Homeዜናበመልካም አስተዳደር ቅሬታ የሚነሳበት ብልጽግና ፓርቲ አመራሮቹ ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸውን አመነ

በመልካም አስተዳደር ቅሬታ የሚነሳበት ብልጽግና ፓርቲ አመራሮቹ ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸውን አመነ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
18/02/2018

በመልካም አስተደደርና ብልሹ አሰራር ቅሬታ የሚነሳበት ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በከ8 ሺሕ በላይ የፓርቲው አመራሮች እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 8 ሺሕ 613 የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ላይ የዲሲፕሊን ርምጃ መወሰዱን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገልጸዋል።

በፓርቲው አመራሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ ከኃላፊነት ማንሳት፣ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ እና ሽግሽግን ያካተተ መሆኑንም ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

በየደረጃው ያለው አመራር እና አባል በመልካም ስነ-ምግባር ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በቀጣይ የተሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ በማይወጣ፣ ሕዝቡን በታማኝነት የማያገለግል፣ በብልሹ አሰራርና ሌብነት ውስጥ የተዘፈቀ አመራር ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ፓርቲው አሳውቋል።

በየደረጃው ያለው አመራር እና አባል በጥሩ ስነ ምግባር ኃላፊነቱን እንዲወጣ በዚህም የህዝብ ተጠቃሚነትና ኑሮ እንዲሻሻል ስርዓት እንዲገነባ ፓርቲው በትኩረት እንደሚሰራ መነገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ስብሰባ ማካሄዱም ተነግሯል።

……………………

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News