Homeዜናበአማራ ክልል ደብረሲና አቅራቢያ ባለችው መዘዞ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር...

በአማራ ክልል ደብረሲና አቅራቢያ ባለችው መዘዞ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መዘረፉ ተገለጸ

Advertisement
World Wide Travel Group
mezezo bank robbery

ሳሙኤል ወልዴ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ– የጣርማበር ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት እንደገለጸው መዘዞ ከተማ ከሚገኙ ሶስት የባንክ ቅርንጫፎች ከ41 ሚሊዮን በላይ ብር ተዘርፏል።

ጽህፈት ቤቱ ዘረፋው”ጽንፈኞች” ብሎ በጠራቸው ታጣቂዎች ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ሰባት ሰዓት ላይ መፈጸሙንም አስታውቋል።

እንደ መግለጫው ከሆነ በከተማዋ ባሉ አባይ ባንክ፣ ቡና ባንክ እና ጸደይ ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ዝርፊያ ተፈጽሟል።

የወረዳው ኮሙንኬሽን የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ቸርነትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከቡና ባንክ 11 ሚሊዬን 550 ሺህ ብር፣ ከፀዳይ ባንክ 1 ሚሊዬን 28 ሺህ ብር እንዲሁም ከአባይ ባንክ 29 ሚሊዬን 365 ሺህ ብር በአጠቃላይ 41 ሚሊዬን 943 ሺህ ብር ተዘርፏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ይሁንና ዘረፋውን ፈጽመዋል የተባሉ አካላት እስካሁን ስለጉዳዩ ያሉት ነገር የለም

በአማራ ክልል ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጦርነቱ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መጀመሩ ይታወሳል።

በዚህ ጦርነት ንጹሀን ዜጎችን ለሞት፣ አካል መጉደል፣ ስደት እና ንብረት ውድመት መዳረጉን የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ አሜሪካ፣ ተመድ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም አካላት ጦርነቱ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጠይቀዋል።

የፌደራል እና የክልሉ መንግሥታት በበኩላቸው ንጹሀን ዜጎችን ኢላማ እንዳላደረጉ፣ በታጣቂዎች ላይ ህግ የማስከበር ስራዎች እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

- Advertisement -

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News