
ቦርከና ዜና
29/03/2018
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጤነኛ ምግብ እድቀርብልን በመጠየቃችን ጥይት ተተኮሰብን ሲሉ ቅሬታቸው ገልጸዋል፡፡
ከሳምንት በፊት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚያቀርብላቸው ምግብ እንድስተካከል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ጠይቀዋል። በወቅቱ አመጽ ቀስቅሰዋል የተባሉ ተማሪዎች ሰሞኑን በጸጥታ አካላት በኃይል ከዶርማቸው መወሰዳቸውን እና የተወሰኑት መባረራቸውን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ተናግረዋል።
ቅዳሜ ህዳር 27/2018 ዓ/ም ላይ 17 ተማሪዎች ከዶርማቸው ዩኒቨርሲቲው ባሰማራቸው የጸጥታ ኃይሎች እንደተወሰዱና እስካሁን ድረስ ያሉበት እንደማይታወቅ ተማሪዎቹ ገልጸዋል።
ቅሬታቸውን የገለጹት ተማሪዎቹ፤ የተባረሩት እና ማስጠንቀቂየያ የተሰጣቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ሲፃፍ ማየታቸውን ተናግረው፤ ውሳኔው ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው አብራርተዋል፡፡
ተማሪዎቹ አክለውም “ጤነኛ ምግብ እድቀርብልን በመጠየቃችን ጥይት ተተኮሰብን ” ሲሉ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የደረሰባቸውን በማስታወስ ያማረሩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ተማሪዎች በጸጥታ ኃይሎች እንዲወሰዱ እየተደረገ መሆኑ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፤ አስቸኳይ መፍትሄ እንድሰጥ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ምላ የሰጠው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥያቄ ያነሱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ” በጸጥታ ኃይሎች ከዶርማቸው ተወስደዋል” የዩኒቨርሲቲው የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ተበጀ አስተባብለዋል፡፡
ዶክተር አምሳሉ ” በዩኒቨርሲቲያችን ህገወጥ ሰልፍ በመሩና ባስተባበሩ፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ባደረሱ ተማሪዎች ላይ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ የአካዳሚክ የዲስፕሊን ቅጣት ተላልፏል። ከዚህ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ ነው። ዩኒቨርሲቲያችን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራውን እንደቀጠለ ነው ” ሲሉ ቅሬታውን ውድቅ አድርገዋል፡፡
17 ተማሪዎች በጸጥታ ኃይሎች ከዶርማቸው በተመለከተ፤ በሰጡት ምላሽ 17 ተማሪዎች በጸጥታ ኃይሎች ከዶርማቸው ተወስደዋል የሚለው ፍጹም የተሳሳተ መረጃ ነው። የዲስፕሊን ቅጣት አንቀበልም ያሉ 5 ተማሪዎች በፖሊስ እንዲወጡ አድርገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ምግብ ይስተካከልልን ብለው መብታቸውን መጠየቃቸውን በተመለከተም የዩኒቨርሲቲው የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ከመጠየቅ አልፈው በሀይልና በጉልበት ኮብል ስቶን ድንጋይ በመወርወር ግጭት እንዲጀመር ያነሳሱ፣ በሰላማዊ ተማሪዎች፣ የምግብ ቤት ሠራቸኞችና ካምፓስ ፖሊሶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ማምራታቸው ሰልፉን ህገወጥ ያደርገዋል ሲሉ መልሰዋል፡፡
በዚህ ግጭ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎችና በርካታ የፀጥታ አካላት ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የወደመው ንብረት የዶርሚተሪ እና የመመገቢያ አዳራሽ መስታውት መሰበርና፣ ጄኔሬተር የማቃጠል ሙከራ ናቸው ብለዋል፡፡
ዶክተር አምሳሉ አክለውም፤ የዲስፕሊን ቅጣት በተመለከተ በአጠቃላይ ይህን ጥፋት የመሩና ያስተባበሩ የሚመለከተው የዩኒቨርስቲው የስራ ክፍል የተረጋገጠ ሲሆን 5 ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ሲሰናበቱ ፣ 3 ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታቸው የተወገዱ ሲሆን፣ 19 ተማሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ሲሉ አብራርተዋል።
ቅጣቱ በማህበራዊ ሚዲያ ከእውነት የራቁ የዩኒቨርስቲውን ገጽታ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ የማይወክሉ መረጃዎችን የሚያሰራጩት ተማሪዎችን ያካተተ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከሳምንት በፊት ምግብ ይስተካከልልን ብለው በሰላማዊ ሰልፍ ላቀረቡት ጥያቄ ዩኒቨርሲቲው በሚቻለው መጠን በምግብ በኩል የተነሱ ጥያቄዎች ከተማሪዎቹ ጋር በመወያየት ምላሽ እየሰጠ ይገኛል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ይንእንጂ ተማሪዎቹ ግን ያቀረቡት ጥያቄ እንዳልተመለሰላቸውና፤ በአንጻሩ ከዩኒቨርስቲው አመራሮች ዛቻ እና ማስፈራያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
………………………………………………………………….
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






