Homeአበይት ዜናኤርትራ ለብልጽግና መግለጫ ምላሽ ሰጠች

ኤርትራ ለብልጽግና መግለጫ ምላሽ ሰጠች

Advertisement
World Wide Travel Group

መርሻ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ኤርትራ ባልዋልኩበት ስሜ ጠፍቷል ላለችበት የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ሰሞነኛ መግለጫ በይፋ ምላሽ ሰጥታለች፡፡

ብልጽግና በኤርትራ ላይ የማያባራ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን የኤርትራው ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡ ቃል አቀባዩ የኤርትራን ስም በማጥፋት ዘመቻ ላይ ተጠምዷል ላሉት ብልጽግና በይፋዊ ኤክስ ገጻቸው በሰጡት ምላሽ፣ መሰረት የሌለው መረጃ በስፋት እያሰራጨ ነው ገልጸዋል፡፡

በኤርትራ ላይ ተከታታይነት ያለው “አሉታዊ እና ሐሰተኛ መረጃ እያሰራጨ ነው” ነው የተባለው ብልጽግና፣ ተሳዳሚ ቡድን መሳማራቱንም የማነ ጠቁመዋል። ብልጽግና በራሱ እንደ ፓርቲ በኤርትራ ላይ ከሚያቀርበው መሰረተ ቢስ ክስ በተጨማሪ፣ ደጋፊዎችንና ተሳዳቢዎቹን ማሰማረቱን የማነ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የማነ ለብልጽግና ምላሽ የሰጡት ፓርቲው ከሰሞኑ የምክር ቤት ሰብሳባ አድርጎ በስም ያልጠቀሳትን ኤርትራን በገደምዳሜ በጦርነት ጠማቂነት ከከሰሳት በኋላ ነው፡፡ ፓርቲው ከምክር ቤት ሰብሰባው በኋላ ባወጣው መግለጫ፣ ኤርትራን በስም ባይጠራም “የተራዘመ ጦርነት የተጨናገፈባቸው” ግጭት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት ከሷታል፡፡

ብልጽግና በመግለጫው “ጦርነት የተጨናገፈባቸው” በሚል የተጠቀመው አገላለጽ የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት በመቆሙ ተከፍታለች የምትባለውን ኤርትራን ለማመላከት ነው፡፡ ኤርትራ በብልጽግና መግለጫ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ተቃናቃኝ ኃይሎችን በማስተባበር ተወንጅላለች፡፡

የማነ ለዚሁ ወንጀላ ብልጽግናን በስም ጠቅሰው በሰጡት ምላሻቸው “የፓርቲ ደጋፊችና ተሳዳቢዎች” በኤርትራ ላይ በየቀኑ “የስድብ መዓት በማውረድ” ተጠምደዋል ብለዋል፡፡ ብልጽግና በኤርትራ ላይ ከፍቷል የተባለው “የስም ማጥፋት ዘመቻ” ኢትዮጵያን ወደኋላ እየጎተተች ነው የሚል መሆኑን የማነ ጠቁመዋል፡፡

ኤርትራ “የኢትዮጵያን ልማት ስታስተጓጉል ቆይታለች” የሚል የስም ማጥፋት እየቀረበባት መሆኑን የማነ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኤርትራ የቀጠናው አገራት እድገትና ብልጽግና ከማስተጓጎል ይልቅ የተሸለ ለውጥ ቢያስመዘግቡ ጠቃሚ ነው ብላ እንደምታምን አመላክተዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የማነ በምላሻቸው “የዜሮ ድምር” የፖለቲካ ስሌት የኤርትራ የቀጠናዊ ፖሊሲ አማራጭ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል። አክለውም የብልጽግናን “ድብቅ ዓላማን ለማራመድ” ሲባል፣ ኤርትራን ሀቅ በሐሰት ትርክት ማጥፋት አይቻልም ብለዋል።

የፕሬዝዳንር ኢሳያስ አፈርቂ እና የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ከፍተኛ ሰጣ ገባ ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል፡፡ ከወዳጅነት በድንገት ወደ ጠላትነት የተቀየረው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ግንኙነት መሻከር፣ ለኢትዮ-ኤርትራ ዳግም ጦርነት መቀስቀስ ምንጭ እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡

__

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

- Advertisement -

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News