Homeየዓለም ዜናየአፍሪካ ዜናየደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት ተነሱ።

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት ተነሱ።

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
05/03/2018

ቦል ሜል ከማንኛውም የመንግስት እና የፖለቲካ ኃላፊነት እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ተገልጿል።

ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በፃፉት ደብዳቤ የተባረሩት ሜል፣ ፕሬዜዳንት ሳልቫኪርን አመስግነዋቸዋል ተብሏል።

የ52 አመቱ ቤንጃሚን በመኖሪያ ቤታቸው በነበሩበት ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም የአይን አማኞች ተናግረዋል።

እማኞቹ ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት ከተነሱ ከሰዓታት በኋላ የግል ጥበቃዎቹ እንደተቀየሩና የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ዶክመንት ሲወስዱ እንዳዩ ተናግረዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በሀገሪቱ ፖለቲካ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸው በሚነገርላቸው ምክትል ፕሬዚዳንት ቦል ሜል ላይ የወሰዱት እርምጃ ያልተለመደ ነው ተብሏል።

ቤንጃሚን ቦል ሜል በአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ የተጣለባቸው ፖለቲከኛ ናቸው። በቀጣይ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ተተኪ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን ምክትል ፕሬዚዳንታቸውን ቤንጃሚን ቦል ሜልን ከሥልጣናቸው ማሰናበታቸው በጁባ ፖለቲካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ነው የተባለው።

ኪር ቀደም ሲል ሜልን የወታደራዊ ጄኔራልነት ማዕረጉን በመግፈፍ ከብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት አሰናብተዋል።

ከዚህ ባለፈም የቦል ሜል የቅርብ አጋር ናቸው የተባሉትን የማዕከላዊ ባንክ ገዥ እና የገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊን አሰናብተዋል። በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው የማያርዲት መግለጫ ላይ ስለተሰናበቱት ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ውሳኔ የወሰዱት በቅርቡ በእርሳቸው እና በተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቻር መካከል የተደረሰው ሥልጣንን የመጋራት ስምምነት ከፈረሰ በኋላ አገሪቱ ወደ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የእርስ በርስ ጦርነት ልትገባ ትችላለች የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።

የ52 ዓመቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቦል ሜል ከሥልጣን በመባረራቸው ቅሬታ እንዳልተሰማቸው ገልፀዋል።

ይልቁንም ሜል ለኪር በጻፉት ደብዳቤ ላይ “የደቡብ ሱዳንን ሕዝብ በምክትል ፕሬዝዳንትነት የማገልገል ዕድል ስለሰጣችሁኝ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፤ “ደቡብ ሱዳን እና የገዢው ፓርቲ የሱዳን ህዝብ ሊበሪሽን አርሚ (SPLM) በእርስዎ አመራር ስር ከፍ ብለው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነት አለኝ” ብለዋል።

ቦል ሜል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ባለፈው ዓመት 2024 የካቲት ወር ላይ ጄኔራል ጄምስ ዋኒ ኢጋን በመተካት ነበር።

- Advertisement -

የገዢው ፓርቲ የሱዳን ህዝብ ሊበሪሽን አርሚ (SPLM) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበሩት ሜል፣ አቅማቸው እየደከመ የመጡትን የ74 ዓመቱ ኪርን ሊተኩ ይችላሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር።

ፕሬዚዳንቱ ቦል ሜልን በብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት (ኤንኤስኤስ) ውስጥ በነበሩበት ወቅት ወደ ሙሉ ጄኔራልነት ደረጃ ከፍ አድርገዋቸዋል።

ቤል ሜል እድገቱን ያገኙት እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 በሙስና ወንጀል ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ከጣለችባቸው በኋላ ሲሆን ማዕቀቡ በዚህ ዓመትም መጀመሪያ ላይ አንዲቀጥል ተወስኖባቸዋል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ቦል ሜል የፕሬዝዳንት ኪር መንግስት የኢኮኖሚ ዘዋሪ ቀኝ እጅ ናቸው ብሎ የሚያምን ሲሆን። የፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት ግን ይህንን የአሜሪካ መንግሥት እይታ አይቀበለውም። ቦል ሜል በበኩላቸው በእርሳቸው ላይ ለተሰነዘረው የሙስና ክስ በቀጥታ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን መነሳታቸው የተሰማው በፓርቲው ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ መኖሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት መወራቱን ተከትሎ ነው። በፓርቲው ውስጥ ከፋፋይ አካሄድን ይከተሉ ነበር የሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።

ቦል ሜል ከሥልጣን መነሳታቸው በይፋ ከመገለፀው በፊት በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኝ መኖሪያቸው እና ቢሯቸው የሚገኙ ጥበቃዎች እንዲነሱ መደረጋቸው ተገልጿል።
በነዳጅ ሀብቷ የበለፀገችው ደቡብ ሱዳን ከሱዳን በመገንጠል ነጻ አገር ሆና የተመሠረተችው እአአ በ2011 ነው።

ከሁለት ዓመት በኋላ በኪር እና ማቻር መካከል አለመግባባት ከሰፈነ በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ቆይታለች።
እአአ የ2018 የተፈረመው ጦርነቱን ያስቆመው የሥልጣን መጋራት ስምምነት የተለያዩ ተግዳሮቶች እየገጠሙት ሲመጣ በአገሪቱ ውጥረት እየጨመረ እንዲሁም አልፎ አልፎ ግጭቶች መፈጠር ጀምረዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ለማካሄድ ታቅደው የነበሩ አገራዊ ምርጫዎች ሁለት ጊዜ የተራዘሙ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፕሬዚዳንቱ ታማኝ ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ተባብሷል።

ማቻር ከምክትል ፕሬዝደንትነት ተነስተው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በነፍስ ግድያ፣ የአገር ክህደት እና በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ይህ እርምጃ ውጥረቱን የሚያባብስ እና ዳግም ሕዝባዊ አመፅ ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

የማቻር ክስ አሁንም በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ነው። ቃል አቀባያቸው የተከሰሱበትን ክስ “ያልተፈጠረውን ለመፈለግ የተወሰደ ፖለቲካዊ እርምጃ” ሲሉ ገልፀውታል። ክሱ የተመሠረተው ከማቻር ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የሚሊሺያ ቡድን ጥቃት ፈጽሞ መንግሥት 250 ወታደሮች እና አንድ ጄኔራል ተገድለዋል ከተባለ በኋላ ነው ተብሏል።

…………………………………..

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News