Homeዜናውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ "ኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ይገባታል? አይገባትም? የሚለውን እኛና...

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ “ኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ይገባታል? አይገባትም? የሚለውን እኛና እኛ ብቻ ነን የምንመልሰው” – ሲል ለኤርትራ ምላሽ ሰጠ

Advertisement
World Wide Travel Group

ሐሙስ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም

የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በተመለከተ ኤርትራ እያቀረበችው ላለው ውንጀላና ግብጽ ህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ለጸጥታው ምክር ቤት ላቀረበችው አቤቱታ ጉዳይ የኢትዮጵያ ወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለእነዚህ ጉዳዮች ማብራሪያ የሰጡት የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅና ለረሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ እያቀረበች ያለውን የባህር በር ይገባኛል ጥያቄ ኤርትራ በተደጋሚ እንደ ወንጀል በመቁጠር እየከሰሰች ተስለውላለች።

ስለባሕር በር ጉዳይ ኤርትራ እያቀረበችው ላለው ተቃውሞ የኢትዮጵያ ምላሽ ምን እንደሆነ አምባሳደር ነብያት ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አምባሳደሩም፣ “የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ይገባታል አይገባትም? ለምን ፍላጎት ኖራት? የሚለውን እኛና እኛ ብቻ ነን ልንመልስ የምችለው” ሲሉ ግልጽና አጭር ምላሽ ሰጥዋል፡፡

የባህር በር ለምን እንደሚያስፈልገን በዝርዝር አስረድተናል ሲሉ የተደመጡት አምባሳደር ነብያት፣ የባህር በርን ለማግኘት ኢትዮጵያ የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የባሕር በር ጥያቄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካላትም ቅቡልነት እያገኘ እንደመጣ የተናገሩት አምባሳደሩ፣ “የባህር በር ማግኘት የምንችልበትን ሁኔታ በተመለከተ ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እናራምዳለን” ሲሉ የኢትዮጵያን አቋም አሳውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ አምባሳደሩ ግብፅ ለጸጥታው ምክር ቤት ስላቀረበችው የውንጀላ ደብዳቤ ኢትዮጵያ በቂ ምላሽ መስጠቷንም በዛሬው እለት አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አምባሳደር ነብያት ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ለግብፅ አቤቱታ የኢትዮጵያን ምላሽ የተጠየቁ ሲሆን፣ “ግብፅ ለጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ልካለች፤ የኢትዮጵያ መንግስትም አቋሙን ልቅም አድርጎ ግብፅ ላቀረበችው ክስና ውንጀላ ምላሽ ሰጥቷል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ህዳሴ ግድቡ ተጠናቀቀ ማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከውሃ ጋር በተያያዘ ጥያቄ አይኖርም ማለት አይደለም” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አክለው፣ “በራሱም ሌሎች አዳዲስ ጥያቄዎችንም ሊከፍት ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ግን የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርጋ የመልማት ፍላጎቷን አጠንክራ የምትሰራበት ነው የሚሆነው” ነው ያሉት።

“ለግብፅ ውንጀላ፣ ኢትዮጵያ በዘለቄታ የሚኖራትን የውሃ ሃብቶች መጠቀም መብቷ እንደሆነ በኢትዮጵያ በኩል ምላሽ ተሰጥቷል” ሲሉም አምባሳደር ነብያት ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News