Homeዜናአንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራር ትናንት ምሽት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ...

አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራር ትናንት ምሽት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ።

Advertisement
World Wide Travel Group

01/04/2018
ቦርከና ዜና

በአንድ ሳምንት ውስጥ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቦርከና የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከፍተኛ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ውቤ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ እና እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሁለት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ የከፍተኛ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ውቤ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቦርከና ከተቋሙ ሰራተኞች አረጋግጧል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ሶስቱም ከፍተኛ አመራሮች ማለትም ትናንት ምሽት በፖሊስ የተያዙት አቶ ሀብታሙ ውቤ፣ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ እና አቶ አንዱዓለም ሲዓ፤ በፌደራል ፖሊስ የተጠረጠሩበት ዋና ወንጀል፣ ከውጭ ሀገር ኮንትራክተሮች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ሀገር ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ ገቢ በማሳጣት እና በከባድ የሙስና ወንጀል መሆኑ ተረጋግጧል።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናከር ለታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል ነው የተባለው።

የእስሩ ሂደት የጀመረው ከሳምንት በፊት ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቦርከና የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

አንድ የተቋሙ ሰራተኛ ለቦርከና በሰጡት አስተያየት “የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ተቋሙ በመግባት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕላኒንግ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ኢንጂነር ህይወት እሸቱን እና የቢዝነስ ዘርፍ ዋና ምክትል ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ አንዱዓለም ሲዓን ቢሮ ካስፈተሹ በኋላ በሰራተኞች ፊት በካቴና አስረው ወስደዋቸዋል” ብለዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ ያደረገው ደግሞ፣ እስሩ የተፈጸመው ተቋሙ የፀረ-ሙስና ቀንን ለማክበር ዝግጅት እያደረገ በነበረበት ዋዜማ ላይ መሆኑ ነው ተብሏል።

የፀረ ሙስና ቀንን ለማክበር እቅድ የተያዘው ከቀኑ 10:00 እንደነበር አስታውሶ፣ ሁለቱ አመራሮች ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት 2 ሰዓት ቀድም ብሎ ስምንት ሰዓት አካባቢ መያዛቸውን ተናግሯል።

አስተያየት ሰጭው “መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞቹ ህዳር 25 ‘የፀረ-ሙስና ቀን ይከበራል’ የሚል መልዕክት አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም፣ የዝግጅቱ መሪ መሆን የነበረባቸው አመራሮች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው በተቋሙ ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መደናገርን ፈጥሯል” ሲል አብራርቷል።

በዚህ የሙስና መረብ ውስጥ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ተጨማሪ የስራ ኃላፊዎችም እየተፈለጉ እንደሆነ መስማቱን የነገረን የመረጃ ምንጩ፣ “የእስር ዘመቻው ወደ ሌሎችም ዘርፎች ሊስፋፋ እንደሚችል እየተነገረ ነው፣ ፖሊስ ጉዳዩን በምርመራ እያጣራ ስለሆነ ነው እንጂ በቀጣይ የሚያዙ አመራሮች አሉ” በማለት ተናግሯል።

- Advertisement -

…………………………………………………..

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News