Homeአበይት ዜናአፋብኃ ከ70 በላይ የብልጽግና ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርጌያለሁ አለ

አፋብኃ ከ70 በላይ የብልጽግና ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርጌያለሁ አለ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
24/02/2018

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በተለያዩ ግንባሮች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች ከ70 በላይ የአገዛዙን ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ አድርጌያለሁ ብሏል።

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ሁለተኛ ኮር፣ ሰባተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ልዩ ኦፕሬሽን በአገዛዙ ጥምር ኃይል ላይ ከፍተኛ ድልን ማግኘት ችያለሁ ሲል ዛሬ አሳውቋል።

በልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከአጸደማርያም እና ሻሁራ ከተማ መሽጎ የነበረው 62ኛና 66ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙ ሰራዊት ተስቦ በአንድ የሞት ወረዳ ከገባ 7ኛ ቀኑን ማስቆጠሩን ገልጿል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“ሠራዊቱ ከገባበት መውጣት ሲያቅተው ባለበት ቦታ ሆኖ ፎቶ እየተነሳ ጭራሽ አጸዳሁ፣ ማረክሁ፣ በተንኋቸው እያለ በየሚዲያው” ይናገራል ያለው አፋብኃ፣ ሆኖም ግን እንዲህ እያለ የማፊያ የሚድያ ስራ እየሰራ ባለበት ቅጽበት በፋኖ ኃይሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል ነው ያለው።

እንዲሁም፣ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ከከሰዓት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ከዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በአገዛዙ ጥምር ኃይል ላይ ከባድ ውጊያ መክፈቱን ፋኖ ገልጿል።

በዚህም የአገዛዙ ኃይል ሸሽቶ ወደ መጣበት ሻሁራ ከተማ ለመግባት ሲያደርግ በነበረው የኋሊት ሩጫ በተከፈተበት ተኩስ፣ 18 ሲገደሉ፣ 24 ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል ብሏል። እንዲሁም፣ ሁለት ኦራልና አንድ አምቡላንስ ሙሉ በሙሉ መጉዳት ችሏል ብሏል።

በሌላ በኩል፣ በሁለተኛው አውደ ውጊያ ሁለቱ የካራማራ እና የአጣናው ዋሴ የክፍለ ጦር በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ መተማ ከተማ በተደረገው አውደ ውጊያ አመርቂ ድል ተግኝቷል ነው የተባለው።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክፍለ ጦር አሳምነው ብርጌድ እና አጣናው ዋሴ ክፍለ ጦር ተካ ብርጌድ ጋር በመጣመር ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ጠላት ወደ መሸገበት መተማ ከተማ ተወርውሮ በመግባት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ሲፋለሙት አድረዋል ተብሏል።

“በዚሁ ኦፕሬሽን የአገዛዙን ቡድን ክፉኛ መውጫ መግቢያ አጥቶ፣ የብልፅግናው አመራርም በየስርቻው ተደብቆ ሲሸበር እና ከባድ በትርም ሲያርፍበት አመሻሽቷል” ሲል አፋብኃ ዛሬ አስታውቋል።

በዚሁ የሌሊት ልዩ ኦፕሬሽን 12 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ 21 ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል ሲል አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ገልጿል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ በበኩሉ፣ ፋኖ ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ወገልጤና ካምፑ ድረስ ዘልቆ በመግባት የአገዛዙን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል ሲል አስታውቋል።

- Advertisement -

በዛሬው እለት ከሁለት በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በካፓቸው ውስጥ ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል ነው ያለው።

……………………………

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News