Homeዜናጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ሰላም እጦነት ምንጭ ነው ያሉትን ሽፍትነት አጠፋለሁ አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ሰላም እጦነት ምንጭ ነው ያሉትን ሽፍትነት አጠፋለሁ አሉ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
11/02/2018


                  የኦነግ እና ህወሓት “መገንጠል አይሠራም”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን የሰላም ምንጭ ነው ያሉትን ሽፍተነት ለማጥፋት መንግሥታቸው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከእርስ በእርስ ግጭት እሰከ እርስ በእርስ ጦርነት የተንሰራፋውን ቀውስ የሽፈት እንቅስቃሴ ነው ያሉት ዐቢይ፣ መንግሥታቸው የፈጠረው ችግር እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵየ ሰላም እጦት የተለመደ እንጂ እርሳቸው በሚመሩት መንግሥት የተፈጠረ አይደለም ብለዋል፡፡

ዐቢይ ከባልልጣናት ጋር በባሌ ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ ለዘመናት ሰላም እንዳልነበራት በመግለጽ፣ በእርሳቸው አስተዳደር የተለየ ነገር እንዳልተፈጠረ ገልጸዋል፡፡ ትላንት ምሽት በመንግሥታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያዎ በተሰራቸው የባሌ ውይይት ላይ ስለ ሰላም ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስተዳደራቸው መርህ በሽፍታ ደረጃ የተገለጸውን እንቅስቀሴ በማጥፋት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 100 ዓመታት ሰላም አልነበረም። አሁን ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ስላለ፣ በየቀኑ ስለምንሰማው ነው እንጂ የበዛው ሰላም አልነበረም” ሲሉ ተደምጠዋል። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በየዘናቱ ግጭቶች የነበሩ ቢሆንም፣ እንደዚህ ወቅት ማንነትን መሰረት የደረገ የእርስ በእርስ ግጭትና ጦርነት መኖሩ ላይ ብዙዎች ጥያቄ ያነሳሉ፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኢትዮጵያን የሰላም እጦርት ከሽፈት እንቅስቃሴ የመነጨ ነው ያሉት ዐቢይ፣ ሽፍታ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠፍቶ አያውቅም” በማለት ችግሩ የመንግሥታቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥልጣን ዘመናቸው “ሽፍታ ለማሳደድ 100 ፐርሰንት የደከሙ” ያሏቸውን መሪዎችን፣ በተቹበት ንግግር መንግሥታቸው “ሽፍታ እናጠፋለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

የእርሳቸው መንግሥት “ሽፍታ ባህል ስለሆነ እያጠፋነው በአንድ እጃችን እናለማለን” የሚል አካሄድ እንደሚከተል ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የእርስ በእርስ ግጭትና ጦርነት በሽፍታ እንቅስቃሴ ደረጃ የሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህል ሆኗል ያሉትን ሽፍትነት “እናጠፋዋለን” ቢሉም፣ የኢትዮጵያ ሰላም እጦት በሽፍታ ደረጃ የወረደ መሆኑን ላይ ብዙዎች አይስማሙም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ትውልድ ተቀባብሎ የሚያጸናት አገር ትሆናለች። በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እንዳንድ አካባቢ የምናያቸው ጉዳዮች መልክ እየያዙ ይሄዳሉ” ብለዋል።

‘ልገንጠል’ ብሎ ከሰሜን እስከ ደቡብ የተደራጀ ፓርቲ መኖሩን ያነሱት ዐቢይ፤ ከእነዚህ አካላት ውስጥ አንዱም አገሩን አያውቅም፣ ሕዝቡን አያውቅም፣ ባህሉን አያውቅ ብለዋል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ‘ልጠቅልል’ የሚለውም ኢትዮጵያን አላወቃትም። ‘ልገንጠል’ የሚለውም ኢትዮጵያን አላወቃትም” ያሉት ዐቢይ፤ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን (ኦነግ) በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“የእነ ጻድቃን ህወሓት ‘ልገንጠል’ በሚልበት ሰዓት፤ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ወጣቶች በዚያ ዘመን ትግራይን፣ ባህሉን አያውቁትም” ሲሉም፣ በውይይቱ ላይ ወደተሳተፉት ጀነራል ጻድቀን ገብረተንሳይ ጣታቸውን በመቀሰር ተችተዋል፡፡

በተመሳሳይ ኦነግ “እንኳን ኦሮሚያን መገንጠል ቀርቶ የትውልድ ስፍራውን እንኳን በትክክል አያውቀውም፤ ባሌን አያውቅም። ሌላውም ነጻ አውጪ ይኸው ነው” በማለት ተችተዋል።
አክለውም “ልጠቅልል ባዩም ዘመኑን አያውቅም” በማለት የወቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ብትፈልግም ባትፈልግም አይቻልም፤ አለፈ ያ ታሪክ። ከኋላ ጋር መታሰር አያስፈልግም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “መገንጠልም፣ መጠቅለልም አይሠራም። መስማማት፣ በትብብር ሁሉም ያለውን ሀብት እያወጣ እንዲለማ አድርጎ መኖር ብቻ ነው የሚያዋጣው። ይህንን መገንዘብ አለመቻል ነው ችግር ያመጣብን” ሲሉ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

ዐቢይ በንግግራቸው “ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም የለም፣ ሰላም መቅደም አለበት” የሚል ቅሬታ በተለያየ መንገድ እንደሚነሳ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግሥት አቋም፤ “ሰላም እንዲመጣ እንለምናለን፣ ሰላም እንዲመጣ እንሠራለን። ሰላም እስከሚመጣ ግን አንቀመጥም፤ እናለማለን” የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።

- Advertisement -

……….

ቦርከናን ይደግፉ :- እዚህ ገጽ ላይ  

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News