
ቦርከና ዜና
19/02/2018
ተደጋጋሚ የመሬት መንጥቀጥ አደጋ እያስተናገደች ያለችው ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ተቋማዊ የዘርፉ መሳሪያ እንደሌላት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።
ቦርከና፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጂኦፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ከሆኑት አታላይ አየለ (ፕ/ር) ገለጻ እንደተረዳው፣ ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶ የምትከታተልባቸው መሳሪያዎች ከግለሰብ ፕሮጀክቶች የሚመጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በአፋርና በትግራይ ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እየተመታች የተስተዋለች ቢሆንም፣ ክስተቱን መከታተያ ተቋማዊ መሳሪያ የሌላት ከመሆኑ ባሻገር የተማረና የሰለጠ የሰው ኃይል ችግር እንዳለባትም ዩኒቨርሲቲው ተናግሯል።
በዩኒቨርሲቲው የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንደገለጹት፣ በዘርፉ እንደ ሀገር በጀት ተይዞ በበቂ የሰው ኃይል ተሰማርቶ ክትትል የሚየደርግበት ሁኔታ የለም።
በአጠቃላይ ዘርፉ ያለበትን ደረጃ ሲያስረዱም፣ “በበቂ አቅምና ሁኔታ ላይ ነን ማለት አይቻልም፡፡ የምንከታተልባቸው መሳሪያዎች በግለሰቦች ፕሮጀክቶች የሚመጡ ናቸው” ሲሉ ያለውን ክፍተት በግልጽ አስረድተዋል።
ችግሩ ለመቅረፍ፣ መንግስት አቅም በመገንባት እንዲሁም የዘርፉን ክስተት በተመለከተ ወቅታዊ ትንታኔ የሚሰጡና ክስተቶችን የሚመዘግቡ ባለሙያዎችን ሊያሰለጥንና ብቁ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
እንደ የአሜሪካ ጂኦሎጅካል ሰርቬይና ሌሎች ዓለማቀፋዊ ተቋማት የመሬት መንቀጥቀጥን ክስተት ልኬት በቶሎ የሚያወጡት በበጀት፣ በአቅም እንዲሁም በሰው ኃይል የተደራጁ በመሆናቸው መሆኑም ተገልጿል።
ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ የሆኑ በርካታ የዓለም ሀገራት በቂ የሆነ ምርምር እንደሚያደርጉና በመሳሪያም የሚያደርጉት ክትትል በቂና ወቅታዊ መሆኑን ያስረዱት ተመራማሪው፣ በኢትዮጵያም አደጋው እየተደጋገመ በመሆኑ ተመሳሳይ ዝግጅት እንዲደረግ አሳስበዋል።
እንደ አደጉት ሀገራት እንኳ ባይሆን ካሏት መሳሪያዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያን አቅም የሚመጥን መልኩ በመስክ ሊቀመጡ የሚችሉ ዘመኑን የሚመጥኑ መሳሪያዎችና ራሱን የቻለ የዘርፉ ተሽከርካሪ እንዲሟሉ ተጠይቋል።
ኢትዮጵያ ሳይንሱን የሚያውቁ ባለሙያዎች ቢኖሯትም፣ እንደሌሎች ሀገራት በብዛት በቂ እንዳልሆኑ፣ የዘርፉን ስራ ሊያሰራ የሚችል ምቹ የሥራ ሜዳ፣ የመሳሪያ እጥረት፣ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንደሌለ ተቋሙ ገልጿል።
ኢትዮጵያ በአፋር እና በትይራይ ክልሎች በሰውና በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት እስከማድረስ የደረሰ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ያጋጠማት ሲሆን፣ ከቀናት በፊትም በፈንታሌ ተራራ አደጋው ተከስቶ ነበር። የዘርፉ ባለሙያዎችም አደጋው ሊቀጥል እንደሚችል እየገለጹ ናቸው።
………………………………………..
የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






