Homeዜናበህዳሴ ግድቡ ፕሮጀክት ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት 450 ሚሊዮን ዩሮ ኪራሳ ደርሷል...

በህዳሴ ግድቡ ፕሮጀክት ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት 450 ሚሊዮን ዩሮ ኪራሳ ደርሷል ተብለ

Advertisement
World Wide Travel Group
በህዳሴ ግድቡ ፕሮጀክት _
ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ

ሐሙስ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ/ም

-የተበላሸውን ኮንክሪት ለማስተካከል ተጨማሪ ሦስት ዓመታት መውሰዱ ተነግሯል

በህዳሴ ግድብ ላይ ልምድ የሌለው ኮንትራክተር እንዲሰራ መደረጉ አንድን የኤሌክትሪክ ኃይል ጣቢያ መገንባት የሚያስችል 450 ሚሊዮን ዩሮ ኪሳራ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ስለሀይድሮ ኤሌክትሪክ ምንም አይነት ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት ኢትዮጵያ 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ መክፈሏን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ፕሮጀክቱን ረጅም ጊዜ ያቆየውና ትልቅ መሰናክል የተፈጠረው ምንም አይነት ልምድ የሌለው ኮንትራክተር ውስብስቡን የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራ እንዲሰራ በመደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የበለስ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን ለመገንባት የፈጀውን 460 ሚሊዮን ዩሮ በማሳያነት ጠቅሰው፣ ህዳሴ ግድብ ላይ ልምድ የሌለው ኮንትራክተር እንዲሰራ መደረጉ አንድን የኤሌክትሪክ ኃይል ጣቢያ መገንባት የሚያስችል ኪሳራ አድርሷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ፣ “ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት መንግስት 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ከፍሏል” ብለዋል፡፡ 

ኮንትራክተሩ፣ ኮንትራቱ ከተፈረመ ከሁለት ወራት በኋላ የሲቪል ስራውን መውሰዱን፣ በግድቡ መሰረት ላይ ልል ድንጋይ እንዳጋጠመው፣ ድንጋዩን አውጥቶ መሰረቱን በኮንክሪት ለመሙላት ተጨማሪ ሦስት ዓመት እንደሚወስድበት በወቅቱ መገለጹንም ተናግረዋል፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የሀገር ውስጥ ኮንትራክተር በዘርፉ እንዲበቃ፤ በጥሩ እሳቤ የፕሮጀክቱን ግንባታ መጀመሩን በበጎ ያነሱት ኢንጅነር ክፍሌ፣ መንግስት በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ለኮንትራክተሩ እንዲሰጥ መወሰኑ ትልቅ ስህተት ነበር ሲሉ ተቆጭተዋል፡፡ 

ህፃናት ቁርሳቸውን ትተው፤ እናቶች ከመቀነታቸው ያላቸውን ገንዘብ ሰጥተው፣ ህዝቡ በአጠቃላይ ተሳትፎ ሲሰራ እንደነበር ገልጸው፤ በቂ መረጃ ለህዝቡ ባለመሰጠቱ የኢትዮጵያዊያንን ሞራል በእጅጉ እንደጎዳ  ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ የገጠሙትን ችግሮች በመገምገና የኮንትራት ይዘቱ እንዲቀየር ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

_

- Advertisement -

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News