Homeዜናሩሲያ ለኢትዮጵያ የመከላከያን አቅም ለማሳደግ ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

ሩሲያ ለኢትዮጵያ የመከላከያን አቅም ለማሳደግ ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
11/02/2018

ሩሲያ የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም ለማጠናከር ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

ሞስኮ ወታደራዊ ድጋፍ አደርጋለሁ ያለችው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር ከገለጹ በኋላ ነው፡፡

ወደ ሞስኮ ያቀኑት የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በወታደራዊ ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሀገራቸው የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም ለማሳደግ የቀረበላትን ጥያቄ እንምታጤነው ገልጸዋል፡፡

ሩሲያ የኢትዮጵያን መከላከያ ለማጠናከር በቀረበላት “ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ ትብብር ዙሪያ የሀገሪቱን ፍላጎት ለማጤን ዝግጁ ነች” ማለታቸውን ስፑቲኒክ ዘግቧል፡፡ ሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ቀርቧል ያለችውን ፍላጎት፣ ሁለቱ አገራት ወታደራዊ ትብብራቸውን እየጠናከሩ መሆኑ በሚገለጽበት አጋጣሚ ነው፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ታሪካዊ መሰረት ያለው ወታደራዊ ትብብር ያላቸው ሲሆን፣ አሁን ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ምን አይነት ፍላጎት እንዳሳየ ልተገለጸም፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት ሩሲያ ሰራሽ የዘመኑ ጦር መሳሪያዎችን የማግዛት ፍላጎት እንዳለው ይገለጻል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሩሲያ ጋር ከጦር መሳሪያ ግዥ በተጨማሪ፣ ሰፊ በወታደራዊ የቴክኒክ ጉዳዮች የመተባበር ፍላጎት መሳየቱን የስፑቲኒክ ዘገባ ያመላክታል፡፡ ሩሲያም የኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም የማሳደግ ትብብር መሻት ለማሳደግ ጥረት እንደምታደርግ ላቭሮቭ ለጌዲዮን ገልጸውላቸዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዲዮን ጢሞቲዎች በበኩላቸው ለሩሲያው አቻቸው በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል ተብሏል፡፡ ጌዲዮን በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ማብራሪያ ለላቭሮብ የሰጡት ማብራሪያ በዝርዝር ያነሷቸው ጉዳዮች ባይለጹም፣ የኢትዮ-ኤርትራ አሁናዊ ውጥረት አንዱ ሊሆን እንደሚል ይጠበቃል፡፡

ላቭሮው ስለ አፍሪካ ቀንድ ከኢትዮጵያ አቻቸው ማብራሪያ ከቀረበላቸው በኋላ ሩሲያ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነትን እንደምትደግፍ ገልጸዋል፡፡ ላቭሮቭ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ማብራሪያ “በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ፣ በብቸኝነት እና ሙሉ ለሙሉ ዓለም አቀፍ ሕግን በማክበር መፍታት እንደሚያስፈልግ ተስማምተናል” ብለዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ላቭሮብ ሩሲያ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” የሚለውን መርህ ሁሌም ታከብራለች ብለዋል፡፡ ሩሲያ በቀጠናው ሀገራት በሚታዩ ግጭቶች የሰላም አማራጮችን ለመፈለግ ጭምር የአውሮፓ ሀገራት እና የአሜሪካን ጣልቃ ገብተነት እምብዛም አትደግፍም፡፡

ሩሲያ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ወደ ጦርነት እንዲያመራ ከማይፈልጉ ሀገራት መካከል አንዷ ነች፡፡ ሩሲያ ከሁለቱም ሀገራት ጋር ግንኙነቷን ማስቀጠል የምትፈልግ ሲሆን፣ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ረዳጀ ለሁለቱም ሀገራት ስታቀርብ እንደነበር ይገለጻል፡፡

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ከወታደራዊ እሰከ ኒውክሌር ኃይል ልማት ሰፊ ማዕቀፍ ያለው ስምምነት ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡ ሁለቱ ሀገራት የፈረሙት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስምምነት የኢትዮጵያ ቀጠናዊ የበላይነት እንደሚያረጋግጥ ጌዲዮን በውይይቱ ላይ አንስተዋል ተብሏል፡፡

………………

- Advertisement -

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News