Homeየዓለም ዜናመካከለኛው ምስራቅ እና እስያየዶሃው ስብሰባ የቅርብ ጊዜውን የእስራኤል ጥቃት በማውገዝ ተጠናቀቀ

የዶሃው ስብሰባ የቅርብ ጊዜውን የእስራኤል ጥቃት በማውገዝ ተጠናቀቀ

Advertisement
World Wide Travel Group
የዶሃው ስብሰባ
ከማህበራዊ ሜዲያ

ቦርከና ዜና

የአረብ ሀገራት የጋራ የመከላከያ ምክርቤት እና ከፍተኛ ወታጀራዊ ኮሜቴ በቅርቡ በዶሃ አስቸኳይ ስብሰባ እንዳያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል ተብሏል። የአረብ እስላማዊ አስቸኳይ ስብሰባ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ተካሂዷል። ስብሰባው የአረብ እና እስላማዊ ሀገራት የእስራኤልን እብሪት ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። 

ስብሰባው ለዚህም የሚረዳ ህብረት የተንፀባረቀበት እንደነበረ ከስብሰባው በኋላ በወጣው መግለጫ ጠቁመዋል። የአረብ ፓርላማ ፕሬዚዳንት መሀመድ ቢን አህመድ አል ያማሂ ከስብሰባው የተገኘው ውጤት አንድነት የተሞላበት ቅንጅት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያየንበት ውጤት ነው ብለዋል። 

እስራኤል በኳታር ላይ የሰነዘረችውን ጨካኝ ጥቃት በማውገዝ የተባበረ የአረብ እና እስላማዊ አቋም ታይቷል ሲሉ ተናግረዋል። በስብሰባው ከዶሃው ጥቃት በተጨማሪ ላለፉት ሁለት አመታት ጋዛ ውስጥ በፍልስጥኤማውያን ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት አውግዘዋል ተብሏል። 

በስብሰባው ሀገራቱ ለኳታር ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል ነው የተባለው።  ሉዓላዊነትን በሚጥሱ የትኞቹም እርምጃዎችን መታገስ እንደማይገባ አሳስበዋል። ሀገራቱ ቀጠናዊ መረጋጋትን የመፍጠር አስፈላጊነት ላይ በስፋት መወያየታቸውን ገልፍ ታይምስ ዘግቧል። በስብሰባው የፍልስጤም ህዝብ መብት መከበር እንዳለበትና ለዚህም የአረብ ሀገራት ጫና መፍጠር እንዳለባቸው ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አለማቀፉ ማህበረሰብ እየተካሄደ ያለውን ብሄር የማፅዳት እና ዘር የማጥፋት ወንጀል ለማስቆም  ህጋዊ እና ሰብዓዊ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ተብሏል። አጥፊዎች ተጣርተው በአለማቀፍ ፍርድ ቤት ፍርድ እንዳያገኙ ማድረግ ይገባል ብሏል። ያማሂ ስብሰባው ጭቆና እና ወረራ እንድቆም ድምፅ የተስተጋባበት እንደነበር ተናግረዋል። 

በተመሳሳይ መልኩ የአረብ ሀገራት የጋራ የመከላከያ ምክርቤት እና ከፍተኛ ወታጀራዊ ኮሜቴ በዶሃ አስቸኳይ ስብሰባ እንዳያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል ተብሏል።

የመከላከያ አመራሮቹ በሚኖራቸው ውይይት የአባል ሀገራቱን ደህንነት ለመጠበቅ የጋራ መከላከል እርምጃዎችን ለመውሰድ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ይመክራሉ መባሉን ዘፔኒንሱላ ዘግቧል።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጅድ መሀመድ አል ናስሪ ከስብሰባው ጎን ለጎን በሰጡት መግለጫ ስብሰባው በቅርቡ እንደሚካሄድ ገልፀው፣ መቼ እንደሚደረግ ግን  ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አልነስሪ ታሪካዊ በተባለው በዚህ ስብሰባ የገልፍ፣ የአረብ እና እስላማዊ ሀገራት ግንኙነታቸውን ለማቀራረብ የተጠቀሙበት እንደነበር ተናግረዋል።

_

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News