Homeየዓለም ዜናየአፍሪካ ዜናፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ኬንያ ለኡጋንዳ የባሕር በር እንድትሰጥ አሳሰቡ።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ኬንያ ለኡጋንዳ የባሕር በር እንድትሰጥ አሳሰቡ።

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
05/03/2018

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ፣ ኬንያ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ለኡጋንዳ የባሕር በር ካልሰጠች ወደፊት በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በማለት ማስጠንቀቃቸው አነጋጋሪ አጀንዳ ሁኗል።

ኡጋንዳ የሕንድ ውቅያኖስን የመጠቀም መብት አላት ሲሉ የተናገሩት ሙሴቪኒ፣ ኡጋንዳ በኬንያዋ ሞምባሳ ወደብ በኩል ከሕንድ ውቅያኖስ ከታገደች ወይም ለውቅያኖሱ የሚኖራት ተደራሽነት እንደ መብት ሳይሆን እንደ ልዩ ጥቅም የሚታይ ከሆነ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል ብለዋል።

ወደብ አልባ አገራት የባሕር በር እንዳያገኙ ማገድ እብደት ነው በማለት ሙሴቪኒ ያወገዙ ሲሆን፣ ኡጋንዳ ለደኅንነቷ እና ኢኮኖሚዋ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ መብት አላት በማለት አጽንዖት ሠጥተው አስረድተዋል።

ኡጋንዳ ወደብ አልባ መሆኗ የባሕር ኃይል ለመገንባት እንቅፋት እንደፈጠረባትም ሙሴቬኒ ጠቁመዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ፣ በባሕር በር ምክንያት ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለውን የፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ማስጠንቀቂያ አጣጥሎ፣ ኡጋንዳ ከሕንድ ውቅያኖስ እንደማትታገድ አስታውቋል።

ሆኖም ኡጋንዳ በሞምባሳ ወደብ የንግድ አገልግሎት ከማግኘቷ ውጪ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የባሕር በር እንድታገኝ ኬንያ ትፍቅድ እንደሆነ ሚንስቴሩ ግልፅ ማብራሪያ አልሰጠም።

አንድ የሚንስቴሩ ከፍተኛ ባለስልጣን ግን፣ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት “የሉዓላዊነት” እና “የተፈጥሮ ሃብት” ጉዳዮች ምን ማለት እንደሆኑ መቼም አይጠፋቸውም የሚል ምላሽ ሠጥተዋል ተብሏል።

……………………………………

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News