Homeዜናህወሓት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የመንግሥትን የጦርነት ዝግጅት እንዲያስቆምለት ጠየቀ

ህወሓት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የመንግሥትን የጦርነት ዝግጅት እንዲያስቆምለት ጠየቀ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
24/02/2018

ህወሓት የፌደራል መንግሥት እያደረገ ነው ያለውን “ሌላ ዙር ጦርነት ለማካሄድ ግልጽ እንቅስቃሴ” የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን እንቅስቃሴ እንዲያስቆም አሳቧል።

ህወሓት የሁለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ የሰሜኑን ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ሦስተኛ ዓመትን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግሥቱን አጥብቆ ወንጅሏል፡፡ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ፌደራል መንግሥት ጠፋተኛ እንደሆነ የገለጸው ህወሓት፣ በራሱ በኩል ስለጣሳቸው የስምምነቱ ድንጋጌዎች ያለው ነገር የለም፡፡

ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካማኝነት መፈጸም የነበረባቸው ተግባራት ተፈጻሚ አለመሆናቸውን በመግለጫው አንስቷል። በሁለት ዓመቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት የትግራይ ሕዝብ “ጭፍጨፋ፣ “ፆታዊ ጥቃት፣ መፈናቀል” እንዲሁም ንብረት “ዘረፋ” እና “ውድመት” እንደተፈጸመበት ገልጿል።

ጦርነቱን ለማስቆም ከሦስት ዓመት በፊት የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላም ጦርነቱ “በዝምታ ከሚካሄድ ዘር ማጥፋት ጋር ቀጥሎ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል” ብሏል። በዚህም ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ አለመቻላቸውን እንዲሁም “ወራሪ” ሲል በጠራው ኃይል ሥር የሚኖረው የትግራይ ሕዝብ “እየተገደለ፣ እየታፈነ” እና “በማንነቱ ምክንያት እየተሰቃየ” መሆኑን በማንሳት ወንጅሏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ህወሓት በመግለጫው “”የፍትሕ እና የተጠያቂነት ሂደት እንዲሁም የጦርነቱ መነሻ እና አፈታቱን በተመለከተ ፖለቲካዊ ንግግር አልተጀመረም” ሲል ወቅሷል፡፡ በአጠቃላይ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተጠበቀው ውጤት ሳያመጣ ሦስት ዓመታትን ደፍኗል ያለው ህወሓት፤ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥትን እና በስምምነቱ ሂደት የተሳተፉ አካላትን ወቅሷል።

መግለጫው የፌደራል መንግሥት ፕሪቶሪያ ላይ የተስማማበትን ስምምነት መፈጸም አለመቻሉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሷል። አደራዳሪ አገራት፣ አህጉራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች ስምምነቱ በተፈረመበት መንፈስ እና ተግባራዊ መሆን በጀመረበት ፍጥነት እንዲሄድ መከታተል ላይ ያሳዩት መዘናጋትም ለስምምነቱ በተሟላ ሁኔታ አለመፈጸም አስተዋጾ ማድረጉንም አንስቷል።

ህወሓት የፌደራል መንግሥት የተጣሉበትን ግዴታዎች ካለመፈጸም ባሻገር፤ ስምምነቱን የሚጥሱ ተግባራት ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ በመግለጽ ከስሷል። በትግራይ ሕዝብ እና ብሔራዊ ተቋማቱ ላይ ተከታታይ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እንዲሁም ስም ማጥፋት ማካሄድ ህወሓት በፌደራል መንግሥት ተፈጽመዋል ያላቸው ተግባራት ናቸው።

የፌደራል መንግሥት “ታጣቂዎች በመመልመል፣ በማሠልጠን እና በማደራጀት የትግራይ ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲዋጋ እየሠራ ነው” ሲልም ከስሷል። “ከዚህም አልፎ የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚያፈርስ እና ሌላ ዙር ጦርነት ለማካሄድ ግልጽ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል” በማለት በፌደራል መንግሥት ላይ ውንጀላውን አቅርቧል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት የሚያደርገው እንቅስቃሴ በሁሉም መልክ በጣም የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትል በመጥቀስ አስጠንቅቋል። መንግሥት በጦርነት የሚሟላ ፍላጎትም ሆነ የሚፈታ ልዩነት እንደሌለ አውቆ፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፈጸም ኃላፊነቱን እንዲወጣ እና ፖለቲካዊ ንግግርን እንደመፍትሔ እንዲወስድም አሳስቧል።

……………………………..

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

- Advertisement -

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News