Homeአበይት ዜናበአዲስ አበባ-ጎጃም መስመር ላይ የተጣለው ገድብ ተነሳ

በአዲስ አበባ-ጎጃም መስመር ላይ የተጣለው ገድብ ተነሳ

Advertisement
World Wide Travel Group
አዲስ አበባ - ጎጃም
ፋና ብሮድካስቲንግ

መርሻ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከአዲስ አበባ-ጎጃም መስመር የጣለውን የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

ለተከታታይ አራት ቀናት ተዘግቶ የቆየው የአዲስ አበባ-ጎጃም መስመር ዛሬ ነሀሴ 5/2017 ዓ.ም መከፈቱን ተሰምቷል፡፡ በመንግሥት የተዘጋውን የሞጣ-ባህር ዳር መንገድ ለማስከፈት ታስቦ የተዘጋው መንገድ መከፈቱን የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሩ አስረስ ማረ ገልጸዋል፡፡

የአማራ ፋኖ በጎጃም መንግሥት የዘጋውን መንድ ለማስከፍት በወሰድ የአጻፋ መንድ መዝጋት እርምጃ ከነሀሴ 1/2017 ዓ.ም ጀመሮ መንገዱ መዘጋቱ ይታወሳል፡፡ የአዲስ አበባ-ጎጃም መንገድ መዘጋቱን ተከትሎ፣ በርካታ ተሸከርካሪዎች ባለፉት አራት ቀናት በያሉበት ቆመው ሰንብተዋል፡፡

ከዛሬ ነሀሴ 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ መንገዱ መከፈቱት የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሩ አስረስ ማረ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ መንገድ ለማስከፈት የተዘጋው መንገድ የተከፈተው መንግሥት የዘጋው መንገድ ስለተከፈተ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከሐምሌ መጀመሪያ 2017 ዓ.ም በመንግሥት የተዘጋው የባህር ዳር-ሞጣ መንገድ እስኪከፈት ድረስ የአዲስ አበባ-ጎጃም መንገድ ከአምቡላንስ በስተቀር ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ የደብረ ማርቆስ-ባህር ዳር መንገድ ጌደብ ወንዝ ድልድይ መደርመሱን ተከትሎ፣ መንግሥት የዘጋው መንገድ ሳይከፈት ክልከላው ተነስቷል ተብሏል፡፡

የአካባቢ አብዛኛዎቹ መንገዶች ለተሸከርካሪ ዝግ በሆኑበት አጋጣሚ ድልድዩ መደርመሱ በማኅበረሰቡ ላይ እንቅስቃሴ ላይ ጨኛ መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡ የእንቅስቃሴ ክልከላውን የጣለው የአማራ ፋኖ በጎጃም የማኅበረሰቡን እንግልት ታሳቢ በማድረግ ክልከላውን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

መንግሥት የፋኖ ኃይሎች በስፋት ይንቀሳቀስባቸው ያላቸው መስመሮች ለተሽከርካሪ መዝጋቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከተዘጉት ዋና ዋና መንገዶች መካከል የሞጣ-ባህር ዳር እና ጎጃም ከወሎ የሚያገናኘው የመርጡለ ማርያም-መካነ ሰላም ይገኙበታል፡፡

__

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News