Homeነፃ አስተያየትየሕዳሴ ግድብ በጸነሰው አላማ ለነማን እና ለምን ጥቅም

የሕዳሴ ግድብ በጸነሰው አላማ ለነማን እና ለምን ጥቅም

Advertisement
World Wide Travel Group
የሕዳሴ ግድብ

በዜግ ፋንታ
መቅድም
(ጽሁፍን በሙሉ በፒዲኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

የሕዳሴን ግድብ በጸነሰው ሰው አላማ መሰረት ለነማን እና ለምን ጥቅም የሚለው ጉዳይ ኢትዮጵያኖች እና የአለም በጎ አድራጊ
ሰዎች ጠይቀው መልስ ያላገኙበት ጥያቄ ነው። ግድቡ ተሰርቶ ቢያልቅም ችግሩ አንዳለ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የማያውቀውን
ዕዳ ተሸክሞ ይገኛል። ግድቡ በሚስጥር ተይዞ ያለ ሕዝብ ዕውቅና እና ፍቃድ ተገንብቷል። ይህ ድርጊት የተፈጸመው በኢትዮጵያ
ጠላቶች ትብብር ነው። ለአንድ ሀገር፣ ለአንድ ሕዝብ በእድገቱና ብልጽግናው ጥረት ላይ ከዚህ የበለጠ በደል ሊፈጸም አይችልም።
ሕዝብ የመሪውን ድርጊት አምኖ እና ተቀብሎ ይሁን ብሎ አይደለም። በራሱ የተደረገው ጭቆና የማያለዋውስ በመሆኑ ነው። የተማረ
ሰው ጠፍቶ አይደለም። ወይም ሽማግሌውና አገር ጠባቂው ከምድሩ ጠፍቶ አይደለም። አገሬቱን በበላይነት የሚያስተዳድረው
የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትሕነግ)በየአንዳንዱ ዜጋ ላይ ከባድ ቁጥጥር በማድረግ አፍኖ ስለያዘው ነው። አንድ አጥፊ መሪ
ሕዝብንና አገርን እስኪያወድም ድረስ መጠበቅ የለበትም። በቃ የሚባልበት ግዜ መኖር አለበት። ይህ ጽሑፍ የቀረበው በዚሁ
መንፈስ ሲሆን፣ የግድቡ አላማ ለነማን እና ለምን ጥቅም እንደተገነባ ግልጽ ለማድረግ ነው።

በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባ ማናቸውም ግድብ ችግሩ አገራዊ ብቻ ሳይሆን አህጉራዊ እንዲሁም የአለም አቀፉን ሕብረተሰብ
የሚያሳስብ ብዙ እንከኖች አሉ። ስለዚህ፣ የአባይ ወንዝ ጉዳይ የሚመለከታቸው አገሮች ሶስቱ ብቻ አይደሉም (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን
እና ግብፅ)። በተዘዋዋሪ ወይም በቀጥታ የሚመለከታቸው የአባይ ወንዝ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑ ብዙ ተፈጥረዋል። በዚህ ምክንያት
የአባይ ወንዝ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ የፖለቲካ ተወናዋዮች ተጨምረዋል ማለት ነው። ስለሆነ፣ የሕዳሴ
ግድብ የብዙ አገር ከባድ ሚናዎች የኢትዮጵያን ችግር እምንት አድርገውታል። የሕዳሴ ግድብ ስራ ሲጀመር ጀምሮ አወዛጋቢ ነበር።
ዋናው ምክንያት፣ የግዙፉ ግድብ ግንባታ፣ አለም ባወቀው በተለመደ የልማት ኢንጂነሪንግ መንገድ ተከትሎ ባለመሄዱ ነበር። ዕቅዱ
በሚስጢር ተወጥኖ ለግንባታ መብቃቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የአለምን ሕዝብ አጥብቆ አሳስቧል።

መለስ ዜናዊ የግድቡ ጸናሽ በማድረግ አድናቆትና ሙገሳ የሚያጎርፉ ብዙ ደጋፊዎች ነበሩ። አብዝሃኛዎቹ በግል ምቾትና በበላይነት
ስሜት የረኩ የትሕነግ ካድሬዎች እና ወያኔዎች (የትግራይ ብሰተኞች)ናቸው። በነሱ ልቦና ግድቡ እንደ ትልቅ ስኬት ተቆጥሯል።
በዚህ ስሜት የተዋጠው ስው፣ ግድቡ ጥቅም መስጠት የሚጀምርበትን ቀን ለማክበር ሽር ጉድ እያለ ነው። የኢትዮጵያ ጠ/ም አቢይ
አህመድ ድግሱን እየመሩ ናቸው። እሳቸውም ከመለስ ዜናው ይበልጥ ተሞጋሽ መሆን አለብኝ ባይ ሆነዋል። መለስ ዜናዊ ከአፄ
ኃይለ ስላሴ ክብሩን ለመንጠቅ ሞክረዋል። ግን ንጉሡን ባንቋሸሹበት ቋንቋ ተንቋሸዋል። አቢይ አህመድም በተራቸው ከመለስ ዜናዊ
ክብሩን ለመንጠቅ እየሞከሩ ናቸው። ተንጠልጥሎ የቀረውን ግድብ ነፍስ የዘራሁለት እናቱም አባቱም እኔ ነኝ ብለዋል። ሁለቱ ባዶ
ክብር ሲነጣጠቁ ማየት ሕዝብን ሳያዝናና አይቀርም። ሟቹ ተገላግለዋል፤ ቢኖሩም አድናቆትን የሚፈልጉ አይሆኑም። ልባቸው ሻክሮ
ነው ያለፉት። አቢይ አህመድ ግን የሕዳሴው ሲኬት ከስማቸው ጋር ቢላከክ ደስ ይላቸዋል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደስ
ብሎት እንደመካሻ ስልጣናቸው እንዲራዘም ይመርጠኛል የሚል ተስፋ ስላላቸው ነው። አቢይ ሰኞ ገባያ ብቅ ማለት አለባቸው።
ገባየተኛው ባለፈው መምረጡን እንዲያነሱበት የሚፈልግ አይደለም። ንጉሡም ደስ የሚላቸው ሕዝብ ምስጋናውን
ለተገደሉት/ለተሰውት ለኢንጂነር ስመኝ ቢሰጥ ነው። የሕዝቡም ምርጫ ይህን ይመስላል።

ሙሉውን በፒ ዲ ኤፍ እዚህ ላይ ያንብቡ

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News