Homeዜናየጂቡቲና የኬንያ ፕሬዚዳንቶች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይፋዊ ምረቃ እንደሚገኙ አስታወቁ

የጂቡቲና የኬንያ ፕሬዚዳንቶች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይፋዊ ምረቃ እንደሚገኙ አስታወቁ

Advertisement
World Wide Travel Group

ሰኞ ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ/ም

Kenya _ Djibouti _ Ethiopian Dam Inauguration
somaliland.com

የጂቡቲና ኬንያ ፕሬዜዳንቶች ነገ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይፋዊ ምረቃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።  

የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኢል ኦማር  አዲስ አበባ የሚገኙ ሲሆን፣ በዚህም በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ከካረቢን አፍሪካና የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ ባሻገር በህዳሴ ግድቡ ምርቃት እንደሚገኙ ተመልክቷል።

በይፋዊ የፌስቡ ትስስር ገጻቸው በተገለጸው መሠረት ፕሬዚዳንት እስማኤል የኢትዮጵያ 2017 ዓ/ም የመጨረሻዋ ቀን እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ ይኖራቸዋል።

በዚህም ነገ ማለትም ማክሰኞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ይከናወናል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ባለው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ እንደሚሳተፉ በግልጽ ታውቋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

እንዲሁም የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምረቃ ፕሮግራም ላይ እንደሚገኙ ጽሕፈት ቤታቸው ባወጣው መግለጫ በይፋ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ናቸው።

ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም የገነቡት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የራስን መቻል ምልክት ለኢትዮጵያ፣ አዲስ ምዕራፍ መሆኑንም ኬንያ አስታውቃለች።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የራስን መቻል ምልክት ለኢትዮጵያ ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ነው ያለችው ኬንያ፣ ከኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት እያገኘች መሆኑንም አስታውቃለች።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ጽህፈት ቤት መግለጫ፣ ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያገናኛት የኃይል ማስተላለፊያ መሰረት ልማት፤ ከባቢን የማይበክል ኃይል ከኢትዮጵያ በመተጣጣኝ ዋጋ እያገኘች መሆኑን፣ የግድቡ መጠናቀቅ  ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማጠናከር፤ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖራት ያግዛል ብሏል።

በተያያዘ መረጃ፣ በህዳሴ ግድቡ ስለመታደማቸው በግልጽ ባይነገርም የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ ማምራታቸው ታውቋል።

ፕሬዜዳንት ሳልኪር በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከታደሙ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ  ቃል አቀባያቸው አምባሳደር ዴቪድ አሙር ገልጸዋል።

ጽሕፈት ቤታቸው ጉዟቸውን አስመልክቶ፣ “ፕሬዜዳንት ኪር በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅምና በቀጠናዊ ትብብር ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ” ሲል ማስታወቁን ቦርከና ተረድቷል።

- Advertisement -

በህዳሴ ግድቡ ምርቃት የተጋበዙ የሀገራት መሪዎች እነማን እንደሆኑ ከሳምንት በፊት ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበሩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ ተጋባዦቹ እነማን እንደሆኑ በዝርዝር ከመናገር ቢቆጠቡም ለኢትዮጵያ በጎ የሚያስቡ ሀገራት መሪዎች በምረቃው እንደሚጋበዙ ጠቁመው ነበር።

አምባሳደሩ አሁን እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሊካሄድ ስለመሆኑ፣ በጉባዔው እስከ 25 ሺሕ የሚሆኑ ታዳሚዎች እንደሚሳተፉ ጨምር አስቀድመው መግለጻቸውን ቦርከና መዘገቡ ይታወሳል።

በምረቃ ዋዜማ ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደያዘና ከጳጉሜ 2 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮም ውኃው በላይኛው የግድቡ አናት ዘልቆ መፍሰስ እንደጀመረ ታውቋል።

ህዳሴ ግድቡ ግንባታው በ2003 ዓ/ም በቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ተጀምሮ ሂደቱ ለ14 ዓመታት ከቆዬ በኋላ በ233 ቢሊዮን ብር ፈሰስ በ2017 ዓ/ም ተጠናቋል።

ግድቡ 233 ቢሊዮን ብር ለግንባታ ፈሰስ እንደተደረገበት፣ ከአጠቃላይ ወጪው 223 ቢሊየን ብር 91 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዘጠኝ በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ተሳትፎ እንደተገኘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሞኑን መነገሩ ይታወሳል።

_

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News