
ቦርከና ዜና
02/04/2018
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ በ15 ቀን ውስጥ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚደረግ ገልጿል።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃኒ ሳይሆን መቆየቱን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች፤ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ቢደረግም የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
የታሪፍ ማሻሺያ እንዲደረግላቸው ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉንም ገልጸዋል።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሺያ የተደረገላቸው የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 80 ብር በሚሸጥበት ወቅት እንደነበር የታክሲ አሽከርካሪዎቹ አስታውቀዋል።
ሆኖም የነዳጅ ዋጋ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ያደረገ ቢሆንም የታሪፍ ማሻሺያው ግን ሳይስተካከል መቆየቱን አስረድተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የታክሲ አሽከርካሪ እንደገለጹት ከሆነ ታሪፉን እንዲያስተካክል የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተጠይቆ እንደነበር አስታውሰው የነዳጅ ዋጋ ሦስት ጊዜ ሲጨምር ታሪፍ ላይ የተደረገ ማሻሻያ ግን የለም ብለዋል።
ከ 80 ብር ወደ 121 ብር ሲጨምር ምንም የታክሲ ታሪፍ ማሻሺያ አልተደረገም በማለት በቅሬታ አብራርተዋል።
ትናንት ታኀሳስ 1/2018 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተሻሽሎ ቀርቧል። ትናንት ከ ቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ 121 ብር ሲሸጥ የነበረውን አንድ ሊትር ቤንዚን 8 ብር ከ 12 ሳንቲም ጨምሮ በ 129.12 ብር እንድሸጥ ተወስኗል።
ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲንም በተመሳሳይ ዋጋ እንዲሸጡ መወሰኑን ቦርከና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ ካደረገው መረጃን መሰረት አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።
በዚህ ሁኔታ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ የትራንስፖርት ታሪፍ ሳይሻሻል መቅረቱ ጫና ፈጥሮብናል ያሉት የታክሲ ሾፌሮች በጥቂት ሳምንታት አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ይደረጋል ብንባልም ተግባራዊ አልተደረገልንም ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዴኤታ አቶ በሪኦ ሐሰን በበኩላቸው “መጥተው ይጠይቁ እኔ ጋር” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
ሆኖም ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ወስጥ ዐዲስ የትራንፖርት ታሪፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሺያ ይደረጋል የሚል እቅድ ይዟል ተብሏል።
……………………………
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






