
ቦርከና ዜና
09/03/2018
ፕሬዝዳንት ማያርዲት ከሚኒስትሮች በተጨማሪ የግዛት ገዥ እና የፖሊስ አዛዥን ከሃላፊነት ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ባደረጉት የካቢኔ ሹመት አራት ሚኒስትሮችን፣ የግዛት ገዥ እና የፖሊስ አዛዥን ከስልጣን አሰናብተዋል፡፡
በመንግስታዊው የደቡብ ሱዳን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኤስኤስቢሲ) ላይ በተነበበው የመጀመሪያው አዋጅ ጀምስ ዋኒ ኢጋ የኢኮኖሚ ክላስተር ምክትል ፕሬዝዳንት እና ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት ባለፈው ሳምንት የተባረሩትን ቤንጃሚን ቦል ሜልን በመተካት ነው።
ሁለተኛው ድንጋጌ የፍትህ እና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ጆሴፍ ጌንግ አኬክን በማንሳት በቀድሞው የማስታወቂያ እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩኢ ሉዌት ተክተዋል።
በሦስተኛ ትእዛዝ የመንገድ እና ድልድይ ሚኒስትር የነበሩት ሲሞን ሚጆክ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በፒተር ላም ተተክተዋል።ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣብ ለምን እንዳባረሩ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የሰላም ስምምነቱ ፕሬዝዳንቱ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የመንግስት ባለስልጣናትን የመሾም እና የማሰናበት ስልጣን ይሰጣል።በደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ በ2015 ስምምነት ተፈርሟል ፣ ግን በ 2016 እንደገና ፈርሷል ። በ 2018 ዳግም ሌላ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል ፣ ምንም እንኳን አሁንም ስምምነቱ አንዳንድ ችግሮች ቢገጥሙትም ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ከመጋቢት ወር ጀምሮ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ።
የሌሎች ፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎችን መሾም እና ማባረር የሚችለው በአመራራቸው ፈቃድ ብቻ ነው።
ማያርዲት ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስለት ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት በማንሳት ተመሳሳይ እርምጃ ወስደው ነበር፡፡
ቦል ሜል በፕሬዝዳንቱ ከማንኛውም የመንግስት እና የፖለቲካ ኃላፊነት እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ተገልጿል።
ፕሬዜዳንት ማያርዲት በፃፉት ደብዳቤ የተባረሩት ሜል፣ ፕሬዜዳንት ሳልቫኪርን አመስግነዋቸዋል ተብሏል።
የ52 አመቱ ቤንጃሚን በመኖሪያ ቤታቸው በነበሩበት ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በሀገሪቱ ፖለቲካ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸው በሚነገርላቸው ምክትል ፕሬዚዳንት ቦል ሜል ላይ የወሰዱት እርምጃ ያልተለመደ ነው ተብሏል።
ቤንጃሚን ቦል ሜል በአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ የተጣለባቸው ፖለቲከኛ ናቸው። በቀጣይ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ተተኪ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን ምክትል ፕሬዚዳንታቸውን ቤንጃሚን ቦል ሜልን ከሥልጣናቸው ማሰናበታቸው በጁባ ፖለቲካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም የቦል ሜል የቅርብ አጋር ናቸው የተባሉትን የማዕከላዊ ባንክ ገዥ እና የገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊን አሰናብተዋል። በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው የማያርዲት መግለጫ ላይ ስለተሰናበቱት ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ውሳኔ የወሰዱት በቅርቡ በእርሳቸው እና በተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቻር መካከል የተደረሰው ሥልጣንን የመጋራት ስምምነት ከፈረሰ በኋላ አገሪቱ ወደ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የእርስ በርስ ጦርነት ልትገባ ትችላለች የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።
የ52 ዓመቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቦል ሜል ከሥልጣን በመባረራቸው ቅሬታ እንዳልተሰማቸው ገልፀዋል።
ይልቁንም ሜል ለኪር በጻፉት ደብዳቤ ላይ “የደቡብ ሱዳንን ሕዝብ በምክትል ፕሬዝዳንትነት የማገልገል ዕድል ስለሰጣችሁኝ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፤ “ደቡብ ሱዳን እና የገዢው ፓርቲ የሱዳን ህዝብ ሊበሪሽን አርሚ (SPLM) በእርስዎ አመራር ስር ከፍ ብለው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነት አለኝ” ብለዋል።
ቦል ሜል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ባለፈው ዓመት 2024 የካቲት ወር ላይ ጄኔራል ጄምስ ዋኒ ኢጋን በመተካት ነበር።
የገዢው ፓርቲ የሱዳን ህዝብ ሊበሪሽን አርሚ (SPLM) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበሩት ሜል፣ አቅማቸው እየደከመ የመጡትን የ74 ዓመቱ ኪርን ሊተኩ ይችላሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር።
ፕሬዚዳንቱ ቦል ሜልን በብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት (ኤንኤስኤስ) ውስጥ በነበሩበት ወቅት ወደ ሙሉ ጄኔራልነት ደረጃ ከፍ አድርገዋቸዋል።
ቤል ሜል እድገቱን ያገኙት እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 በሙስና ወንጀል ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ከጣለችባቸው በኋላ ሲሆን ማዕቀቡ በዚህ ዓመትም መጀመሪያ ላይ አንዲቀጥል ተወስኖባቸዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን መነሳታቸው የተሰማው በፓርቲው ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ መኖሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት መወራቱን ተከትሎ ነው። በፓርቲው ውስጥ ከፋፋይ አካሄድን ይከተሉ ነበር የሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።
ቦል ሜል ከሥልጣን መነሳታቸው በይፋ ከመገለፀው በፊት በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኝ መኖሪያቸው እና ቢሯቸው የሚገኙ ጥበቃዎች እንዲነሱ መደረጋቸው ተገልጿል።
በነዳጅ ሀብቷ የበለፀገችው ደቡብ ሱዳን ከሱዳን በመገንጠል ነጻ አገር ሆና የተመሠረተችው እአአ በ2011 ነው።
ከሁለት ዓመት በኋላ በኪር እና ማቻር መካከል አለመግባባት ከሰፈነ በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ቆይታለች።
………………………………………………………
የቦርከናን ዮቲዮብ ቻናል ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






