Homeዜናቡና ለመላክ የብቃት ማረጋገጫ የሚጠይቅ የንግድ ማህበር 20 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል...

ቡና ለመላክ የብቃት ማረጋገጫ የሚጠይቅ የንግድ ማህበር 20 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እንዲያቀርብ አስገድጅ መመሪያ ወጣ

Advertise Here
Advertise here

• ለግለሰብ ጠያቂ መነሻ ካፒታሉ ቢያንስ 15 ሚሊዮን መሆን አለበት ተብሏል

አርብ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ/ም


የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት ለሚጠቅይቅ የንግድ ማህበር፣ ግለሰብ እና ባለ አንድ አባል የግል ማህበር አዲስ የተሻሻለ አስገዳጅ መመሪያ ማውጣቱ ታውቋል፡፡

ቡና ላኪነትን በተመለከተ ወጣ የተባለው መመሪያው ለቡና ላኪ የንግድ ማህበር፣ ለግለሰብ እንዲሁም ለባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚጠይቀው መስፈት የተለያየ መሆኑን ቦርከና ከመመሪያው ተመልክቷል፡፡

ይሄው የባለስልጣኑ አዲስ ተሻሽሎ ወጣ የተባለው መመሪያ የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚጠይቅ የንግድ ማህበር በባንክ የተረጋገጠ 20 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታሉ ማቅረብ እንዳለበት ያስገድዷል፡፡  

ከዚህ በሻገር ከባለአክሲዮኖቹ ቢያንስ ሁለት ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው አባላት የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል ይላል መመሪያው፡፡

እንዲሁም፣ የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት የሚጠይቅ የግል አመልካች ደግሞ ቢያንስ 15 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እና የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ በባንክ ተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ እንዳለበት መመሪያው በግልጽ ያስረዳል፡፡

በዚሁ መመሪያ መስፈርት መሰረት፣ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከጠየቀ 20 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እና የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ አለበት ተብላል፡፡

በሌላ በኩል፣ የቡና ጥራት ባለሙያ ሆኖ የሚቀጠር አካል ቢያንስ የዲፕሎማ ማዕረግ ያለው፣ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፣ እውቅና ካለው የቡና ማሰልጠኛ ተቋም የታደሰ የቀማሽነት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን እንዳለበትም የባለስጣኑ መመሪያ ያስገነዝባል፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አዲስ ተሻሻለ የተባለውን መመሪያ ማውጣት ያስፈለገው በቡና ግብይት፣ ጥራትና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1100/2017 ላይ ቡና ላኪዎችን በተመለከተ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ድንጋጌ ተሟልቶ ባለመካተቱ መሆኑን የቡናና ሻይ ባለስልጣን በዚሁ መመሪያ አስረድቷል፡፡

_

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News