Homeአበይት ዜናየትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባንክ ሒሳብ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተሰጠ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባንክ ሒሳብ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተሰጠ

Advertisement
World Wide Travel Group
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

መርሻ 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባንክ ሒሳብ እንዲታገድ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ እንዲታገድ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስተላለፈው፣ ከመምህራን ያልተከፈ ውዝፍ ደመውዝ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በኹለት ዓመቱ ደም አፋሳሽ የሰሜኑ ጦርነት ወቅት 17 ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው የትግራይ መምህራን ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ውስደው አስወስነዋል፡፡

ጉዳዩን ከአንድ ዓመት በላይ የተመለከተው የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመምህራን ውዝፍ ደመውዝ እንድከፍል በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አክብሮ የመምህራኑን ውዝፍ ደመወዝ አልከፈለም ተብሏል፡፡

የትግራይ መምህራን ማኅበር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ እና የትግራይ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ምህረተ በየነ (ዶ/ር) ታስረው እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡ ባለሥልጣናቱ ታስረወ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተጠየቀባቸው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ችላ በማለት ለመምህራን መከፈል የነበረበትን ገንዘብ ወጪ አድርገዋል በሚል ነው፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የተከሳሾቹ ጠበቃ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሒሳብ ቁጥር ተቀምጦ የነበረው ገንዘብ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቁ ቀደም ብሎ ወጪ የሆነ በማለት ተከራክሯል፡፡ ገንዘቡ ወጪ የተደረገው ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰራተኞች ደመወዝ መሆኑንም ጠበቃ ማስረዳታቸው ተጠቁሟል፡፡

ይህንኑ ተከተሎ በመምህራን ወገን ከሳሽ የትግራይ መምህራን ማኅበር የፍርድ ቤት ውሳኔ አላከበረም ያለውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባንክ ሒሳብ እንዲታገድ ጠይቋል፡፡ ከከሳሽ በኩል የቀረበለትን አቤቱታ የመረመረው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባንክ አካውንት እንዲታገድ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈቱትን የአስተዳደሩ የባንክ ሒሳቦች ተዘግተው ምርመራ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ የመምህራኑን ውዝፍ ደመውዝ እንዲከፍል ውሳኔ የተላለፈውበት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምርምራ እንዲደረግበት ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባንክ ሒሳብ ታግዶ ለመምህራን ደመወዝ መከፈል የነበረበት ገንዘብ የት እንደገባ እንዲጣራ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ገንዘቡ መቼ ወጪ እንደሆነና ወደ የትኛው ሒሳብ እንደተላለፈ እንዲረጋገጥ ትዕዛዝ የሰተው ፍርድ ቤቱ፣ ጉዳዩን ለመመለከት ለሐምሌ 22/2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

- Advertisement -

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News