Homeአበይት ዜናከህወሀት ባፈነገጡ ፖለቲከኞች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ በትግራይ መንቀሳቀስ ጀመረ

ከህወሀት ባፈነገጡ ፖለቲከኞች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ በትግራይ መንቀሳቀስ ጀመረ

Advertisement
World Wide Travel Group

ሳሙኤል ወልዴ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – በቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሌሎች ፖለቲከኞች የተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ቢሮውን በመቐለ መክፈቱን አስታውቋል።

ፓርቲው ከመቐለ በተጨማሪም በራያ እና አካባቢው ባሉ ከተሞች ተጨማሪ ቢሮዎቹን ከፍቻለሁ ብሏል።

ፓርቲው በቀጣይም ሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳ ከተሞች ላይ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶችን እንደሚከፍትም ገልጿል።

ከህወሀት ፓርቲ ተገንጥለናል ባሉ ፖለቲከኞች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት ነበር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ፈቃድ የተሰጠው።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በአባላት ምልመላ ላይ መሆኑን የገለጸው ስምረት ፓርቲ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጭ ላይ እንደሚወዳደር ይጠበቃል።

በተለይም ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ለሚያደርገው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ስምረት ዋነኛ አጋር ሊሆን እንደሚችልም የፓርቲው አመሰራረት እና አመራሮች እንቅስቃሴ ያስረዳል።

ከአምስት ወራት በፊት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አካል የነበረው ህወሀትን ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ማገዱ ይታወሳል።

ቦርዱ ህወሀትን ያገደው ጠቅላላ ጉባኤውን አላካሄደም በሚል ሲሆን ህወሀት ግን የቦርዱን ውሳኔ ተቃውሟል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የትግራይ ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ ስራ የጀመረው ስምረት ፓርቲ ከክልሉ ውጪም አባላትን በመመልመል ላይ ሲሆን በቀጣዩ ወር ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የሰከነ መስሎ የነበረው የክልሉ ፖለቲካ ህወሀት ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሳደጉን ተከትሎ ዳግም የፖለቲካው ትኩሳት እየጨመረ መጥቷል።

የህወሀት እና ፌደራል መንግሥት አለመግባባትን ለማርገብ ከሰሞኑ ከሁሉም ሀይማኖቶች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ወደ መቀሌ አቅንተው ተወያይተው ተመልሰዋል።

ሽማግሌዎቹ በዛሬው ዕለትም በተመሳሳይ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸው ተገልጿል።

- Advertisement -

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News