Homeአበይት ዜናሽኩቻ የበዛበት ክልል ባለሥልጣን ራሳቸውን  አጠፉ

ሽኩቻ የበዛበት ክልል ባለሥልጣን ራሳቸውን  አጠፉ

Advertisement
World Wide Travel Group
ሙሉነህ ተክሉ

መርሻ

በባለሥልጣናት መካከል የእርስ በእርስ መካሰስና ውዝግብ የበዛበት ሲዳማ ክልል ባለሥልጣን ራሳቸው አጥፍተዋል።

ራሳቸው ያጠፉት ባለሥልጣን የሲዳማ ክልል የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ተክሉ ናቸው። ባለሥልጣኑ ራሳቸውን ያጠፉት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

ባለሥጣኑ ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት ቢሮ ገብተው ሥራቸውን ሲከውኑ ነበር ተብሏል። አስከ ምሳ ስዓት ድረስ በቢሯቸው ከመቆየታቸው በተጨማሪ፣ ምሳም ከባልደረቦቻቸው ጋር መብላታቸው ተጠቁሟል።

ባለሥህጣኑ ከምሳ በኋላ ወደ ቤታቸዉ መሄዳቸውን የገለጸ ሲሆን፣ ብዙም ሳይቆይ ወዲያ ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ ሞታቸው ተሰምቷል። ከአማሟታቸዉ ጋር በተያያዘ ከእውነት የራቁ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን የጠቆመው ዞኑ፣ የተባለው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ብሏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከባለሥጣኑ አሟሟት ጋር በተያያዘ ከተሰራጩት መረጃዎች መካከል ‘በግምገማ ምክንያት’ የሚል እንደሚገኝበትም ጠቁሟል። ባለሥጣኑ ራሳቸውን ያጠፉበት መንግሥታዊ ግምገማ ነው የሚለውን ያጣጣለው ዞኑ፣ በቅርብ ጊዜ የተደረገ ግምገማ የለም ብሏል።

የባለሥልጣኑ አሟሟት ከክልሉ ባለሥልጣናት የእርስ በእርስ ሽኩቻ ጋር የተገናኘ መሆኑም በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ተሰራጭቷል።

አንዳንዶች ባለሥጣኑ ራሳቸው አጠፉ በሚለው ድምዳሜ ላይ ጥያቄ በማንሳት ጉዳዩ በጥልቅ ምርመራ እንድታይ እየጠየቁ ነው።

የዞኑ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ በሰጠው ማብራሪያ ስለ አሟሟታቸው ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን አመላክቷል። የክልሉ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ ስለ መጀመሩም ይሁን፣ ስለ ባለሥጣኑ ሞት ያለው ነገር የለምተ

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የዞኑ ብልግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የባለሥልጣኑ ሞት አረጋግ የሐዘን መግለጫ አውጥቷል። ይሁን እንጂ እንደ ዞኑ አስተዳደር ራሳቸውን እንዳጠፉ ያልገለጸ ሲሆን፣ ጉዳዩን ፖሊስ እንደያውና የምርመራ ውጤቱን ተከታትሎ ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ጠቁሟል።

አቶ ሙሉነህ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት የአለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል። ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው ቀደም ብሎ በተለያዬ ደረጃዎች በመምህርነት ማገልገላቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

- Advertisement -

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News