Homeአበይት ዜናፋኖ ከ170 በላይ የመንግስት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አደረኩ አለ

ፋኖ ከ170 በላይ የመንግስት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አደረኩ አለ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
07/02/2018

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር፣ ዛሬ ከ170 በላይ የመንግስት ታጣቂዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርጌያለሁ ሲል አስታውቋል፡፡

ሰሞኑን በነበረው ውጊያ በመንግስት ወታደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች በተባለችው የፋኖ አባል ግድያ የተበሳጨው ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር በአንድ ቀን ከመቶ በላይ የአገዛዙን ሠራዊት ደምስሻለሁ ብሏል።

“120 በላይ የመንግስት ወታደር ሲደመሰስ፣ ከ50 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል” ያለው ክፍለ ጦሩ፣ “የእህታችን ደም ሳይውል ሳያደር መልሰናል” ሲል ገልጿል፡፡

ባለፉት ቀናት ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር በአዲስ ቅዳም ውጊያ ሲያደርግ እንደነበር መግለጹ የሚታወሰው አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ፣ ዛሬ በነበረው ውጊያ በርካታ ምሽጎችን መስበሩን እና በመንግስት ወታደሮች ላይ ኪሳራ ማድረሱን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“በአውደ ውጊያው በርካታ ምሽጎችን በመሰባበርና የከተማ የጨበጣ ውጊያ በማድረግ የመንግስት ወታደር ተመትቷል” ያለው ክፍለጦሩ፣ በክፍለሩ ጥምር ጦር አዲስ ቅዳም ከተማን መቆጣጠር ተችሏል ብሏል፡፡

“ጥምር ጦሩ አዲስ ቅዳም ከተማን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ጠላትን ድባቅ መትቷል” ያለው ፋኖ፣ የመንግስት ወታደር ዲሽቃና መሰል የቡድን መሳሪያዎችን ቢጠቀምም ከሞት አልዳነም ሲል የቀናውን ድል አስረድቷል፡፡

“የክፍለጦሩ ጦር አዛዥ አውደ ውጊያውን እየመራ ከመንግስት ወታደሮች 2 ክላሽንኮቭ ማርኳል” ሲልም አስታውቋል፡፡

በዛሬው አውደ ውጊያም ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰናል፣ በርካቶችም ተማርከዋል ሲል ጠቁሞ፣ በዚህም ሁለት ብሬን፣ አንድ እስናይፐር እና ከ80 በላይ ክላሽ ገቢ አድርጌያለሁ በማለት በዝርዝር አስረድቷል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የመንግስት ወታደሮች በበኩላቸው “የፋኖ ታጣቂዎችን ገድለናል፣ ማርከናል” ሲሉ በማህበራዊ ሜዲዎቻቸው ሲያሰራጩ ተስተውለዋል፡፡

በተያያዘ መረጃ፣ አፋብኃ ምሥራብ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ፣ ዛሬ በራያ ቆቦ ወረዳ፣ ተኩለሽ፣ ጨፌ ሜዳ፣ በዋ ንጉስጋሌ በተሰኙት አካባቢዎች ከመንግት ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን የሚመለከቱ መረጃዎች ከስፍራው እየወጡ ናቸው፡፡

በዚሁ ውጊያ ፋኖ ድል እንደቀናው እየተነገረ ሲሆን፣ አፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ከዚህ ቀደም በወሎ በኩል ባጠናቀቀው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ ድል፣ “በ18 ቀናት በመቶዎች የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ፣ በሺዎች የሚቀጠሩትን አቆሰልኩ” ማለቱ አይዘነጋም።

እንዲሁም፣ “ከ20 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ማረኩ” ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ዕዙ ይህንን ግዳጁን ካጠናቀቀ በኋላ ዛሬ በራያ ቆቦ የተለያዩ አካባቢዎች ተጋድሎ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

- Advertisement -

……..

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

1 COMMENT

  1. ፋኖ በተለያዩ ጊዜአት የፌዴራል ጦር ሠራዊቱን “ሙትና ቁስለኛ አደረግሁ” ብሎ የዘገበውን ቁጥር ስደማምር ነበር። እውነት አድርጎት ከሆነ እንዴት እና ለምን እስከ ዛሬ አራት ኪሎን መቆጣጠር አልቻለም ብዬ ማሰብ ጀምሬአለሁ። መልሱን የምታውቁ ተስፋ ሳልቆርጥ ቶሎ አስረዱኛ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News