Homeአበይት ዜናፋኖ የመንግስት ሠራዊትን በስድስት አቅጣጫ ማጥቃቱን እና ገነቴ ከተማን መቆጣጠሩን አስታወቀ

ፋኖ የመንግስት ሠራዊትን በስድስት አቅጣጫ ማጥቃቱን እና ገነቴ ከተማን መቆጣጠሩን አስታወቀ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
06/02/2018

የአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ፣ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እና ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዞች ዛሬ በተለያዩ የጦር ግንባሮች ድል መጎናጸፋቸውን አፋብኃ አስታውቋል።

አፋብኃ ዛሬ ማለትም ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ/ም በተደረጉ ውጊያዎች ቀኑኝ ካላቸው ድሎች አንዱን ሲያስታውቅ፣ አፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አሃዶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ተጋድሎ ገነቴ ከተማን ተቆጣጥረዋል ብሏል።

ንጉስ ሚካኤል ኮር የዘመቻ አባ ናደው የተሳኩ ድሎችን በማስቀጠል ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ነው ሲልም ጠቁሟል።

እንዱሁም፣ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ፣ ዛሬ ከመንግስት ታጠቂዎች ጋር ባደረገው ውጊያ፣ 8 የመከላከያ አባላት ሲሞቱ፣ 5ቱ ከባድና ቀላል ቁስለኛ አድርጓል ሲል አፋብኃ መረጃ አጋርቷል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“ቦታ ለማስፋት ከዋና ካምፓቸው ተነስቶ ወደ ደምደንጋይ ቀበሌ የተንቀሳቀሰውን የመንግስት ሰራዊት በሦስት አቅጣጫ በመምታት በመጣበት እግሩ መትቶ መልሶታል” ሲልም ገልጿል።

ቦታ ለማስፋት ተንቀሳቀሰ የተባለው የመንግስት ሠራዊት “ዜጋንሳ” በተሰኘ ቦታ በፋኖ እየተባረረ ነበር በተባለበት ወቅት፣ ለእገዛ ከአዴት ተወርውሮ ወደ ገረገራ አቅጣጫ የመጣውን የመንግስት ኃይል ደግሞ “ጉርጅባር” ከተባለ ቦታ በደፈጣ ጥቃት ወደመጣበት መመለስ ተችሏል ነው ያለው።

በሌላ በኩል፣ በእየለቱ የሚፈጸመው የፋኖ ሰርጎ ገብ፣ የደፈጣ እና የመደበኛ ውጊያ ያስመረራቸው፣ ከስምንት በላይ የመንግስት ኃይሎች ትጥቅ ያላቸው ይዘው የሌላቸው ከጓደኛቸውን ቀምተው ፋኖን በመቀላቀል ከሞት ድነዋል ሲል አፋብኃ አስታውቋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በእነዚህ ከላይ በተጠቀሱት ሁለት እዞች ዛሬ ተጎናጸፍኩት ካለው ድል በተጨማሪ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ባደረገው ውጊያ በመንግስት ኃይሎች ጥቃት ማድረሱንም ገልጿል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በጀማ ቻይና ካንፕ መሽጎ የነበረውን የመንግስት ወታደር የነበረበት ቦታ ድረስ ዘልቆ ገብቶ ከበባ በማስገባት ከጥቅም ውጪ እንዲሆን አድርጌያለሁ ብሏል።

እንዲሁም፣ ከሦስት ማለትም ከለሚ ወደ ጀማ፣ ከመርሀቤቴ ወደ ጀማ፣ ከመርሀቤቴ አለም ከተማ ወደ ጀማ አቅጣጫዎች ሞርተርና ዲሽቃ ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረን የመንግስት ኃይል በሦስቱም ፋኖ አጥቅጣጫዎች አጥቅቻለሁ ሲል ዕዙ ገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ “ስጋ እያበላን ያስቀመጥነው 100 ሺሕ ገዳ ኮማንዶ ኃይል አለን” ማለታቸውን ያስታወሰው አፋብኃ፣ በተለያዩ የአማራ ክፍሎች ያስገባቸው ኃይሎች ዛሬም የፋኖ ምት አስተናግደዋል ብሏል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ሦስቱ ዕዞች በተለያዩ አቅጣጫዎች ከመንግስት ኃይሎች ጋር አደረጉት ባለው ውጊያ ገነቴ ከተማን ሲቆጣጠር፣ የመንግስት ወታደሮችን በሦስት አቅጣ ድል አድርጌያለሁ ብሏል።

- Advertisement -

የመንግስት ታጣቂዎች በበኩላቸው ፋኖን ድል አድርገናል ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ፋኖ ተቆጣጠርኩት ያለውን ገነቴ ከተማን በተመለከተ ግን ከመንግስት በኩል እስካሁን በቀጥታ የተባለ ነገር የለም።

……….

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News