Homeዜናሓራ መሬት ተቀቀናቃኙ ህወሓት ግልጽ ጦርነት ከፍቶብኛል አለ

ሓራ መሬት ተቀቀናቃኙ ህወሓት ግልጽ ጦርነት ከፍቶብኛል አለ

Advertisement
World Wide Travel Group

ህወሓትን ለመዋጋት በአፋር ክልል የተደራጀው ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል ግለጽ ጦርነት ታውጆብኛል ብሏል፡፡ ህወሓት ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ በራያ ግንባር ጥቃት ከፍቶብኛል ያለው ታጣቂ ኃይሉ፣ ተፈጸመብኝ ባለው ጥቃት ተዋጊዎች እንደተገደሉበት ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል፡፡

ሓራ መሬት ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተከፍቶብኛል ባለው ጥቃት የሞቱበትን ተዋጊዎች ቁጠር በውል አልገለጸም፡፡ በህወሓት በኩል ይፋዊ ማረጋገጫ ባይጣም በሓራ መሬት ላይ በከፈተው ጥቃት ቀላል የማይባል ጉዳት ማድረሱን የሚገልጹ መረጃዎች ከስፍራው እየወጡ ነው፡፡

ከሁለት ቀን በፊት በራያ አዘቦ እና ወጅራት አካባቢዎች የተጀመረው የሓራ መሬት እና የህወሓት ኃይሎች ውጊያ እስከ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡ በህወሓት እና በሓራ መሬት መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከሁለቱም ወገኖ በኩል ተዋጊዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው እየተሰማ ነው፡፡

ሓራ መሬት በግልጽ ጦርነት ተከፍቶብኛል ባለበት መግለጫ ተዋጊዎች እንደሞቱበት ጠቅሶ ሐዘኑን ገልጿል፡፡ በህወሓት በኩል በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ከቆሰሉ ተዋጊዎች መካከል ዛሬ አንዱ መሞቱ እየተገለጸ ነው፡፡

በብ/ጀነራል ገብረእግዚኣብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) የሚመራው ሓራ መሬት ተከፍቶብኛል ያለው ግልጽ ጦርነት በሌሎች አካላት ላይ የተቃጣ ነው ብሏል፡፡ ህወሓት በራያ ግንባር ከፍቶታል የተባለው ጥቃት በፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት እና በአካባቢው ሕዝብ ላይ ጭምር የተቃጣ መሆኑን ሓራ መሬት በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ህወሓት በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ አደጋ ድቅኗል ያለው ታጣቂ ኃይሉ ደብቆ ያቆያቸውን ከባድ መዳሪያዎች እያወጣ መሆኑን በመጠቆም ነው፡፡ ህወሓት ከስምምነቱ አፍንግጦ የደበቀውን መድፍ፣ ታንክ፤ ZU-23፤ ሮኬት ከቀበረበት እያወጣ መሆኑን ሓራ መሬት በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ሓራ መሬት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለማፍረስ ጭምር ተከፍቷል ያለው ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተቀበረቡት የወጡ ከባድ መሳሪያዎች ማረጋገጫ ናቸው ብሏል፡፡ በዚሁ መግለጫ ስምምነቱን ጥሶ ወደ ዳግም ጦርነት እየተገባ ነው የተባለው ህወሓት፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የህለውና አደጋ ደቅኗል ሱል ሓራ መሬት ከሷል፡፡

እንደ ጌታቸው ረዳ ባሉ በቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችና በፌደራል መንግሥት ይደገፋል የሚባልለት ሓራ መሬት ለተከፈተበት ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ታጣቂ ኃይሉ የህወሓትን ጥቃት የመቋቋም ተመጣጣኝ አቅም ስለመኖሩ በውል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

ታጣቂ ኃይሉ በመግለጫው የፌደራል መንግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ባለው ህወሓት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡ እንዲሁም የፕሪቶሪያ ስምምነት አደራዳሪዎችና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በተመሳሳይ በህወሓት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ በሓራ መሬት ቀርቦላቸዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በትግራይና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሰፈረው ሓራ መሬት እና ህወሓት መካከል ውጊያ ሲቀሰቀስ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም መተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ጊዜ የተኩስ ልውውጦች አድርገው ከሁለቱም ኃይሎች በኩል ተዋጊዎች መሞታቸውን መዘገቡ ይታወሳል፡፡

………………………………….

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

- Advertisement -

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News