ኩብለላውን ለማስቀረት 1000 ኢትዮጵያውያንን አሰልጥኘ ለውጭ ሀገራት ልሰጥ ነው ብሏል

ቦርከና ዜና
ማክሰኞ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ/ም
ቴክኒሻኖች በገንዘብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በገንዘብ እየኮበለሉ መሆኑ ፈተና ፈጥሮብኛል ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።
አየር መንገዱ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒሻኖችን እያስኮበለለ ነው ለተባሉ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት 1000 ኢትዮጵያውያን አሰልጥኖ ሊሰጥ መሆኑንም ገልጿል።
ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ አስቸገሩኝ ላሏቸው ሀገራት ቴክኒሽያኖችን አሰልጥነው ሊሰጡ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ከዘመን ኢኮኖሚ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒሽያኖችን በገንዘብ እያስኮበለሉ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቴክኒሽያኖች በጣም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ የሚወስዱ የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ አየር መንገዶች አሉ ያሉት አቶ መስፍን፤ የቴክኒሽያኖች መኮብለል በአየር መንገዱ ላይ ፈተና ፈጥሯል ሲሉ ገልጸዋል።
እስካሁን ስንት ሰዎች እንደኮበለሉ ባይገልጹም፣ ሀገራቱ እያስኮበለሉ ከሚወስዷቸው ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ንግግር ተጀምሮ አስኮብላዮቹ የሚፈልጉትን ያህል ቴክኒሽያን አሰልጥነን እንሰጣለን በማለት አቶ መስፍን መግለጻቸው ተሰምቷል።
በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት አየር መንገዶች1000 ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለመስጠት ዝግጅት ማደረጉን ተጠቁሟል።
_
ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






