
መርሻ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ-በሰሜኑ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ሦስት የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሰራተኞች የተገደሉት በመከላከያ ሰራዊት መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በትግራይ ክልል በሰብዓዊ ሥራ ላይ በተሰማሩበት የተገደሉት የድርጅቱ ሰራተኞች የግድያ ሁኔታ ከአራት ዓመታት ገደማ በኋላ ታውቋል፡፡ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) ሦስቱም ሰራተኞቹ የተገደሉት በመከላከያ ሰራዊት መሆኑን ባደረገው የውስጥ ምርምራ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
የተገደሉት የረድኤት ድርጅቱ ሰራተኞች ኹለቱ ኢትዮጵያውያን ቴዎድሮስ ገብረማርያም እና ዮሐንስ ሃለፎም እና ስፔናዊቷ ማሪያ ሄርናንዴዝ ማታስ ናቸው፡፡ ሰራተኞቹ የተገደሉት በወቅቱ በጦርነቱ የቆሰሉ ሰዎች ስለነበሩ የህወይት አድን ሥራ ለመሥራት እየተንቀሳቀሱ ባለበት አጋጠሚ ነው ተብሏል፡፡
ሰራተኞቹ የተገደሉት በመከላከያ ሰራዊት “ሆን ተብሎ እና ኢላማ ተደርገው” መሆኑን ድርጅቱ ይፋ ባደረው የውስጥ ምርምራ ውጤት ያመላክታል፡፡ ድርጅቱ ሰራተኞቹ ከተገደሉበት ቀን ጀምሮ ባደረገው የውስጥ ምርመራ ሆን ተብሎ በመከለካያ መገደላቸውና መኪናቸው መቃጠሉን ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
ሰራተኞቹ አካባቢ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች እንደነበር በሳታላይት ምስል ምርምራ ማረጋገጡን ድርጅቱ አመላክቷል፡፡ በወቅቱ አንድ የመከላከያ አዛዥ በረድኤት ሰራተኞቹ ላይ የሰራዊቱ አባላት እንዲገድሏቸው “አስወግዳቸው” የሚል ትዕዛዝ መስጠታቸውን በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
የሦስቱ ሰራተኞች አስክሬን እና ይጓዙበት የነበረው መንገድ ላይ ተጥሎ የተገኘ ሲሆን፣ ይጓዜበት የነበረው ተሸከርካሪ ተቃጥሎ መገኙ ይታወሳል። በወቅቱ በረድኤት ድርጅቶች እና በሰብዓዊ መብት ተቋማት ዘንድ ድርጊቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮ ነበር፡፡
ማሪያ እና ዮሃንሰ በተተኮሰባቸው ወቅት በእግራቸው እየተራመዱ እንደነበር የምርመራ ውጠየቱ ያመላክታል፡፡ ይሁን እንጂ ሰራተኞ ለምን በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ እንደነበ “ለጥያቄ ተጠርተው ይሁን ወይም ከወታደሮቹ ጋር እንነገጋር ብለው የሚታወቅ ነገር የለም” ተብሏል።
ኤም ኤስ ኤፍ ባካሄደው ምርመራ “ጥቃቱ ሆን ተብሎ እና በግልጽ በሚታወቁ ሶስት የረድኤት ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ግድያ መሆኑን” አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የግድያውን ለአገባቡ ለመመርመርና እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት አላሰየም ሲል ድርጅቱ ክስ አሰምቷል፡፡
ድርጅቱ በውስጥ ምርመራ የግድያ ውኔታው ይፋ የደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት በጎ ምናሽ ስላልሰጠው መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላም ስለ ረድኤት ሰራተኞቹ ግድያ በወቅቱ ጦርነት ላይ ከነበሩት ከፌደራል መንግሥትም ይሁን ከህወሓት ታማኝነት ያለው መልስ እንዳለገኘም ጠቁሟል፡፡
__
ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






