

የአማራ ማኅበራት ግብረ ኃይል በታላቋ ብሪታንያ ያወጣው መግለጫ 
The Amhara Association Task Force in Great Britain
Email: amharaassociationstaskforceing@gmail.com
Ref No. AATF005/2025
Date: July 29, 2025
ወቅታዊ መግለጫ
የነጻነት ታጋዮችን ቤተሰቦች በመረሸን ትግልን የማስቆምም ሆነ፣ የሃይማኖት ልዩነት ለመፍጠር በሚሸረብ ሴራ የአማራን አንድነት የመበተን ሙከራ በፍጹም አይሳካም፡፡
ትናንት፣ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በሰሜን ወሎ ዞን፣ ራያ ቆቦ ወረዳ፣ ቆቦ ከተማ አስተዳደር፣ ቆቦ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ፊት ለፊት፣ የ75 ዓመት እድሜ ባለጸጋ የሆኑት የአርበኛ አበበ ፋንታሁን አባት አቶ ፋንታው ደርበው በመንግሥት ኃይሎች እጅግ በአሳዛኝ ሁኔታ ተረሽነዋል፡፡
የአማራን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ የአባቶቻቸውን የጀግንነት ፈለግ ተከትለው በተጋድሎ ላይ ያሉትን አርበኛ አበበ ፋንታሁንን እና መላውን አማራ ፋኖን ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ ያቃተው፣ እንዲሁም በዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ የተዘፈቀው የአብይ አህመድ መንግሥት፣ አማራን እስካላጠፋ ድረስ የማያንቀላፋ ፋሽስት እንደሆነ ሁሉም አካል የሚያውቅ ቢሆንም፣ የመጥፊያው ጊዜ እየደረሰ በመጣ ቁጥር እንደ ወረርሽኝ በሽታ ያገኘውን ሁሉ እያጠፋ ይገኛል።
“መግደል መሰሸነፍ ነው” ባለው በራሱ በገዳዩ ቃለ መሰረት ተስፋ የቆረጠ የብልፅግና ወንደበዴ ቡድን ያገኘውን ሁሉ በመግደል የአማራን ቁጥር መቀነስ፣ በአካል እና በስነልቦቸና መግደል በሚል የበታችነት ስሜት የንፁሃን ዜጎችን ህይወት የመቅጠፍ ሂደቱን ከመቼውም በላይ አቀጣጥሎታል፡፡ ይህ በአባታችን ፋንታሁን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የመጨረሻው የንቀት ደረጃ ሲሆን፣ በተለይም በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተባባሪዎችና ገዳዮች “ሙስሊም መስለው ከክርስቲያኑ ጋር” ለማጋጨት ያደረጉት ሙከራ፣ እጅግ አሳዛኝ እና የታሰበበት መንታ ወንጀል ነው። ይህን መሰል ድርቶች በስም የሚታወቁም የማይታወቁም በርካታ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶች፣ እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን የመጫ ማድረግ የሁሉም አማራ ግዴታ ነው፡፡
አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የግፍ ፈፃሚዎች ዋና መሳሪያዎች በውስጥ የሚፈጠር ባንዳ ምክንያት እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ አሁንም በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በውስጥ ባሉ የተሳሳቱ አማራ የሚኒሻ፣ ጥምር ሀይል እና የመከላከያ ተዋጊዎች፣ የሚዲያ አካላት፣ በስውር ተልኮ በገቡ ዲቃላ ምስለ ፋኖዎች እንጂ ጥላት በአማራ ምድር እንድም ቀን እንደማይቆይ እናምናለን፡፡
በመሆኑም የአማራ ማህበራት ግብረ ኃይል የሚከተሉትን መልከቶች ያስተላልፋል፡፡
