Homeዜናኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታን ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ...

ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታን ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ ማቀዷ ተገለጸ፡፡

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
29/03/2018

የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዛሬ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካዮች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ስራውን መጀመሩን አስታውቋል፡፡ የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ለመገንባት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (አይ.ኤ.ኢ.ኤ) የሚያስቀምጣቸውን 19 መሠረታዊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቃል ተብሏል።

ኢትዮጵያም ይህንኑ መስፈርት አሟልታ በተቆጣጣሪ ኤጀንሲው እገዛና ክትትል ለመስራት ዝግጁ እንደሆነች ተመላክቷል። የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር የስራው ሂደት ሶስት ምዕራፎች ይኖሩታል ያሉ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራውን ለመጀመር ዝግጁ መሆን የሚበሰርበት የዛሬው አይነት ሂደት ነው ብለዋል።

ሁለተኛው ምእራፍ አማራጭና የግንባታ ቦታን መለየት፣የቴክኖሎጂ መረጣ የጨረታ ሂደትና ሌሎችንም ስራዎች ያጠቃልላል ያሉት አብዱረዛቅ፤ ሶስተኛው ምእራፍ የግባታውን ስራ ማጠናቀቅን የሚመለከት እንደሆነ አብራርተዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

እያደገ ባለው የሀይል ፍላጎት ውስጥ የኒክሊየር ሀይል ተጨማሪ አማራጭ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱን ተዓማኒ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በፍጥነት መገንባት አለባት ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የዓለም አቀፉ የኒክሊየር ኃይል ማመንጫ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ (ዶ/ር) ናቸው።
ኢትዮጵያ ከሁለት ወር በፊት የኒክሊየር የኃይል ማመንጫውን ለመገንባት ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ነው። ዛሬ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የተሰናዳው ዝግጅትም ወደ ስራ መገባቱን ማብሰሪያ ትልቁ ምእራፍ ነው ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ የኃይል አቅርቦት ሳይረጋገጥ ከድህነት መውጣት የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያን የኒውክሌር ኃይል ልማት መርኃ ግብር ማስጀመሪያና የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ሥራ ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጌዲዮን፤ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚና የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር በመሆኗ ለሚያስፈልጋት አስተማማኝና ዘላቂ የኃይል አቅርቦት የኒውክለር ኃይል ፕሮግራምን ተግባራዊ ማድረጓን ተናግረዋል።

የኃይል አቅርቦት ሳይረጋገጥ ከድህነት መውጣት የማይታሰብ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም ደህንነትና ሌሎች የአለም አቀፉን የአቶሚክ ኢነርጂ ህግን የሚከተል ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሰንዶካን ደበበ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም መጀመር እና የኮሚሽኑ ወደ ስራ መገባት ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን ለመከታተል የወሰደችው ጠንካራ ውሳኔ ያሳያል ሲሉ ገልጸዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ፕሮግራሙ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር በጤና አጠባበቅ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በምርምር ዘርፎች በማዋል የኢትዮጵያውያንን ህይወት ለማሻሻልም ያለመ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።

በመርኃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሰንዶካን ደበበ፣ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ቦርከና ለመረዳት ችሏል፡፡

………………………………………………..

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News