Homeአበይት ዜናበክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊሰማ የነበረው የዐቃቤ ህግ ምስክር ታገደ

በክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊሰማ የነበረው የዐቃቤ ህግ ምስክር ታገደ

Advertisement
World Wide Travel Group
ፋይል (ማህበራዊ ሜዲያ)

መርሻ 

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዕግድ ትዕዛዙን ያስተላለፈው አቶ ክርስቲያን በጠበቆቻቸው በኩል የይግባኝ አቤቱታ ከቀረበለት በኋላ ነው። ጠበቆች የስር ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታውን ያቀረቡት ከአንድ ሳምንት በፊት ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ነው።

ተከሳሾች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ከዐቃቤ ህግ ምስክር ጋር በተያያዘ በሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አሰምተዋል። ይግባኝ የተባለባቸው ሁለት ብይኖች ሰኔ 18 እና ሐምሌ 1/2017 በስር ፍርድ ቤት የተላለፉ ውሳኔዎች ናቸው።

ይግባኝ የተባለበት ምስክር በአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ በተከፈተው የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ክርስቲያን ላይ የሚመሰክር ነበር። ዐቃቤ ህግ አቶ ዮሐንስን እና የፓርላማ አባሉን አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ በሌሎች ፖለቲከኞች ላይ ክስ የመሰረተው ከአንድ ዓመት ከአራት ወር በፊት መጋቢት 2016 ዓ.ም. ነበር።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በ68 ገጾች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀረበው የዐቃቤ ህግ የክስ ሰነድ በተከሳሾች ላይ አራት ክሶችን አቅርቧል። የወንጀል ሕጉን እና የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጣር እና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ የተፈጸመ “ወንጀልን” የሚመለከተው የመጀመሪያ ክስ የቀረበው በሁሉም ተከሳሾች ላይ ነው።

ክርስቲያን ከመጀመሪያው ክስ በተጨማሪ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ሁለተኛ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክርስቲያን የጦር መሳሪያን ለመያዝ ፈቃድ ሳይኖራቸው አንድ ታጣፊ ክላሽ ከነ ካርታው እና 30 የክላሽ ጥይት በቤታቸው ይዘው መገኘታቸውን ዐቃቤ ሕግ በክስ ሰነዱ ላይ አስፍሯል።

ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 21 የሰው ምስክሮች እና 28 የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። ከ21ዱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ውስጥ 15ቱ ፍርድ ቤት ቀርበው በግልጽ ችሎት ተሰምተዋል። ሆኖም ግን ዐቃቤ ህግ በክስ መዝገቡ ላይ ተጨማሪ የማስረጃ አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኔ 18 ማስረጃው ቀርቦ እንዲሰማ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ከዚህ ትዕዛዝ አንድ ቀን በኋላ ዐቃቤ ህግ “አንድ ምስክር ከመጋረጃ ጀርባ ለማሰማት” እንዲፈቀድለት ሌላ አቤቱታ አቅርቧል። ዐቃቤ ህግ በግልጽ ችሎት ቀርቦ የሚያውቀውን ነገር ነጻ ሆኖ ማስረዳት ስለማይችል ከስጋት ነጻ ሆኖ የሚያውቀውን እንዲመሰክር የምስክርነት ቃሉን ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ እንዲሰጥ ጠይቋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ይሁን እንጂ እነ ክርስቲያን ታደለ ከመጋረጃ ጀርባ መሰማቱ መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብታችን ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው በሚል አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎትም የስር ፍርድ ቤት የሰጣቸውን ብይኖች እንዲሽር ጠይቀዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት፤ “ጉዳዩ ታይቶ ዕልባት እስኪሰጥ ወይም ተለዋጭ ቀጠሮ እስኪሰጥ ድረስ” የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የዐቃቤ ህግን ምስክር ከመጋረጃ ጀርባ ለመስማት የስር ፍርድ ቤት ዛሬ ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም ቀጠሮ ቢኖርም የዕግድ ትዕዛዙን ተከትሎ ለሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት 10/ 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

- Advertisement -

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News