1. ለአርበኛ አበበ ፋንታሁን፦ የምትወዳቸውን አባትህን በማጣትህ ከልብ እያዘንን መጽናናትን እንመኛለን። አባትህ የሁላችንም አባት ናቸው፤ እርሳቸው ራሳቸው ለእውነትና ለአማራነት ኖረው፣ አንተን በጀግንነት አሳድገው የተሰው አኩሪ ታሪክ ባለቤት ናቸው። እኛም የአባትህን ደም፣ የመላውን አማራንም ደም በጋራ እንደምንጠይቅ ቃል እንገባለን።
2. ለመላው የአማራ ህዝብ፦ አንተን በሃይማኖት፣ በጎጥ እና በእርስ በርስ ግጭት ሊያስጨርስህ የመጣውን አውሬ ለመመከት፣ በሃይማኖትም፣ በጎጥም፣ በሃሳብም ልዩነት ሳትከፋፈል በአንድነት
የአማራ ማኅበራት ግብረ ኃይል በታላቋ ብሪታንያ ያወጣው መግለጫ 
እንድትቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የአባታችን መረሸን ይዞት የመጣውን የጠላት ተልዕኮ ለራሳችን አንድነት የመጠቀሚያ ስልት እናድርገው ዘንድ፣ በጥበበኞች አባቶችህ ስም አደራ እንልሃለን።
3. የህልውና ስጋትን ለመታደግ ለተሰማራችሁ ፋኖዎቻችን፦ የአባታችን መሰዋት አንድ እውነት ይናገራል። የማሸነፊያው ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር፣ ሞተን ሳይሆን ቆመን፣ በህይወት ያሉ የምንወዳቸውን ቤተሰቦቻችንን እያጣን እንሄዳለን። ይህ ከተሰዉት ወንድሞቻችሁ በላይ ህመማችሁን ሊያበዛው ይችላል፤ ከምትወዱት አማራና ከምትወዷቸው ቤተሰቦቻችሁ በላይ ሌላ ልዩነት የለም። ስለሆነም፣ “በአንድነት ቆመን ጥላትን ለማሸነፍ የሚያስችል የሃሳብ አንድነት ከእናት አባታችሁ መሰዋት አይበልጥም” በሚል መሪ ቃል፣ ጊዜ ሳትሰጡ እንድትመክሩ እናሳስባለን።
4. ለሃይማኖት አባቶች፦ ይህ የሃይማኖት ተቋማትን የመድፈር ልምምድ፣ እኛ በህሊናችን የምናያትን እና የምንመኛትን መንግሥተ ሰማያት/ጀነት ትውልድ እንዳያያት፣ ሃይማኖት አልባ ትውልድ የመፍጠር ልምምድ ስለሆነ፣ ሁሉም በየእምነቱ ተግቶ እንዲፀልይ፣ ለእውነትና ለአንድነትም እንዲኖር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
5. ለአማራ ሚኒሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ አባላት አማሮች በሙሉ፡– ባለማወቅ፣ በማወቅ፣ ለቤተሰብ በማሰብ፣ በግል ፀብ፣ በሥራ ግዴታ እና በልዩ ልዩ ምክንያት የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ እየሆናችሁ ነው፡፡ እናንተ ለእኛ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ናችሁ፣የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ መሆናችሁን መስማት፣ ማዬት፣ የታሪክ መዝገባችንም ላይ መፈፃፍ ለእኛ ከፍተኛ ህመማችን ነው፡፡ ዉሀ ከላይ ወደ ታች እንዲሚፈስ የተፈጥሮ ግዴታ እንዶነ ሁሉ የአማራ ንፁሀን ደምም ፍትህ ከሰማይ ከፈጣሪ መምጣቱ የማይቀር እውነት መሆኑን አውቃችሁ የታሪክም ፣ የትውልድም፣ የእምነትም ባለ እዳ እንዳትሆኑ አሁኑኑ ወደ አማራነታችሁ እንድትመለሱ እና በጋራ የአማራን የደም ጎርፍ እንድናቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በመጨረሳም ለመላው ዲያስፖራ ፣ የሚዲያ ባለቤቶች ፣ አክቲቪስቶች እና የትግሉ ደጋፊዎች በሙሉ “የፋኖ ቤተሰብ የሚከበር፣ የሚወደስ፣ የሚመሰገን እንጂ የሚሸማቀቅ እና የሚረሸን አይሆንም” በሚል ቃል በአንድነት በመነሳት የጥላትን ሴራ እንድናከሽፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል ለአማራ ህዝብ!
የአማራ ማኅበራት ግብረ ኃይል በታላቋ ብሪታንያ
__
ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena





