Homeዜና38 የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያ ከኤርትራ እስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

38 የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያ ከኤርትራ እስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
26/02/2018

የኤርትራ መንግሥት በእስር የያዛቸው 100 የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ከእስር ተፈተው፣ 38ቱን በመረብ ድንበር በኩል ወደ ሀገራቸው መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

በኤርትራ መንግሥት በእስር ላይ የነበሩ 100 የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያዊያን ተፈተው 38 ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ቢቢሲ ትግርኛ ዘግቧል፡፡ ከእስር ከተፈቱት ኢትዮጵያዊያን መካከል 38ቱ የኢትዮ-ኤርትራን ድንበር አቋርጠው ትግራይ ክልል መግባታቸው ተገልጿል፡፡

ከእስር የተፈቱ ወገኖች በመረብ ድንበር በኩል ወደ ትግራይ መግባታቸውን የራማ ከተማ ከንቲባ አብርሃለይ ግርማይ አረጋግጠዋል፡፡ በእስር ላይ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች በኤርትራ መንግሥት ተሸኝተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ትላንት ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ነው ተብሏል፡፡

የኤርትራ መንግሥት ከእስር የለቀቃቸው የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያዊያን 100 ቢሆኑም፣ 62ቱ እዚያው አስመራ መቅረታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡ አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ከእስር ከተፈቱ በኋላ እዚያው የቀረቱት የኤርትራ መንግሥት በሰጣቸው ዕድል ነው ተብሏል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኤርትራ መንግሥት የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን ኢትዮጵያን ከእስር ከፈታ በኋላ ወደ ሀገራች የመመለስ ወይም በዚያው የመቆየት ምርጫ ሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር ሰጥቷቸዋል በተባለ ዕድል አብዛኛዎቹ በኤርትራ የተዛመዱና የተዋለዱ እያው መቅረትን መርጠዋል ተብሏል፡፡

በኤርትራ መቆየት መርተዋል ከተባሉት 62 የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን መካከል በአስመራ ተወልደው ያደጉ ይገኙበታል ተብሏል፡፡ ከእስር የተፈቱት ሰዎች የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን በተሰለፈበት፣ በሁለት ዓመቱ የሰሜኑ የህወሓት እና የፌደራል መንግሥት ጦርነት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኤርትራ መንግሥት በወቅቱ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው በአስመራ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በጅምላ ማስሩ ሲነገር ነበር፡፡ እስረኞቹ የተፈቱት ጦርነቱ ከቆመ ከሦስት ዓመታት በኋላ የአሰላለፍ ለውጦች ከተስተው ህወሓት እና የኤርትራ መንግሥት “ጽምዶ” የተሰኘ ጥምረት በፈጠሩበት ወቅት ነው፡፡

100 እሰረኞች መፈታታቸውን ያረጋገጡት የራማ ከተማ ከንቲባ አብርሃለይ እንደገለጹት ከሆነ ኤርትራ መኖር የመረጡት በፈቃዳቸው አዚያው ቀርተዋል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ሁለት ምርጫ እንደሰጣቸው ከአምስት ዓመት እስር የተፈቱት መካከል አንዱ የሆኑት በየነ ገብረኪዳን ለቢቢሲ ትግርኛ ምን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“ከእስር ስንፈታ ፍላጎታችንን እንድንመርጥ ተነገረን” የሚለው በየነ፣ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በትውልድ አካባቢው ትግራይ መርጦ መመለሱን ገልጿል። ከእስር የተፈቱት ሰዎች ብዛት 100 መሆኑን የጠቆመው በየነ፣ በኤርትራ መኖር የመረጡት እዚያው ቀርተዋል ብሏል፡፡

የእስረኞቹ መፈታት ህወሓት እና ኤርትራ በአክቲቪስቶቻቸው በኩል በጀመሩት “ጽምዶ” ወይም ግንኙነት መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡ የወዳጅነትና ባላንጣናት ታሪክ ያላቸው የህወሓት እና የኤርትራ ባለሥልጣናት የፈጠሩት ግንኙነት የኢትዮ-ኤርትራን ድንበር በተናጠል ከፍቶ እሰከመቆጣር ዘልቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ተሳትፎ በሌለበት ሁኔታ ድንበር ከተከፈተ በኋላ የሕዝብ ለሕዝብ ነው የተባለው ግንኙነት በስፋት ይታያል፡፡ ከወራት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በኤርትራ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች እንደ አሁኑ ምርጫ ሳይሰጣቸው በባድመ፣ ራማና ዘላምበሳንበ ድንበር በኩል ወደ ትግርይ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

………………………………………

- Advertisement -

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News