Homeየዓለም ዜናየአፍሪካ ዜናግብፅ በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞችን ማሰሯ እና ማባረሯ ተነገረ

ግብፅ በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞችን ማሰሯ እና ማባረሯ ተነገረ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
30/03/2018

ግብፅ በቅርቡ ከ150 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞችን በይፋ ባልተገለጸ ምክንያት ሁኔታ ከአገር ማባረሯን በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ኤርትራውያንን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኤርትራውያን በብዛት ከሚኖሩበት የካይሮ ከተማ አካባቢ እንዲወጡ ተደርጎ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ለወራት ከታሰሩ እየታሰሩ ነው ተብሏል፡፡ ኤርትራዊያኑ ከታሰሩ በኋላ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ በሀገራቸው ኤምባሲ ትብብር ጭምር እየተገደዱ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ኤርትራውያን እንደሚሉት ስደተኞቹን የማስወጣት እርምጃ አሳሳቢ የሆነው ዒላማ ያደርገው ሴቶች እና ፈቃድ ያላቸውን ጭምር ያካተተ መሆኑ ነው። አንዳንዶች ከሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ተይዘው መወሰዳቸውን አድል ጨምሮ ተናግሯል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው ስደተኞች እንደሚሉት አብዛኞቹ ኤርትራውያኑ ከአንድ አስከ ሦስት ወራት በእስር ቤት ከቆዩ በኋላ ወደ አገራቸው የሚባረሩት በኤርትራ ኤምባሲ በኩል ነው። ኤርትራውያን ስደተኞች በተለይም ለረዥም ጊዜ በግብፅ ውስጥ የኖሩት ከባድ ችግር እንደገጠማቸው ገልፀው፣ እስሩ እና ከአገር ማባረሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት እየተባባሰ መምጣቱን ይናገራሉ።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ግብፅ ውስጥ ለረዥም ዓመታት የኖረው ሸምድሃን የተባለ ኤርትራዊ እንደሚለው፣ በተለይ ሱዳን ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በርካታ ስደተኞች ወደ ግብፅ መግባታቸው ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል። ከዚህ ቀደምም ከስደተኞች ፈቃድ ወረቀት ጋር በተያያዘ እስር እና ከአገር ማባረር የነበረ ቢሆንም፤ የአሁኑ ግን በአገሪቱ ካለው የኢኮኖሚ እና የምንዛሪ ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

የግብፅ ፓወንድ ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሪ ዋጋ ባለፉት ሦስት ወራት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፣ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት በሚል ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ገንዘብ መንዛሪዎችን እያደነ መሆኑን ተነግሯል። የግብፅ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ ክፉኛ በማሽቆልቆሉ የመሠረታዊ ፍጆታዎች እና የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኤርትራውያኑ ይናገራሉ።

በዚህም የተነሳ የአገሪቱ ዜጎች ከማማረር አልፈው ለችግሩ አንዱ ምክንያት በአገራቸው የበዙት የውጭ አገር ስደተኞች መሆናቸውን በመግለጽ እንደሚያምርሩ እና አንዳንዴም እንደሚተናኮሉ ኤርትራውያን ይጠቅሳሉ።

በተጨማሪም ግብፃውያን በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያሰሙት ቅሬታ ከአገሬው በተለየ የሚከተሉት የአለባበስ ዘይቤ፣ አልኮል መጠጥ እና ጸብ መሆኑን ካይሮ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን ቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በአንድ ወቅት በኤርትራውያን እና በግብፃውያን መካከል የቡድን ጸብ አጋጥሞ የነበረ ሲሆን፣ በጉዳዩ ውስጥም በካይሮ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ገብቶ ከአገሪቱ የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን ስምምነት መፈጠሩን ስደተኞች ያስታውሳሉ።

……………………………………..

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

- Advertisement -

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News