Homeየዓለም ዜናየአፍሪካ ዜናበዳርፉር በነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉት አሊ መሃመድ አብድአልራህማን የ20 አመት እስር...

በዳርፉር በነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉት አሊ መሃመድ አብድአልራህማን የ20 አመት እስር ተፈረደባቸው።

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
30/03/2018

አለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት በዳርፉር በነበረው ጥሰት በተሳተፉት አሊ መሃመድ አብድአልራህማን ላይ የ20 አመት እስር ወስኗል ተብሏል።

አሊ ኩሻይብ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀውና ከ20 አመታት በፊት በዳርፉር ጭፍጨፋ ወቅት ጃንጃዊድ የተባለው ታጣቂ መሪ የነበረው ግለሰብ ባለፈው ጥቅምት በፈፀማቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ መባሉ ይታወሳል።

ኩሻይብ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ህዝብን በአስገዳጅ መልኩ ከቦታው ማዘዋወር እና ንፁሃንን ማጥቃትን ጨምሮ በ31 ክሶች ጥፋተኛ ተብሏል።

መርማሪዎች የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በወንጀለኛው ላይ የእድሜ ልክ እስራት ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ የ20 አመት እስር ወስኗል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ግለሰቡ በተደጋሚ አሊ ኩሻይብ እኔ አይደለሁም ብሎ መካዱ ሲታወስ ጠበቆቹ የ7 አመት እስር ብቻ እንዲፈረድበት ጠይቀው ነበር።

ከ2003-2004 በነበረው የዳርፉር ጭፍጨፋ ከ300,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ2.5 ሚሊየን በላይ ሰዎችም ተፈናቅለዋል።

የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በዳርፉር ጉዳይ የተሰጠ የመጀመሪያው ውሳኔም ሆኗል።

በ2020 ለአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የመንግስት አካላት ይገድሉኛል በሚል ራሱን አሳልፎ የሰጠው አሊ ኩሻይብ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በእስር ቤት ያሳለፈው ጊዜ ከውሳኔው ላይ ይቀነስለታል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር የሱዳን ታጣቂ መሪ የነበሩትን ሰው ጥፋተኛ ሲል በይኗል።

ከ20 ዓመት በፊት በዳርፉር በነበረው ጦርነት ወቅት በሰብዓዊነት ላይ የተቃጡ ወንጀሎችን ፈፅመዋል የተባሉት እና ጃንጃዊድ የተባለውን ታጣቂ ቡድን መርተዋል የተባሉት አሊ መሐመድ አሊ በፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጧል።

ታጣቂ ቡድኑ በመንግስት ድጋፍ ያገኝ ነበር ሲባል ቡድኑ ለብዙ ሺህ ሰዎች ሞት፣ መደፈር እና የመብት ጥሰት ምክንያትም ነበር።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከዳርፉር ጦርነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ያለበት የመጀመሪያ ጉዳይም ነው ተብሏል።

- Advertisement -

የዳርፉር ጦርነት ጅማሬውን በ2003 ያደረገ ሲሆን በርካታ አረብ ያልሆኑ ሰዎች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈፀመበትም ነው።

ዳርፉር አሁንም ቢሆን ከጦርነት ያልተላቀቀች ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉና የሱዳን ጦር ዋነኛ መፋለሚያ ስፍራ ሆና ቀጥላለች።

ፍርድ ቤቱ አሊ መሐመድ አንድም አረብ ያልሆነ ዘር በአካባቢው እንዳይቀር ለታጣቂዎቹ ትዕዛዝ መስጠታቸውንና ሴቶችን ለወሲብ ባርነት መዳረጉን ገልጿል።

በአጠቃላይ የታጣቂው ቡድን መሪ በ2003 እና 2004 በዳርፉር በነበረው ጦርነት በነበረው ሚና በ27 ክሶች ጥፋተኛ ሆኗል።

በዳርፉር ጦርነት በነበራቸው ተሳትፎ አሊ መሐመድ በቀጣይ የፍርድ ውሳኔው ዛሬ ተላልፎባቸዋል።

አሁን ውሳኔ ይሰጥባቸዋል ከተባሉት የታጣቂ ቡድን መሪ ውጪ ሌሎቹ ያልተያዙ ሲሆን ኦማር አልበሽር በሰሜናዊ ሱዳን በሚገኝ ወታደራዊ እስር ቤት ይገኛሉ።

አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በ2019 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ያጡትን ኦማር አልበሽርን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከዳርፉር ጦርነት ጋር በተያያዘ የእስር መያዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

……………………………………………………..

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News