህመሞች የሚጠቁ ሰዎች በአካባቢው ባለው ግጭት ምክንያት በቶሎ ወደ ህክምና ተቋማት መምጣት እንዳልቻሉ ለቦርከና ሚዲያ በላከው  መግለጫው ላይ ተጠቅሷል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁመው ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ ታካሚዎች ለተደራራቢ ወጪዎች ከመዳረጋቸው ባለፈ በትራንስፖርት ወቅት ዝርፊያን ጨምሮ ድብደባ እና ሌሎች አካላዊ ጥቃቶች እየደረሱባቸው ነውም ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ከጤና ተቋማት ወደ ሆስፒታሎች ሪፈር የሚባሉ ታካሚዎች በጦርነቱ ምክንያት መጓዝ እና ህክምና ማግኘት እንዳልቻሉም በቡድኑ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

በተለይም ሰፊ ታካሚዎችን በሪፈር ተቀብሎ ህክምና በመስጠት የሚታወቀው ጎንደር ሆስፒታል በጦርነቱ ምክንያት መንገዶች በመዘጋታቸው እና ታካሚዎች በየመንገዱ በሚያጋጥማቸው ፍተሻ ምክንያት ተማረው በመቅረታቸው የታሰበውን ያህል ህክምና እየሰጠ እንዳልሆነ ተገልጿል።

የፌደራል መንግሥት የክልል ልዩ ሀይሎችን ዳግም አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ካስተላለፈበት ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ይህ ጦርነት ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ንጹሀን ለሞት፣ ዝርፊያ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መጋለጣቸውን የሀገር ውስጥ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ ጠቅሰዋል።

__

ድጋፍ ያድርጉ :- ቦርከና ከ13 ዓመታት በላይ ነጻ መድረክ በመሆን አገልግሏል ፤ ወደ ፊትም በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ስላለበት እና አስቸጋሪ  በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰራ ስለሆነ  ችግሩን ለመቅረፍ በዓመት $5 ወይንም $10 የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ አቅም ካለዎት እዚህ ገጽ ላይ በመሄድ ድጋፍ ያድርጉ፡፡ https://borkena.com/subscribe-borkena/


የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News